Saturday, 09 May 2020 12:39

“The Art of Living Dreams” መጽሐፍ ለንባብ በቃ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

    በዶ/ር አብርሃም ፍሰሃዬ የህይወትና የስራ ታሪክ ላይ የሚያጠነጥነውና በራሳቸው በዶ/ር አብርሃም ተጽፎ የተዘጋጀው  “The Art of Living Dreams” መጽሐፍ ለንባብ በቃ፡፡
መጽሐፉ በኤርትራዊው ዶ/ር አብርሃም ፍሰሃዬ የትውልድና የእድገት፣ የስራና አሁን እስካሉበት የሙያ ዘርፍ፣ እንዲሁም እንዴት ከአስመራ ወደ ኢትዮጵያ መጥተው መማርና መስራት እንደጀመሩ የሚተርክ ነው፡፡ የመጀመሪያ የህክምና ዶክትሬታቸውን (MD) ያገኙት በአስመራ ኦሮታ ከተሰኘው የህክምና ት/ቤት ነው፤ ከጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም የህክምና ኮሌጅ ተመርቀውም በጳውሎስ ሆስፒታል የማህፀንና የፅንስ ህክምና ረዳት ፕሮፌሰር ሆነው እያገለገሉ ይገኛሉ፡፡
በ116 ገፅ የተቀነበበው መጽሐፉ፣ በ300 ብርና በ15 ዶላር ለገበያ የቀረበ ሲሆን ኤፕሪል 21 ቀን በጳውሎስ ሚሊኒየም የህክምና ኮሌጅ አዳራሽ ውስጥ ለምርቃት መብቃቱም ታውቋል፡፡

Read 9634 times