ኢንፍሉዌንዛበመባልቀደምሲልየሚታወቀውእንደጉንፋንያለከአየርጸባይወይንምከተለያዩምክንያቶችየተነሳጊዜንጠብቆየሚታይናየሚጠፋግንብዙሰዎችበየጊዜውእንደሚይይዛቸውጉንፋንቀለልያለሳይሆንከበድየሚልሕመምያለውናከሰውወደሰውየመተላለፍባህርይያለውሕመምነው፡፡ ኢንፍሉዌንዛ ኤ እና ቢ በመባልበሁለትየሚለይሲሆን ቢ የተባለውበተለይበሰዎችላይየሚፈጠርሲሆን ኤ የተባለውግንበእንስሶችላይምሊፈጠርየሚችልነው፡፡ ሁለቱምአይነትየኢንፍሉዌንዛሕመሞችከተያዙትሰዎችበማስነጠስወይንምበማሳልጊዜበሚወጣውቫይረሱንየተሸከመእርጥበትአማካኝነትወደሌላውሰውመተንፈሻአካልበመግባትለሕመምይዳርጋልይላልመረጃችን፡፡
በኢንፍሉዌንዛየተያዙሰዎችከዚህየሚከተሉትንምልክቶችሙሉበሙሉምይሁንበከፊልያሳያሉ፡፡
• ትኩሳት፤
• ሳል፤
• ጉሮሮአካባቢሕመም፤
• በአፍንጫበኩልእርጥበትያለውፈሳሽ (ንፍጥ)፤
• የተለያዩየሰውነትክፍሎችወይንምጡንቻዎችሕመም፤
• እራስምታት፤
• ድካም፤
• አንዳንድሰዎች (በአብዛኛውህጻናት) ደግሞየማስታወክእናየተቅማጥሊኖራቸውይችላል፡፡
አንዲትእርጉዝሴትበጉንፋንወይንምበኢንፍሉዌንዛወይንምበሌላሕመምምክንያትየትኩሳትሕመምቢታይባትበተለይምእርግዝናውከመጀመሪያውደረጃማለትምእስከሶስትወርድረስባለውጊዜላይከሆነበተረገዘውጽንስውልደትላይችግርሊያስከትልይችላል፡፡ ከዚህምበተጨማሪእርጉዝዋሴትበትኩሳትሕመምበምትሰቃይበትጊዜየግድወደህክምናመሔድእናሕመሙንመቋቋምእንዲያስችላትከሐኪምጋርበፍጥነትመመካከርናአንዳንድመድሀኒቶችንመውሰድሊኖርባትይችላል፡፡
አንዲትሴትበተለይምበመጀመሪያውየእርግዝናተርምላይእያለችጉንፋንቢይዛትየሚደርስባትየጤናመታወክአስቸጋሪስለሚሆንጥንቃቄማድረግይገባታል፡፡ መረጃውእንደሚገልጸውእርግዝናውእስከሶስትወርእድሜባለውጊዜእርጉዝዋሴትኢንፍሉዌንዛወይንምኃይለኛጉንፋንቢይዛትጽንሱንየማጣትወይንምካለጊዜውየመውለድእጣፈንታወይንምኪሎውአነስተኛየሆነልጅመውለድእንዲያጋጥምምክንያትሊሆንይችላል፡፡ አንዲትእርጉዝሴትኢንፍሉዌንዛሲይዛትበተለይምእርግዝናውበሁለተኛናበሶስተኛደረጃላይየሚገኝከሆነሳንባዋበከፍተኛደረጃኦክስጂንስለሚፈልግሕመሙንጠንካራሊያደርገውይችላል፡፡
እ.ኤ.አ በ2016 በተደረገጥናትእንደታወቀውይህየኢንፍሉዌንዛfluየሚባለውሕመምክትባትበወሰዱትእናባልወሰዱትእርጉዝሴቶችላይልዩነትአሳይቶአል፡፡ክትባትየወሰዱትሴቶችላይሕመሙ በ51%ቀንሶተገኝቶአል፡፡ በዲሴምበር 17/2019 የተደረገውጥናትእንዳመለከተውምበእርግዝናጊዜየሚከሰትኢንፍሉዌንዛወይንምfluበጽንሱላይክብደቱንየመቀነስወይንምካለጊዜውየመወለድሁኔታንሊያስከትልበትእንደሚችልበተደጋጋሚመታየቱንያረጋግጣል፡፡ (Influenza virus may cross the placenta and infect the fetus.) ኢንፍሉዌንዛቫይረስየእንግዴልጅንበማለፍጽንስንሊጎዳእንደሚችልአጥኚዎችይገልጻሉ፡፡ እርግዝናበራሱየእርጉዝዋንሴትተፈጥሮአዊአቅምማለትምልብን፤ሳንባንየመሳሰሉትአካላትላይጫናስለሚፈጥርእንደfluያሉ (ኢንፍሉዌንዛ) ሕመሞችሁኔታውንወደከፋደረጃለማድረስቀላልሊሆንላቸውይችላል፡፡
"A high core body temperature can kill the fetus in the first eight weeks of pregnancy," Dr. Hill…ከፍተኛደረጃየደረሰትኩሳትበእርጉዝዋሴትላይሲከሰትበመጀመሪያውስምንትሳምንታትጊዜውስጥጽንሱእንዲቋረጥምክንያትሊሆንይችላል፡፡ ባጠቀላይምኢንፌክሽንየሚያስከትሉእንደባክቴሪያ፤ቫይረስ፤ፓራሳይትወይንምፈንገስ(bacteria, viruses, parasites or fungi) ያሉበቀጥታምይሁንበተዘዋዋሪመንገድከአንድሰውወደሌላሰውየሚተላፉInfections (ኢንፌክሽኖች)ናቸው፡፡
ከተወሰኑወራትወዲህአለምንያስጨነቀው COVID-19 ኮሮናቫይረስቀደምሲልእ.ኤ.አ በ2003/ ከተከሰተውSARS ከተሰኘውቫይረስጋርተመሳሳይነትቢኖረውም (novel coronavirus) COVID-19 ግንበአይነቱየተለየነው፡፡ አጠራሩም novel coronavirus (ኖቭልኮሮናቫይረስ)የተባለውእስከዛሬድረስተከስቶየማያውቅበአይነቱአዲስየሆነከአሁንቀደምሰዎችበዚህቫይረስሕመምተይዘውየማያውቁበትወረርሽኝበመሆኑነው፡፡
COVID-19 ወቅትንተከትሎከሚከሰተውኢንፍሉዌንዛወይንምጉንፋንጋርበመጠኑበተመሳሳይነትየመተንፈሻአካላትላይሕመምያለውቢሆንምነገርግንበሳንባላይከፍተኛጉዳትየሚያደርስትንፋሽየሚያሳጥርእናየመተንፈሽችሎታንየሚያሳጣእጅግየከፋደረጃያለውሕመምነው፡፡ በአለምላይያሉህዝቦችቀደምሲልየነበረውንኢንፍሉዌንዛወይንምጉንፋንየመቋቋምአቅምያላቸውሲሆንበአዲስመልክየመጣውንኮሮናቫይረስግንለመቋቋምየሚያስችልተፈጥሮአውአቅምማንምየለውምማለትየሚያስችለውበቫይረሱየተያዙሁሉካልታከሙየመዳንአዝማሚያውየማይታመንበመሆኑነው፡፡ኢንፍሉዌንዛወይንምጉንፋንበቤትውስጥበሚደረግየተለያየእርዳታመዳንሲቻልኮሮናቫይረስግንየግድጠንከርያለህክምናመውሰድያስፈልገዋል፡፡
እንደየአለምጤናድርጅትእማኝነትበአለምአቀፍደረጃየኮሮናቫይረስከያዛቸውሰዎችመካከል 3.4%ያህሉሕይወታቸውያለፈሲሆንበኢንፍሉዌንዛምክንያትለህልፈትየተዳረጉትግንበሕመሙከተያዙትውስጥበጣምትንሽማለትምወደ 1%ብቻናቸው፡፡
አንድሰውትኩሳት፤ሳል፤የመተንፈስችግርእናየትንፋሽማጠርምልክትሲታይበትካለምንምማንገራገርበአፋጣኝወደሕክምናመሄድእንዳለበትየጤናመረጃዎችያስጠነቅቃሉ፡፡ ምናልባትምበቫይረሱከተያዙሰዎችአካባቢከነበሩምልክቱ ከ 5-6 ቀንድረስየሚታይበመሆኑእራስንመከታተልተገቢይሆናልእንደWHO ምክር፡፡
COVID-19 የተሰኘውቫይረስቀደምሲልሲታወቅከነበረውኢንፍሉዌንዛጋርየማይመሳሰልአስከፊወረርሽኝእስከሆነድረስበእርግዝናላይያሉሴቶችበእጅጉሊያስቡበትናሊጠነቀቁእንደሚገባማጤንተገቢሲሆንበተለያዩመገናኛብዙሀንየሚገለጹየጥንቃቄመንገዶችንችላማለትበጭራሽአይገባም፡፡
ሰዎችበቫይረሱከተመረዙበሁዋላ ከ5-6 ቀንድረስባለውጊዜትኩሳትናሳል ፤የትንፋሽማጠር፤ የመተንፈስችግርሊደርስባቸውይችላል፡፡ የህመምስሜቱ ከ2-14 ቀንድረስእየጨመረሊሄድይችላል፡፡ ማንኛውምሰውማለትምበእርግዝናላይያሉሴቶችወይንምሕጻናትምልክቱከታየባቸውበፍጥነትተገቢውንሕክምናእንዲያገኙለማድረግቤተሰብድርሻውንሊወጣይገባል፡፡
እርጉዝሴቶችቀድሞውኑምየተለያዩሕመሞችማለትምየልብሕመም፤የስኩዋር ፤የመተንፈሻአካልሕመም፤ካንሰርያለባቸውከሆነእናበኮሮናቫይረስከተያዙይበልጥሊጎዱእንደሚችሉአስቀድሞማወቅያስፈልጋል፡፡ በእርግጥበእርግዝናምክንያትበቫይረሱለመያዝየተለየምክንያትየለም፡፡ ግንእንደማንኛውምሰውቫይረሱቢይዛቸውበእርግዝናውምክንያትያላቸውተፈጥሮአዊየሰውነትአቅምመቀነስንጨምሮየከፋችግርእንዳይገጥማቸውአስቀድሞመጠንቀቅጠቃሚይሆናል፡፡
ምንጭ፡-Influenza (flu) and pregnancy | March of Dimes
www.marchofdimes.org
Saturday, 02 May 2020 12:02
(Influenza) ኢንፍሉዌንዛእናእርግዝና
Written by ፀሐይ ተፈረደኝ ከኢሶግ
Published in
ላንተና ላንቺ