Monday, 20 April 2020 00:00

“ጋዜጠኞች” ሙያችሁን ለማስከበር በራሳችሁ ላይ ዝመቱ!

Written by  (ከአብዱራህማን አህመዲን፤ የቀድሞ የፓርላማ አባል)
Rate this item
(2 votes)

የዛሬ ሁለት ሳምንት በዚሁ ርዕስ ስር በቀረበው ክፍል 2 ጽሑፍ ስለጋዜጠኛነት ምንነት (ትርጉም) እና ስለ ጋዜጦች ህትመት አጀማመር፣ ስለሬዲዮ፣ ቴሌቪዢንና ዲጂታል ዲያ ታሪካዊ አመጣጥ፣ ስለ ጋዜጠኛነት መርሆዎችና የስነ ምግባር ደረጃዎች (principles and ethical standards) ምንነት፣ የተለያዩ ሀገሮችን የጋዜጠኞችና የጋዜጠኛነት የስነ ምግባር ደንብ ይዘትና ተያያዥ ጉዳዮች አጠር ያለ ማብራሪያ መቅረቡ ይታወሳል፡፡ በዚህ መጣጥፍ ደግሞ፤ “ጋዜጠኞችሙያችሁንለማስከበርበራሳችሁላይዝመቱ”ያልኩበትንምክንያት፤ እንዲሁምስለ ሀገራችንሜዲያዎችና ስለዘመኑ የሀገራችን ጋዜጠኞችያለኝንአስተያየትበአጭሩ ለማቅረብ ጥረት ይደረጋል፡፡
ደጋግሜ እንደጠቀስኩት አንጋፋውጋዜጠኛናደራሲበዓሉግርማ“ጋዜጠኛነትላብናደምንይጠይቃል” ይላል፡፡በአሁኑወቅትግንላብናደምሳይሆንማይክመጨበጥብቻሰዎችንጋዜጠኛእያደረጋቸውነው፡፡በአሁኑወቅትግንላብናደምሳይሆንበፌስቡክሁለትመስመርጽሁፍመጻፍብቻሰዎችንጋዜጠኛእያደረጋቸውነው፡፡… በአሁኑወቅትግን ጋዜጠኛነት መንገደኛው ሁሉ ዘው ብሎ የሚገባበት “ተራ ሙያ” ሆኗል፡፡ እናም በአሁኑወቅትበሀገራችንእየሞቱካሉትሙያዎችአንዱጋዜጠኛነትነው ብል ከሀቁ ብዙም የራቅኩ አይመስለኝም፡፡ (ምክንያቴን በጽሁፉ ሂደት ታገኙታላችሁ)
የዚህን ጽሁፍ ረቂቅ ማዘጋጀት ከጀመርኩ አንድ ወር ያህል ተቆጥሯል፡፡ በዚህ የአንድ ወር ጊዜ ውስጥ በሀገራችን ባሉ መገናኛ ብዙሃን ዙሪያ ያጋጠሙኝን የጋዜጠኛነት “ህፀፆች”የጽሑፌ መንደርደሪያ አድርጌ ለማቅረብ ወደድሁ፡፡ በቅርብ ጊዜ የተፈጸሙ ስለሆኑ ለብዙዎቻችን እንግዳ አይሆኑም ብየ አስባለሁ፡፡
ባለፈው መጋቢት ወር አጋማሽ አካባቢ በአንድ ምሽት የኢትዮጵያ ሬዲዮን ዜና ፋይል እያዳመጥኩ ነበር፡፡ የዜና ፋይል የእለቱ አጋፋሪ አንድ የዜና ርእስ አነበበና ለዝርዝሩ ወደ ዜና አጠናቃሪ (ዘጋቢ) ዘንድ መራ፡፡ (የቀጥታ ስርጭት መሆኑን ልብ በሉ) የዜናው ዘጋቢ የሆነች ሴት ጋዜጠኛ ሪፖርት ማቅረብ ጀመረችና (በምን ምክንያት እንደሆነ ባናውቅም) ሳቋን ለቀቀቺው፡፡ እንደምንም ተቆጣጥራ ለመቀጠል ሞከረች… አልቻለቺም… ዘገባው ተቋረጠ… ተረኛ አዘጋጁ ወደ ሌላ ዜና ተሸጋገረ… ጣቢያው ለተፈጠረው ሁኔታ ህዝብን ይቅርታ አልጠየቀም… ጋዜጠኛዋም ይቅርታ አልጠየቀቺም… “ውሾን ያነሳ ውሾ ይሁን” ተብሎ ታለፈ…
በዚያው ሰሞን የፋና ቴሌቪዥንን ዜና ስከታተል ነባር ጋዜጠኛዋ ለቃለ ምልልስ የጋበዘቺውን እንግዳ ስም በአግባቡ መጥራት አቅቷት ስትዘባርቅ አየኋት፣ ሰማኋት… ይህቺ ጋዜጠኛ የአንድ ሰሞን የፌስቡክ መሳቂያ መሳለቂያ ሆና ሰነበተች፡፡ ቴሌቪዥን ጣቢያውም ሆነ ጋዜጠኛዋ ህዝብን ይቅርታ ስለመጠየቃቸው የሰማሁትም ያየሁትም ነገር የለም፡፡ ይሄም “ውሾን የሰነሳ ውሾ ይሁን” በሚል መንፈስ ታለፈ…
ጊዜው ራቅ ቢልም ጋዜጦችና መጽሄቶችም ተመሳሳይ ስህተቶችን ሲፈጽሙ እንደነበር አስታውሳለሁ፡፡ በተለይም ከ1990ዎቹ መጀመሪያ እስከ ምርጫ 97 ድረስ ባሉት ዓመታት ጋዜጦች ጯሂ ርዕስ በመጻፍ ውስጡ ሲነበብ ከርእሱ ጋር የማይገናኝ ዜና ያቀርቡ ነበር፡፡ ለምሳሌ፤ “ፕሬዝዳንቱ ሙቱ፣ ጠቅላይ ሚንስትሩ ስልጣን ለቀቁ… ወዘተ.” የሚል ርእስ በትልልቅ ሆሄያት (Font - ፎንት) በፊት ገጹ ላይ ጽፎ የወጣ ጋዜጣ ውስጡ ሲነበብ የሌላ ሀገር ፕሬዝዳንት ወይም ጠቅላይ ሚንስትር ዜና ሆኖ ይገኛል፡፡ እንዲህ ያደረገ የጋዜጣ ዝግጅት ክፍልም ሆነ ዜናውን ያጠናቀረ ጋዜጠኛ ህዝብን ይቅርታ ጠይቆ አያውቅም፤ በህግ የሚጠይቀውም አካል የለም፡፡
የሌላው የጋዜጠኛነት ሙያ መለኪያ ቋንቋ ነው፡፡ አንድ ጋዜጠኛ የሚሰራበትን ቋንቋ በአግባቡ ማወቅ ይጠበቅበታል የሚል እምነት አለኝ፡፡ ይህም ሁለት ጥቅም አለው፡፡ አንደኛ፤ መልእክቱን ሳይዛባ ለማድረስ ያስችለዋል፤ ብዥታም ውዥንብርም አይፈጥርም፡፡ ሁለተኛ፤ ለቋንቋው እድገትና በቋንቋውም አማካይነት የህዝብን ባህል፣ ወግና ልማድ ለመመዝገብና ለማስተዋወቅ ይረዳል፡፡ በመሆኑም ጋዜጠኛነትን “አንቱ” ከሚያሰኙት ነገሮች አንዱ የጋዜጠኞች የቋንቋ አጠቃቀም ነው በሚለው ላይ ብዙዎች ይስማማሉ፡፡
በደርግ የአስተዳደር ዘመን በአሜሪካ እና በጀርመን ድምፅ ሬዲዮ የአማርኛ ፕሮግራም አዘጋጅ የነበሩ ጋዜጠኞች ዘገባዎቻቸውን በሚያቀርቡበት ወቅት አዳዲስ ቃላትን በመጠቀም፣ በተለይም የእንግሊዝኛ ቃላትን ወደ አማርኛ በመመለስ፣ ተወዳጅና ዝነኛ ፕሮግራሞችን ያቀርቡ እንደነበር አስታውሳለሁ፡፡ የዚያ ዘመን የኢትዮጵያ ሬዲዮ/ቴሌቪዥን የአማርኛ ፕሮግራም ጋዜጠኞችም የእንግሊዝኛ ቃላትን ከመጠቀም ይልቅ ከግዕዝና ከሌሎች አገር በቀል ቋንቋዎች በመዋስ ወይም በማዳቀል አዳዲስ የአማርኛ ቃላትን ይፈጥሩ ነበር፡፡ ብዙዎቹ ጋዜጠኞች የራሳቸው የሆነ የአነባበብ ዘዬ ነበራቸው፡፡ (የዳሪዎስ ሞዲ፣ ታደሰ ሙሉነህ፣ ዓለምነህ ዋሴ፣ ነጋሽ ሙሐመድ፣ በቀለ ተሾመ፣ ጎርፍነህ ይመር፤ ደምሴ ዳምጤ፣ ልዑልሰገድ ኩምሣ፣ ጌታቸው ኃ/ማሪያም፣ ጋሽ ሰለሞን ገ/ስላሴ፣ ብርቱካን ሐረገ ወይን፣ ሚሊዮን ተረፈ፣ ንግሰት ሰልፉን… የአነባበብ ድምፆች ያስታውሷል፡፡ ዛሬ ዛሬ የራሱ የአነባበብ ስልት ያለው ጋዜጠኛ አለ ይሆን?) የአዲስ ዘመንና የዛሬዪቱ ኢትዮጵያ ጋዜጣ አዘጋጆችና ዓምደኞችም እንዲሁ አዳዲስ ቃላትን በመፍጠር የአማርኛ ቋንቋን ለማዳበር ያደረጉት ጥረት በጊዜ መርዘም የሚረሳ አይደለም፡፡
ከደርግ ውድቀት በኋላ የግል ጋዜጦች እንደ አሸን ፈሉ፡፡ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ደግሞ 24 ሰዓት የሚሰራጩ ኤፍ.ኤም ሬዲዮና ቴሌቪዥን ጣቢያዎች በመበራከታቸውና ብዙው የአየር ሰዓት በቀጥታ ስርጭት የሚሸፈን በመሆኑ የቋንቋ ጉዳይ ትኩረት የሚሰጠው አልሆነም፡፡ መዝገበ ቃላትን አገላብጦ፣ ከግእዝና ከሌሎች ቋንቋዎች ቃላትን ተውሶ ወይም አዳቅሎ መጠቀም የሚታሰብ አልሆነም፡፡ ጋዜጦችም ሆኑ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ጣቢያዎች በጉራማይሌ ቋንቋ መቅረባቸው ፋሽን የሆነ ይመስላል፡፡ የእንግሊዝኛ ቃል ሳዮሰነቅር የሚያቀርብ ጋዜጠኛ ብርቅ ሆኗል፡፡ የስፖርት ጋዜጦች ሳይቀሩ ቀደም ሲል አቻ የአማርኛ ቃል የተቀመጠላቸውን ቃላት ትተው የእንግሊዝኛውን ቃል በአማርኛ (ሣባ) ፊደል ሲጽፉ ይስተዋላል፡፡ የባሰውና ኀዘናችንን መሪር የሚያደርገው ነገር የአማርኛ (ሣባ) ፊደሎችን አጣርተው የማያውቁ “ጋዜጠኞች” ማየታችን ነው፡፡
የአርታኢ (ኤዲተር) አለመኖር ሌላው የጋዜጠኛነት ችግር ነው የሚል እምነት አለኝ፡፡ ጋዜጠኛ ያገኘውን መረጃ ሁሉ ጽፎ አያትምም፡፡ መረጃ ሁሉ በሬዲዮ ሞገድ አሊያም በቴሌቪዥን ስርጭት ለህዝብ አይቀርብም፡፡ ጋዜጠኛ መረጃው በህብረተሰብ መልካም አኗኗርና ስነ ልቦና ላይ የሚያደርሰውን ተጽእኖ ጭምር ማጤንና መወሰን ይጠበቅበታል፡፡ ከጋዜጠኛው ግምት ውጪ የሆነውን ደግሞ አርታኢ ያርቀዋል፡፡ በእንግሊዝኛው “Editor”በአማርኛ “አርታኢነት” የሙያ ዘርፍ ነው፡፡ አርታኢ “ሳንሱር አድራጊ” አይደለም፡፡ አንድ ዜና ወይም ፕሮግራም ለህዝብ ከመድረሱ በፊት በአርታኢ መታየትና መመዘን፣ መገምገም፣ መታረምና መስተካከል እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡ የአርታኢነትን ሥራ አስቸጋሪ የሚያደርገው በቴሌቪዥንና በሬዲዮ በሚቀርብ የቀጥታ ስርጭት ወቅት ነው፡፡ ለቀጥታ ስርጭት ደግሞ ልምድ፣ አቅምና አስተማማኝ ችሎታ ያለው ጋዜጠኛ በመመደብ ችግሩን መቅረፍ የሚቻልበት መንገድ አለ፡፡ በደርግ ጊዜ ከአብዮት አደባባይ የቀጥታ ስርጭት በሚተላለፍበት ወቅት ያን ስራ ለመስራት የሚመደቡ ውስን አንጋፋ ጋዜጠኞች ብቻ ነበሩ፡፡ ዛሬ ዛሬ አማተር ጋዜጠኞች ጭምር በቀጥታ ስርጭት ተመድበው “የት ልግባ” የሚያሰኙ አሳፋሪ ቃላት የምንሰማበት ሁኔታ ነው ያለው፡፡
ጋዜጠኛነትን ከሙያ ብቃት ጋር አያይዘን እንመልከት፡፡ በኔ እምነት ጋዜጠኛነት ከዩኒቨርስቲ በመመረቅና ዲግሪ በመጫን ብቻ የምንቀዳጀው ሙያ አይደለም፡፡ ይህንን የምልበት ዋነኛ ምክንያት፤ ብዙዎች ጋዜጠኛነትን በዝንባሌያቸው መርጠው የተማሩት ሳይሆን ዩንቨርስቲዎች በሚያደርጉት ምደባ ተምረው የተመረቁ በመሆኑ ነው፡፡ በርግጥ የዩነንቨርስቲ ትምህርት የጋዜጠኛነትን “ቴክኒካዊ እውቀት” ያጎናጽፋል፡፡ በዩንቨርስቲ ትምህርት የተገኘ “ቴክኒካዊ እውቀት” ተፈጥሯዊ ችሎታና ዝንባሌ ካልታከለበት ቅርጽ እንጂ ይዘቱ “ቢከፍቱት ተልባ” ከመሆን የዘለለ ትርጉም የለውም፡፡ በዝንባሌና በተፈጥሮ ስጦታ የታጀበ ጋዜጠኛነት በተለይ ከቋንቋ አጠቃቀም ጋር ተያይዘው የሚከሰቱ ችግሮችን ያስወግዳል ብየ አስባለሁ፡፡
ጋዜጠኛነትን ከህዝብ ክብር አንጻር መመልከትም ይቻላል፡፡ እኔ በምከተለው በእስልምና ሃይማኖት በቀን 5 ጊዜ ሶላት መስገድ ግዴታ ነው፡፡ ሶላት ለመስገድ የቆመ ሰው“በዓይኑ የማያየው ፈጣሪው ፊት” እንደቆመ መቁጠር እንዳለበት ያስተምራሉ የሃይማኖት አባቶች፡፡ እናም ፈጣሪ ፊት ከመቆሙ በፊት ታጥቦ፣ ንፁህ ሆኖ፣ ንፁህ ለብሶ፣ ልቡንም መንፈሱንም ንፁህ አድርጎ ለስግደት መቆም ግዴታ ነው፡፡ አንድ ጋዜጠኛም የማያያቸውና የማያውቃቸው ግን ደግሞ የሚያከብራቸውና መረጃ በማቅረብ የሚያገለግላቸው “አድማጭ፣ ተመልካችና አንባቢዎች” አሉት፡፡ የአንድ ጋዜጠኛ አለቆች እነዚህ “አድማጭ፣ ተመልካችና አንባቢዎች” ናቸው፡፡ አንዳንድ ጋዜጠኞች ከአድማጭ፣ ተመልካችና አንባቢዎች በታች ያሉ አገልጋዮች መሆናቸውን ረስተው በታሪክ አጋጣሚ ያገኙትን ማይክሮፎን ሲጨብጡ ራሳቸውን ከህዝብ በላይ ኮፍሰው፣ አዋቂና ሊቅ መስለው መታየት የእለት ተእለት ገጠመኛችን ከሆነ ዋል አደር ብሏል፡፡ ይህ ዓይነቱ ዝናን መሸከም አለመቻል፣ መታበይና መኮፈስ ደግሞ እንደ ሙያ የጋዜጠኛነትን ግብዓተ መሬት ከመፈጸም የተለየ ሆኖ አይታየኝም፡፡
ለሙያው ክብር የቆመ ጠንካራ የሙያ ማህበር አለመኖር ለጋዜጠኛነት ሙያ ችግር ውስጥ መዘፈቅ ዓይነተኛ ምክንያት ነው፡፡ የየትኛውም ሙያ ማህበር መሰረታዊ ዓላማ ሁለት ናቸው ብየ አስባለሁ፡፡ አንደኛ፡- የአባላቱን መብትና ጥቅም ማስከበር፤ ሁለተኛ፡- የሙያውን ክብርና ደረጃ ማስጠበቅ፡፡ የሙያ ክብር የሚራከሰው በውጫዊ ኃይሎች ብቻ ሳይሆን በራሱ በሙያው ባለቤቶች ጭምር መሆኑ እርግጥ ነው፡፡ ስለሆነም ጠንካራ የሙያ ማህበራት የስነ ምግባር ህግጋትን፣ መርሆዎችን፣ እሴቶችንና መመዘኛ ደረጃዎችን በማስቀመጥ፤ በነዚህ መስፈርቶች በመለካት ራሱን በራሱ እያረመ የመሄድን አቅጣጫ መከተል ይጠበቅበታል፡፡ በኛ ሀገር ይህንን የሚያደርግ፣ በአግባቡ የተደራጀ ጠንካራ የጋዜጠኞች ማህበር “አለ” የሚል እምነት የለኝም፡፡ ጋዜጠኞች ራሳቸው ተከፋፍለው የተደራጁበት ሁኔታ ስላለ በስልጠናና በልምድ ልውውጥ ሙያቸውን ማሳደግና የተከበረ ሙያ ማድረግ አልቻሉም፡፡ የሁሉም ጋዜጠኞች መሰረታዊ ጥያቄ “የፕሬስ ነፃነት” ነው፡፡ ታዲያ…“የሴት ጋዜጠኞች ማህበር፣ የስፖርት ጋዜጠኞች ማህበር፣ የመንግስት ጋዜጠኞች ማህበር፣ የነፃ ጋዜጠኞች ማህበር…” እያሉ መደራጀቱ ፋይዳው ምንድነው? የሚለው ጥያቄ በአግባቡ መፈተሽ አለበት፡፡ ራሳቸውን አንድ ያላደረጉ ጋዜጠኞች ህዝብን በማስተማር ያወቀ፣ መልካም ስነ ምግባርን የተላበሰና የሰለጠነ ማህበረሰብን መፍጠር እንዴት ይችላሉ?
አሁን በእኛ ሀገር ያሉት የጋዜጠኛ ማህበራት ትኩረት “ለጋዜጠኛው መብት ብቻ” መሆኑ ሌላው ጉድለት መስሎ ይታየኛል፡፡ ፓርላማ በነበርኩበት ወቅት ልምድ ለመቅሰም ወደ እንግሊዝ ሀገር ሄደን ነበር፡፡ እዚያ ከጎበኘናቸው ተቋማት አንዱ “የፕሬስ ቅሬታ ሰሚ ኮሚሽን” (Press Compliant Commission) ነበር፡፡ በተደረገልን ገለጻ መሰረት፤ ይህ ኮሚሽን የተቋቋመው በሀገሪቱ ባሉ ዋና ዋና አሳታሚዎችና ጋዜጠኞች ነበር፡፡ (በአሁኑ ወቅት “Independent Press Standards Organisation” ተብሎ መሰየሙን ከመረጃ ቋት ካገኘሁት መረጃ ተገንዝቤያለሁ) የዚህ ኮሚሽን ዋና ተግባር በሀገሪቱ የሚታተሙ ጋዜጦችና መጽሄቶች በዜጎች ላይ ስም ማጥፋትና የመሳሰሉትን ጉዳት ሲያደርሱ ሰዎች በሚያቀርቡት ቅሬታ መሰረት አጣርቶ ውሳኔ ማሳለፍ ነው፡፡ የዚህ ተቋም ዓመታዊ በጀት የሚመደበው ከመንግስት ሳይሆን ከአሳታሚዎችና ከጋዜጠኞች ከሚደረግ ዓመታዊ መዋጮ ሲሆን የሚቆጣጠረውም እነዚህኑ በገንዘብ የሚደጉሙትን አካላት ነው፡፡ ራስን በራስ ማረም ማለት እንዲህ ያለ አሰራርን መፍጠር ነው!
ዛሬ ዛሬ “ጋዜጠኛነት” አላፊ አግዳሚው ሁሉ የሚገባበት ተራ ሙያ መሆኑ ይስተዋላል፡፡ ይህ ሁኔታ ያስገረመው ደራሲና ጋዜጠኛ ቴዎድሮስ ተ/አረጋይ በፌስቡክ ገጹ ላይ “ማንይሆንዘንድሮቃለመጠይቅማድረግንየማይደፍር? መነጋገርስለሚመስልይሆንቃለመጠይቅማድረግየተደፈረው? ለምንሰዎችተነስተውአይዘፍኑም? ለምንሠዓሊነትንአይደፍሩትም? ለምንብዙሙያዎችን "አልችለውም" ብለውቃለመጠይቅማድረግሲሆንይቀላቸዋል? ምናልባትየእኛጋዜጠኛየምንባለውድክመትይሆንሙያውንያስደፈረው? እኛስሙያውንባናከብርእንዴትሰዎችራሳቸውንአያከብሩም? ለምንድነውሁሉምነገርምትትትትት-ትያለብን?” በማለት ጽፏል፡፡ እውነቱን ነው! ሙያው ረክሷል፣ ክብረ-ቢስ ሆኗል፡፡ የሙያው ዳር ድንበር በግልጽ ተለይቶ ባለመታወቁ በአሁኑወቅትበጋዜጠኛእናበአስተዋዋቂ፣በጋዜጠኛእናበዲጄ፣በጋዜጠኛእናበስብሰባአወያይ፣በጋዜጠኛእናበጥያቄናመልስአቅራቢ፣… መካከልያለውልዩነትበግልጽተለይቶሊታወቅአልቻለም፡፡
ለዚህሁሉመደበላለቅናለጋዜጠኛነትሙያመዝቀጥተጠያቂዎቹእውነተኛዎቹ፣የሙያውባለቤትየሆኑት፣ጋዜጠኞችራሳቸውናቸው፡፡የራሳቸውሙያትቢያላይወድቆማንምሲጫወትበትእያዩዝምብለውበሌላማህበረሰባዊህፀፅላይመዝመት፤በራሳቸውዓይንውስጥያለንግንድትተውበሌሎችላይያለንጉድፍለመጥረግደፋቀናከማለትየዘለለትርጉምየለውም፡፡ ለዚህ ነው የጽሁፌን ርእስ እባካችሁ “ጋዜጠኞችሙያችሁንለማስከበርበራሳችሁላይዝመቱ” ያልኩት፡፡
ሙያዊ ስነምግባር በሌላቸው ጋዜጠኞች የተወላገደ ዘገባ ምክንያት በርካታ ሰዎች ተጣልተዋል፡፡ ብዙ ትዳር ሳንካ ገጥሞታል፡፡ ብዙዎች ሞተዋል፣ ተሰደዋል፣ ታስረዋል፡፡ የንግድ ድርጅቶች ከስረው ተዘግተዋል ወይም ያለ አግባብ አትርፈዋል፡፡ ይህ ሁሉ እንዳለ ሆኖ በዚሁ መሀል ፍሬ ያላቸው አድማጭ፣ ተመልካችና አንባቢዎችን አክባሪ፣ የሙያቸውን መርህና ስነ ምግባር ጠብቀው ተግተው የሚሰሩ ክብርና ሞገስ ሊቸራቸው የሚገቡ ጋዜጠኞች መኖራቸው ሊካድ የማይገባው ሀቅ ነው፡፡ የነዚህ ጋዜጠኞች ችግር ሙያቸው እየተራከሰ መሆኑን አይተው እንዳላዩ፣ ሰምተው እንዳልሰሙ፣ አንብበው እንዳላነበቡ ሆነው ማለፋቸው ነው፡፡
የዚህ ጽሑፍ አቅራቢ ከተማሪነቴ ጊዜ ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ በጋዜጣ ላይ ስጽፍ፣ በሬዲዮ መጣጥፎችን ሳቀርብና ስሳተፍ ኖሬያለሁ፡፡ (ግን ጸሐፊ እንጂ ጋዜጠኛ አይደለሁም!) ከዚያ ጊዜ ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ ብዙውን ጊዜየን የማሳልፈው ከጋዜጠኞች፣ ከስነ-ጽሑፍ ባለሙያዎችና ከደራሲ ጓደኞቼና ወዳጆቼ ጋር ነው፡፡ በዚህ ዘርፍ ያፈራኋቸው ጓደኞቼ በርካታ ናቸው፡፡ ከእነዚህ ጓደኞቼና ወዳጆቼ ብዙ ነገር ተምሬያለሁ፡፡ ከጋዜጠኛ ጓደኞቼ ጋር ብዙ ጊዜ በማሳለፌና በዚህ ሙያ ዘርፍ የተጻፉ መጽሐፍትን እንዳነብ እድል በማግኜቴ ስለ ጋዜጠኛነት ጥሩ ግንዛቤ አለኝ፡፡ የማዘጋጃቸውን ጽሁፎችም (አቅም በፈቀደ መጠን) ሚዛን በጠበቀ መልክ እንዳቀርብ ይኸው ግንዛቤየና የወዳጆቼ እገዛ ረድቶኛል ብዬ አስባለሁ፡፡ እናም እኔ የማውቃትን አካፍያለሁ፡፡ የሙያው ባለቤቶች የሆናችሁ “ጋዜጠኞች” በስፋትና በጥልቀት ትወያዩበት ዘንድ ክብሪቷን ጭሬያለሁ፡፡
ጸሐፊውን በኢሜይል አድራሻው፡ This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it. ማግኘት ይቻላል፡፡

Read 8064 times