Saturday, 07 July 2012 09:36

.አብዛኞቹን ግቦች መድረስ ይቻላል.....

Written by  ፀሐይ ተፈረደኝ ከኢሶግ
Rate this item
(0 votes)

በምእተ አመቱ የልማት ግብ መሰረት በኢትዮጵያ የእናቶች መጠን በመቀነስ ላይ ነው ወይንስ? ለሚለው ጥያቄ በእርግጥ የሚሞቱ እናቶች ቁጥር ለጊዜው ቀንሶ ባይገኝም ተያ ያዥ የሆኑ ሌሎች ግቦች ላይ ግን በውጭው አቆጣጠር እስከ 2015/ ድረስ መድረስ ይቻ ላል፡፡ በቀሪው ጊዜም የእናቶችን ሞት መጠን ለመቀነስ እና ግቡን ለማሳካት አስፈላጊው ጥረት ሁሉ ሊደረግ ይገባል፡፡ ..

ዶ/ር ይርጉ ገ/ሕይወት በአ.አ.ዩ ህክምና ፋክልቲ ረዳት ፕሮፌሰር የጽንስና ማህጸን ሕክምና እስፔሻሊስት እና የኢሶግ ፕሬዝዳንት

ከላይ ያስነበብናችሁ መረጃ መሰረት ያደረገው ከአንድ ሳምንት በፊት በአዲስ አበባ ተደርጎ የነበረውን የእናቶችን ሞት ምክንያት የማወቅ የስድስት ወር የስራ ልምድ ልውውጥ ስብሰባ ነው፡፡ በስብሰባው የተገኙት ተሳታፊዎች በአገራችን ከኢሶግ ጋር የሚሰሩ ዘጠኝ ሆስፒ ታሎችና አርባ አምስት ጤና ጣቢያዎችን ጨምሮ ከአፍሪካ እና ፕሮጀክቱን ከሚደግፈው አለም አቀፍ የጽንስና ማህጸን ሕክምና ባለሙያዎች ማህበር የተወከሉ ባለሙያዎች ነበሩ፡፡

የእናቶችን ሞት ምክንያት ለማወቅ ኢሶግ አብሮአቸው ከሚሰራባቸው ሆስፒታሎች አንዱ በአዲስ አበባ የሚገኘው ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ ነው፡፡ በዚያም ያለውን አሰራር በሚመለከት ዶ/ር ማለደ ቢራራ እና እና ዶ/ር ድልአየሁ በቀለ በሆስፒታሉ የጽንስና ማህጸን ሐኪሞች ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን በአጠቃላይ ስለእናቶች ሞት መቀነስ እና ተያያዥ ለሆኑ ጥያቄዎች መልስ የሰጡን ዶ/ር ይርጉ ገ/ሕይወት የኢሶግ ፕሬዝዳንት ናቸው፡፡

ዶ/ር ማለደ እንደሚገልጹት ..በሆስፒታሉ የእናቶችን ሞት ምንነት ለማወቅ በሚደረገው ክትትል ከሐኪሞች እና ነርሶች የተውጣጣ አንድ ኮሚ የተዋቀረ ሲሆን  እንደዚሁም የኮሌጁ ጥራት ቁጥጥር ኃላፊ እና የኮሌጁን ስራ አስኪያጅ ጨምሮ ኮሚው ወደ አስራ አምስት አባ ላት አሉት፡፡ በቅዱስ ጳውሎስ የእናቶችን ሞት ምክንያት ለማወቅ የሚሰራው ኮሚ በሶስት ሲኒየር የጽንስና ማህጸን ሐኪሞች በበላይነት እየተመራ እንዲሁም ሁለት ጠቅላላ ሐኪሞች ደግሞ መረጃውን በመሰብሰብ ስራው በመሰራት ላይ ነው፡፡

ምንም እንኩዋን ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ የሚገኘው በአዲስ አበባ ቢሆንም ታካሚዎቹ የሚመጡት ግን ከተለያዩ በአዲስ አበባ ዙሪያ ካሉ አካባቢዎች ጭምር ነው፡፡ ስለሆነም አሉ ዶ/ር ማለደ .. ስለሆነም በአብዛኛው ሶስቱ መዘግየቶች በመባል  የሚገለጹት ነገሮች  እናቶችን ሲጎዱ ይታያል፡፡ እነርሱም ...እናቶች...

ወደጤና ተቋም መሄድ እንደሚገባቸው አለማወቃቸው

ወደጤና ተቋም መሄድ እንዳለባቸው ቢያውቁም ለመሄድ አለመቻላቸው እና

¨ደጤና ተቋም ቢሄዱም ተገቢውን ሕክምና ማግኘት አለመቻላቸው... ናቸው፡፡

ስለዚህ በእነዚህ ምክንያቶች ጤናቸው የሚጎዳ ብሎም ለህልፈት የሚዳረጉ እናቶች ሁኔታ ያጋጥማል፡፡ በእርግጥ አሁን በኢትዮጵያ የጽንስና ማህጸን ሐኪሞች ማህበር ትብብር የተጀመ ረው ምክንያትን የማወቅ ስራ ከመጀመሩም በፊት እናቶች ለምን ከጉዳት ላይ እንደሚ ወድቁ የሚታወቅ ነገር ያለ ሲሆን ከዚህም በብዛት በወሊድ ጊዜ ከፍተኛ የሆነ የደም መፍሰስ እንዲ ሁም በእርግዝና ጊዜ የሚከሰት የደም ግፊት ፣ የኢንፌክሽን እና ሌሎች ሁኔታዎች እንደነበሩ ይታመናል፡፡ አሁን ግን  ለእናቶች ሞት ምክንያት ምንድናቸው የሚለውን ከመለየት አንጻር በሚሰራው ስራ ተጨባጭ በሆነ መልኩ ስንት እናቶች በምን ምክንያት እንደሚሞቱ ግልጽ የሆነ መረጃ እየተገኘ ሲሆን በየትኛው በኩል በከፍተኛ ሁኔታ መጎዳት እንደሚኖር በሚያ ሳየው መረጃ ዙሪያ በየወሩ ስብሰባ እየተደረገ ባለሙያው እናቶችን ለማዳን የሚያስችለው እር ምጃ ምን እንደሆነ መገመት የሚያስችለው አካሄድ ነው፡፡”

ዶ/ር ድልአየሁ በቀለ እንዳሉትም ..እናቶች ለሞት የሚዳረጉት በሶስት መዘግየቶች ነው ተብሎ ከላይ ከተጠቀሰው ውስጥ በተለይም እናቶች ወደጤና ተቋም መሄድ እንዳለባቸው አለማወቃቸውና ለመሄድ ቢያስቡም እድሉን አለማግኘታቸው ለጉዳታቸው ከፍተኛውን ቁጥር ይይዛል፡፡ በእርግጥ ወደጤና ተቋም ከደረሱም በሁዋላ አንዳንድ የጤና ተቋማት የተሟላ አገል ግሎት መስጠት ባለመቻላቸው ምክንያት እናቶቹ በወቅቱ ተገቢውን ሕክምና ስለማያገኙ የሚጎ ዱበት ሁኔታ ይኖራል፡፡ የጤና ተቋማቱ ታካሚዎችን ጊዜ ሳይፈጁ ወደሚቀጥለው የህክምና አገልግሎት ካለማስተላለፍ በተጨማሪም ከፍተኛ የህክምና ተቋማቱ በትክክል የሚላኩላቸውን ታካሚዎች ወይንም ወላዶች ተጠቃሚዎቹን ማስተናገድ ችለዋል ወይንስ? የሚለውም አጠያ ያቂ ነው፡፡ ስለዚህ በአሁን ወቅት በየሆስፒታሉ የተጀመረው አሰራር ሆስፒታሎቹ እንዲሁም የጤና ባለሙያዎቹ እራሳቸውንም እሚገመግሙበት እና ማስተካከል የሚገባውን ነገር ማየት የሚቻልበት በመሆኑ በጣም ጠቃሚ ነው፡፡..ብለዋል፡፡

ዶ/ር ማለደ የባለሙያዎችን የስራ ተነሳሽነትን በሚመለከት እንደገለጹት ..እናቶች በተለይም በገጠራማው ክፍል የሚኖሩት ወደጤና ተቋም መሄድ እንዳለባቸው አምነው ከዚያም በተቻለ መጠን ያላቸውን ቅሪት አንጠፍጥፈው ወደ ሆስፒታል ከደረሱ በሁዋላ የአገልግሎት አለማግኘት ማለትም ሶስተኛውን መዘግየት የሚፈጥረው በዋናነት የባለሙያው ተነሳሽነት አለመኖር ነው፡፡ የባለሙያ ተነሳሽነት ከብዙ ነገሮችጋር ይያያዛል፡፡ የስራ ጫና ፣የጤና ተቋሙ የመድሀኒትና የመሳሪያ አቅርቦት አለመሟላት፣ የቁጥጥር ማነስ ፣የእውቀትና የክህሎት  ማነስ እንዲሁም ተያያዥነት ያላቸው የጥቅማ ጥቅሞች ሁኔታ ሊፈጥረው ይችላል፡፡ ስለዚህ የባለሙ ያዎች የስራ ተነሳሽነት አንዱና ትልቁ የእናቶችን ጤናነት ለመጠበቅ የሚያስፈልግ ሲሆን ይህን ለማሟላት አስፈላጊው ጥረት ሁሉ መደረግ መቻል አለበት፡፡ የባለሙያዎችን ክህሎት ማሳደግ፣ የጤና ተቋሙን በተሟላ ሁኔታ ማደራጀት እንዲሁም ተገቢውን የስራ ክትትል ማድረግ...ወዘተ አስፈላጊ ነው፡፡..

Ê/ር ድልአየሁ በበኩላቸው ..አንዱ እናቶችን ሊጎዳ የሚችለው የተዛባ አሰራር የቅብብሎሽ ስርአቱ ያለመጠንከር ነው፡፡ ከጤና ተቋማት ወደሆስፒታሎች ለከፍተኛ ሕክምና የሚላኩትን ወላዶች በሚመለከት መደረግ የነበረበት አንዲት እናት ወደሆስፒታል በምትላክበት ወቅት ሆስፒታሉ ተጠይቆ አልጋ መኖሩ ተረጋግጦ ፣ሆስፒታሉም ይህችን እናት ለመቀበል ዝግጁ ሆኖ ሊሆን ሲገባው እናቶች ያለምንም መረጃ ቅብብል ስለሚላኩ ሲንገላቱ ይታያሉ፡፡ ይህ የቅብብሎሽ ችግር እንደ ሀገርም ትልቅ የማሻሻያ እርምጃን የሚፈልግ ነው፡፡ ሌላው ጤና ጣቢያ ዎች ወይንም ክሊኒኮች ለከፍተኛ ሕክምና እናትየውን ወደ ሆስፒታል መላክ ብቻ ሳይሆን የህመ ምዋን ምንነትና የህክምና ውጤቱን ማወቅ ስለሚገባቸው ግብረመልስ እንደሚያስፈልጋቸው የታ መነ ነው፡፡ ይህንን አሰራር በተመለከተ እስከአሁን ምንም የተዘረጋ መስመር የለም፡፡ ስለዚህ በቅ ዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ ዙሪያ ከሚገኙ ስምንት ጤና ጣቢያዎች ጋር በምንሰራው ስራ የግብረመልስ አሰራርን ለመጀመር በዝግጅት ላይ እንገኛለን፡፡ ነገር ግን ይህ በአገር አቀፍ ደረጃ ተግባራዊ እንዲሆን ከፍተኛ እንቅስቃሴን የሚጠይቅ ነው፡፡..

እንደ ዶ/ር ማለደ ..መንግስት በአሁኑ ወቅት በአዲስ አበባ ብቻ ከሰላሳ ያላነሱ የመ ንግ ስት ጤና ጣቢያዎችን ገንብቶአል፡፡ መውለድን በሚመለከት ከፍተኛ የህክምና ክትትል የማያ ስፈልገው እስከሆነ ድረስ በጤና ጣብያዎች እንዲሰሩ ይፈለጋል፡፡ ነገር ግን ወላዶች በአብዛኛው ምጥ ሲይዛቸው በቀጥታ የሚሄዱት ወደ ጤና ጣቢያ ሳይሆን ወደሆስፒታል ነው፡፡የዚህም ምክ ንያቱ በጤና ጣቢያ ያሉ የህክምና ባለሙያዎች በትክክል አያዋልዱም ወይንም በጤና ጣቢያ ƒክክለኛውን የህክምና አገልግሎት አናገኝም ከሚልና ሆስፒታል ውስጥ ዶክተሮች ስላሉ በእነሱ እጅ የመውለድ ፍላጎት ከመኖሩ የተነሳ ነው ፡፡ ነገር ግን ወሊድ የተለያዩ ችግሮች እስካልተ ከሰቱ ድረስ መፈጸም ያለበት በጤና ጣቢያ በአዋላጅ ነርሶች አማካኝነት ነው፡፡ ይህ በየትኛውም የአለም ክፍል ያለ አሰራር ነው፡፡ በእኛ አገር ግን ይህንን ብዙዎች ስለማይፈጽሙ እና በቀጥታ ለትንሹም ለትልቁም ወደሆስፒታል መምጣታቸው ጤና ጣቢያዎችን ያለመጠቀምና በአግባቡ ስራቸውን እንዳይሰሩ ከማድረጉም በላይ በሆስፒታሎች ውስጥ ከፍተኛ ክትትል እንዲደረግ ላቸው የሚያስፈልጋቸውን ታካሚዎችን ቦታ እና የሐኪሞችን ጊዜ በመሻማት ጉዳት እንዲደርስ ምክንያት ይሆናሉ፡፡ ይህ ችግር በመንግስት ከፍተኛ ትኩረት እያገኘ በመሆኑ ትክክለኛ የሆነ የጤና ጣብያዎች አጠቃቀም እንዲኖር መስመር እየተዘረጋ ነው፡፡  በአሁን ወቅት የቅብብሎሽ ስርአቱን ለማጠናከር እንዲያስችል እያንዳዳቸው አዲስ አበባ ውስጥ የሚገኙ ሆስፒታሎች በስራ ቸው አስር አስር ጤና ጣቢያዎች ጋር የስራ ግንኙነት እንዲፈጥሩና ክትትል እንዲያደርጉ የቅብ ብሎሽ ስርአቱም እንዲጠናከር የሚያስችል አሰራር በመዘርጋት ላይ ነው፡፡ ይህ በቀጣዮቹ ጥቂት ወራት ውስጥ እልባት አግኝቶ ወደተሻለ አሰራር ይገባል ብለን እናምናለን፡፡ ..

በስተመጨረሻ ዶ/ር ይርጉ ገ/ሕይወት የኢሶግ ፕሬዝዳንት የእናቶች ሞት መጠን መቀነስን በሚመለከት እንዳብራሩት .. ሞት መጠንን በሚመለከት አሁን ከምን ደረጃ ላይ ነው ያለው? የሚለውን በሚመለከት ያው ቁጥሩ ከፍተኛ ነው ማለት ብቻ ይበቃል፡፡ ነገር ግን መሰረታዊው ነገር ለውጥ ማምጣት አለብን የሚለውን መመልከትነው፡፡ የእናቶችን ሞት መጠን ሙሉ ለሙሉ ከዜሮ ማድረስ ይቻላል ማለት ሳይሆን በተቻለ መጠን ቁጥሩን መቀነስ አስፈላጊ ስለሆነ በትጋት መስራትን ይጠይቃል፡፡ ከምእተ አመቱ የልማት ግብ አንጻር ስንመለከተውም የልማት ግቡ ወደ ስምንት ነጥቦች ሲሆኑ አብዛኞቹን ማሳካት የሚቻልበት አንሄድ እየታየ ነው፡፡ የእናቶች ሞትን መቀነስ ላይ ግን ብዙ መሰራት አለበት፡፡ ያ ማለት ግን እስከጭርሱንም ውጤት የለም ማለት አይደለም፡፡ እንደ ተባበሩት መንግስታት ግምት በኢትዮጵያ የእናቶች ሞት መጠን እየወረደ ያለው ወደ 4.5 ከመቶ አካባቢ ሲሆን የምእተ አመቱን ግብ ለማሳካት ግን የሚጠበቅብን 5.5 ከመቶ ድረስ መውረድ ነው፡፡ ሌላው ነገር ለልማት ግቡ ከተቆረጠው ቀን በፊት የሚደረስባቸው ፣በተቆረጠው ቀን የሚደረስባቸው፣ ከዚያም በሁዋላ የሚደረስባቸው ይኖ ራሉ፡፡ ዋናው ነገር ለልማት ገቡ ከተያዘውም የጊዜ ገደብ በሁዋላ የተደረሰባቸውን ውጤቶች ይዞ መቀጠል መቻል ቁልፍ ነገር ነው፡፡ ስለዚህም ብዙ ነገሮች ማለትም...የቤተሰብ ምጣኔ አገ ልግሎት፣ የቅድመ ወሊድ አገልግሎት ፣የህክምና አገልግሎት ተደራሽነትን ስናይ ብዙ ነገሮች እየተሻሻሉ ነው፡፡ ነገር ግን ሞት የሚለው ነገር የብዙ ነገሮች ውጤት ስለሆነ በርትተን ከሰራን ካሰብነው እቅድ እንደርሳለን የሚል እምነት አለኝ.. ብለዋል ዶ/ር ይርጉ ገ/ሕይወት የጽንስና ማህጸን ሕክምና እስፔሻሊስት፣በአ.አ.ዩ ረዳት ፕሮፌሰርና የኢሶግ ፕሬዝዳንት፡፡

 

 

Read 2593 times Last modified on Saturday, 07 July 2012 12:26