Saturday, 14 March 2020 13:05

“ሳይቃጠል በቅጠል” የኪነ-ጠበብ ምሽት ማክሰኞ ይካሄዳል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(2 votes)

    በሰምና ወርቅ ኢንተርቴይመንት በየወሩ የሚካሄደው 27ኛው ምሽት “ሳይቃጠል በቅጠል” በሚል ርዕስ ማክሰኞ መጋቢት 8 ቀን 2012 ዓ.ም ከቀኑ 11፡00 ጀምሮ በኢትዮጵያ ሆቴል ይካሄዳል፡፡
በዕለቱም ግጥም፣ ወግ፣ ዲስኩርና ለሎችም መሰናዶዎች የሚቀርቡ ሲሆን፣ ፕሮፌሰር አህመድ ዘካሪያ፣ ሙሃዘ ጥበባት ዳንኤል ክብረት፣ አትሌት ኮሎኔል ደራርቱ ቱሉ፣ ገጣሚያኑ በቃሉ ሙሉ፣ ኤሊያስ ሽታሁን፣ ረዳት ፕሮፌሰር ነብዩ ባዬ፣ ኮሜዲየን ሰመረ ባሪያው፣ አርቲስት ሚሊዮን ብርሃኔ (ጩባው) ወጣት ዳግም ተሾመና ዳዊት ፀጋዬ ሥራዎቻቸውን ያቀርባሉ ተብሏል የመግቢያ ዋጋው መቶ (100) ብር ሲሆን የመግቢያ ትኬቱ በኢትዮጵያ ሆቴል፣ በጃፋር፣ በዮናስ፣ በአይናለም መጽሐፍት መደብሮችና ኦሮሞ ባህል ማዕከል አጠገብ በሚገኘው አቡጊዳ ካፌ እንደሚገኝም ለማወቅ ተችሏል፡፡

Read 21472 times