Print this page
Saturday, 25 April 2020 13:15

የዓለም የሃይማኖት መሪዎች አሜሪካ በኢራን ላይ የጣለችውን የሚያሽመደምድ ማዕቀብ ኮቪድ-19 በተደቀነበት ወቅት እንድታነሳ ጠየቁ

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

   የዓለም ቤተ ክርስትያናት ካውንስል፣ አክት አሊያንስና የአሜሪካኑ ብሔራዊ የክርስቶስ ቤተ ክርስትያናት ካውንስል፤ ለአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በጋራ በላኩት ደብዳቤ፤ አሜሪካ በኢራን ላይ የጣለችውንና አገሪቱ ለኮቪድ-19 የምትሰጠውን ምላሽ በእጅጉ እየተገዳደረ የሚገኘውን አቅምን የሚያንኮታኩት ማዕቀብ እንድታነሳ ጠይቀዋል፡፡
“ኖቭል ኮሮና ቫይረስ በየትኛውም ሥፍራ ለሚገኝ የሰው ልጅ ሁሉ የጋራ ጠላት ነው፡፡” የሚለው ደብዳቤው፤”ለዓለማቀፉ ወረርሽኝ ውጤታማ ምላሽ መስጠት ከመቼውም የላቀ ዓለማቀፍ ህብረትና  ትብብርን እንዲሁም ይበልጥ ተጋላጭ ለሆኑት ልዩ ድጋፍን  የሚጠይቅ ሲሆን ተጨማሪ ተጋላጭነት የሚፈጥሩ ሁኔታዎችን ለመቀነስ ፈጣን እርምጃም ይፈልጋል፡፡” ሲል ይመክራል፡፡
የሃይማኖት መሪዎቹ፣ በአሜሪካ የተጣለው ማዕቀብ፣ በኢራን ህዝብ ላይ የሚያሳድረው ተጽዕኖ የሚፈጥረውን ከፍተኛ ስጋት ይጋሩታል፡፡ “በአሁኑ ወቅት ከ67 ሺ በላይ በቫይረሱ የተያዙና ከ4 ሺ በላይ በኮቪድ-19 የሞቱ ሰዎች የተመዘገቡባት ኢራን፤በምስራቃዊ ሜድትራንያን ክልል ክፉኛ የተጠቃች አገር ስትሆን በዓለም ላይ በእጅጉ ከተጠቁ አገራትም አንዷ ናት፡፡” ይላል፤ደብዳቤው:: “የህብረተሰብ ጤና ምላሽዋ ግን ከሜይ 2019 አንስቶ በአሜሪካ በተጣለባት የማያፈናፍን ማዕቀብ የተነሳ ተግዳሮት ገጥሞታል፤ይህም ከሞላ ጎደል አጠቃላይ የኢኮኖሚ እገዳን አስከትሏል፡፡”
አሁን የዓለም ፖለቲካ የሆነው ውንጀላና ነቀፌታ የሚካሄድበት ወቅት  አይደለም ሲል፤ ያሳስባል የሃይማኖት መሪዎቹ ደብዳቤ:: “በአዲሱ ተጨባጭ እውነታ፣ ማናቸውም የብሄራዊ ደህንነት እሳቤ የሚሞረኮዘው ለቫይረሱ በዓለማቀፍ ደረጃ በምንሰጠው ውጤታማ ምላሽ ላይ ነው:: የሚለው ደብዳቤው፤ “አሁን የቫይረሱን ስርጭት ለመቆጣጠር፣ ይበልጥ ተጋላጭ የሆኑትን ለመታደግና  ይህን የጋራ ጠላት ድል ለማድረግ ዓለማቀፍ ህብረትና ትብብር የሚያስፈልግበት ወቅት ነው፡፡” ሲል ያሳስባል፡፡  


Read 1343 times
Administrator

Latest from Administrator