Saturday, 21 March 2020 12:15

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ 30 አገራት የሚያደርገውን በረራ አቋረጠ

Written by  መታሰቢያ ካሳዬ
Rate this item
(1 Vote)

  የአመክሮ ጊዜያቸው የደረሰና ቀለል ያለ ክስ ያለባቸው እስረኞችም እንዲለቀቁ መወሰኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡
          የኢትዮጵያ አየር መንገድ  ወደ ሰላሳ የአለማችን አገራት የሚያደርጋቸውን በረራዎች ማቋረጡን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ አስታውቀዋል፡፡ አያይዘውም ከየትኛውም አገራት ወደኢትዮጵያ የሚገቡ መንገደኞች ለ14 ቀናት በለይቶ ማቆያ ውስጥ የመቆየት ግዴታ እንደተጣለባቸው ተናግረዋል፡፡ በዚህ ቆይታቸውም ገቢ መንገደኞቹ ወጪያቸውን ሙሉ በሙሉ ራሳቸው የሚሸፍኑ ይሆናልም ብለዋል፡፡በማረሚያ ቤቶች ቫይረስ ከገባ ለቁጥጥር አስቸጋሪ ሁኔታ የሚፈጠር በመሆኑ ህጻናትን የያዙ የአመክሮ ጊዜያቸው የደረሰና ቀለል ያለ ክስ ያለባቸው እስረኞች እንዲለቀቁ መወሰኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡ የእምነት ተቋማትም እንደየአምልኳቸው ሁኔታ ለቫይረሱ ስርጭት ምቹ ሊሆን ስለሚችሉ የየራሳቸውን ውሳኔዎች እንዲያሳልፉም ከስምምነት ላይ መደረሱን ጠ/ሚኒስትሩ ጨምረው ገልፀዋል፡፡


Read 915 times