Tuesday, 07 April 2020 21:22

‹‹አስከፊውን ጊዜ ለማለፍ ሁሉም ሃላፊነቱን መወጣት አለበት›› (ወ/ሪት ሳምራዊት ፍቅሩ፤ የራይድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(1 Vote)

ራይድን የሚያስተዳድረው ሀይብሪድ ዲዛይንስ ፒኤልሲ፣ የኮቪድ 19 (ኮሮና ቫይረስ) ወረርሽኝን ለመከላከል በሚደረገው ጥረት የበኩሉን ጥረት እያደረገ ነው፡፡ በበጀት ደረጃም 4.2 ሚ ብር በጀት መድቦ በስሩ ላሉ 15 ሺህ አሽከርካሪዎች፣ ለላዳ ሹፌሮች፣ ለትራፊክ ፖሊሶችና ለፖሊሶችም የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ማስክ፣ የእጅ ማፅጃ ሳኒታይዘርና የግንዛቤ ማስጨበጫ ፍላየር በማድረግ ስድስት ቀን በፈጀ ዘመቻ ስናከፋፍል ቆይተናል፡፡ ትራፊክ ፖሊሶችንና ፖሊሶችን በምንሰጠው ድጋፍ ስር ያካተትነው፣ ያው ከማህበረሰቡ ጋር በስፋት ስለሚገናኙ ይበልጥ ተጋላጭ ናቸው ብለን በማሰብ ነው፡፡ ከአፍና አፍንጫ መሸፈኛውና ከሳኒታይዘሩ በተጨማሪም በሰጠናቸው በራሪ ወረቀት ላይ ከኮሮና ቫይረስ ራስንና ሌሎችን እንዴት መከላከል እንደሚቻል፣ አንድ ሰው ምልክቱ ከታየበት ራሱን ማግለል እንደሚገባው፣ ምልክቱ የታየበትን ሰው ለሚመለከተው አካል እንዴት መጠቆም እንዳለበት፣ እጅን ቶሎ ቶሎ ስለ መታጠብና በአጠቃላይ ስለ ኮሮና ቫይረስ ግንዛቤ ሊያስጨብጣቸው የሚችል ነው፡፡ ይህንን ሥራ ለመስራት በመጀመሪያ 2. ሚ. ብር ነበር የመደብነው፤ ነገር ግን ስላልበቃን ወደ 4.2 ሚሊዮን ብር ከፍ አደረግን፡፡ አጠቃላይ ስራውን ስንጨርስ ግን 5.ሚ ብር አውጥተናል፡፡
የራይድን የቢሮ ሰራተኞች ወደ ውጭ አውጥተን ነው፡፡ ሲሰሩ የነበሩት። በበጎ ፈቃደኝነት 47 ያህል ጋዜጠኞችም ከእኛ ጋር በመሆን ለአሽከርካሪዎች የምንሰጠውን የመከላከያ መሳሪያ በማከፋፈል አግዘውናል፡፡ እንደ ራይድም የራሳችንን ኮሚቴ አቋቁመናል:: ኮሚቴው ዋና ስራው የራይድ ኮርፖሬት ደንበኞች ድጋፍ መስጠት ፈልገው በየቤትኛው ቻናል እንስጥ እያሉ ያሉ ስለሆነ ከጋዜጠኞቹ ጋር በመተባበር፤ ከራይድ ደንበኞች የሚለገሰውን ቁሳቁስም ሆነ ብር በመሰብሰብ መንግሥት ተቋቁማ ድጋፍ አሰባሳቢ ብሄራዊ ኮሚቴ ለማስረከብ ስምምነት ላይ ደርሰናል፡፡
ይህን ከማድረግ በተጨማሪ በመንግሥት በኩል ለሚደረገው ጥሪም የምንችለውን ያህል ምላሽ እንሰጣለን:: ራይድ ለሰራተኞቹም ቢሆን ራሳቸውን እንዲጠብቁ ለጥንቃቄ የሚሆናቸውን ቁሳቁስ በማቅረብና ግንዛቤ በማስጨበጥ ከፍተኛ ጥንቃቄ እያደረግን ነው፡፡ ይህን አስቸጋሪ ወቅት በጽናት ለማለፍ ሁሉም የበኩሉን ድርሻ መወጣት አለበት ብለን እናምናለን፡፡
እኛ እንግዲህ በዚህ ረገድ ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ ከመጠበቅ ጀምሮ በወሎ ሰፈር መንገድና በሲኤምሲ መስመር ሰራተኞቻችንን በማሰማራት ለስድስት ቀን የዘለቀ የቁሳቁስ አቅርቦትና የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ በመስራት የበኩላችንን ስናደርግ ነበር፡፡ አሁንም እንደየአስፈላጊነቱ ባለው ቀዳዳ ሁሉ ትብብራችንን በማድረግ፣ ይህ ጊዜ እንዲያጥርና ወደ ቀደመ ሕይወታችን ተመልሰን ለማየት ድርሻችንን እየተወጣን ነው። ለራይድ አሽከርካሪዎች፣ ለላዳ ሾፌሮች፣ ለትራፊክ ፖሊሶችና ለፖሊሶች ከምንሰጠው በተጨማሪም፣ በግንባታ ስራ ላይ የተሰማሩ መጥተው ሲወስዱ አልከልንም ሁሉም በአቅሙ በሚችለው መልኩ ከተረባረበና ከሥራ፣ የመንግሥትን መልዕክትና ውሳኔ ተግባራዊ ካደረገ፣ ሃላፊነቱን ተወጥቷል ማለት ነው፡፡ በመተባበርና ሀላፊነታችንን በመወጣት ክፉውን ጊዜ እንደምንሻገር ጥርጥር የለኝም፡፡
 ይህንን ስናደርግ ፈጣሪም ያግዘናል:: ለአገሬና ለዓለም ሕዝብ መልካም ቀን እንዲመጣለት እመኛለሁ፡፡

Read 1506 times