Saturday, 07 March 2020 12:38

‹‹ዘገር›› የተሰኘ የግጥም መድበል ለንባብ በቃ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(2 votes)

        ከጎንደር ዩኒቨርሲቲ በኢንቫይሮሜንታል ኸልዝ እንዲሁም ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በኢኮኖሚክስ የተመረቀውና የጥራት ማረጋገጥ ባለሙያ በሆነው ሙሉቀን ሰብስቤ የተጻፉ ግጥሞችን የያዘው ‹‹ዘገር›› የግጥም መድበል ለንባብ የበቃ ሲሆን ከትላንት በስቲያ ሀሙስ ሰሜን ማዘጋጃ በሚገኘው ሳሬም
ኢንተርናሽናል ሆቴል ታዋቂ ገጣሚያን፣ ተዋንያን፣ ድምፃዊያንና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በድምቀት ተመርቋል፡፡ 90 በመቶ ግጥሞቹ አጫጭርና ጥልቅ ሃሳብ ያዘሉ ሲሆኑ በአገራችን ፖለቲካዊና በማህበራዊ ጉዳዮች ላይ የሚያጠነጥኑ የሚሞግቱ ናቸው፡፡ የገጣሚና ጋዜጠኛ በረከት በላይነህ አድናቂ መሆኑን የሚገልፀው ገጣሚ ሙሉቀን፣ ከ2 ሺህ በላይ ግጥሞችን ጽፎ ያስቀመጠ ሲሆን ከ6 ወር በኋላ ‹‹ዘመን›› የተሰኘ ከዚያም ‹‹ዘረር›› የተሰኙ የግጥም መድበሎችን እንደሚያሳትም ጠቁሟል፡፡

Read 11516 times