Saturday, 07 March 2020 12:51

የኢትዮጵያ መንትዮች ማህበር ሊመሰረት ነው

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

  በመንትዮቹ የሕክምና ዶክተሮች ዶ/ር ቃል ኪዳን ጌታሁንና ዶ/ር ኢየሩሳሌም ጌታሁን መስራችነትና አስተባባሪነት የኢትዮጵያ መንትዮች ማህበር ሊመሰረት እንደሆነ ተገለፀ፡፡ የቲዊንስ መካከለኛ ክሊኒክ መስራችና ባለቤት የሆኑት መንትዮቹ ዶክተር እህትማማቾች በአብዛኛው በበጎ አድራጎትሥራ ላይ በመሳተፍ የሚታወቁ ሲሆኑ በኢትዮጵያና በመላው ዓለም የሚገኙ መንትዮችን በማሰባሰብ ከነገ በስቲያ እሁድ የካቲት 29 ቀን 2012 ዓ.ም ከረፋዱ 3፡00
ጀምሮ በማግኖሊያ ሆቴል ማህበሩን በይፋ ለመመስረት ቀጠሮ መያዛቸው ተሰምቷል፡፡ እህትማማቾቹ መንትያ አባላትን ለማሰባሰብ እስካሁን ባደረጉት ጥረት
በኢትዮጵያና በመላው ዓለም 156 ያህል በተለያየ የሙያ ዘርፍ የተሰማሩ አባላትን ማግኘታቸውንና ማሰባሰባቸውን ገልፀዋል፡፡


Read 11351 times