Saturday, 29 February 2020 11:38

“ኢትዮጵያዊነት በዝክረ አድዋ” የኪነ ጥበብ ምሽት ሰኞ ይካሄዳል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

  በአብርሃም ግዛው ኢንተርቴይመንትና የፕሬስ ስራዎች ድርጅት የሚዘጋጀውና ሙሉ ትኩረቱን በአድዋ ድል ላይ ያደረገው ‹‹ኢትዮጵያዊነት በዝክረ አድዋ›› የተሰኘ የኪነ ጥበብ ምሽት ሰኞ የካቲት 23 ቀን 2012 ዓ.ም. ከቀኑ 11፡00 ጀምሮ በኢትዮጵያ ብሄራዊ ቴአትር ይካሄዳል፡፡
በዕለቱ አድዋ አድዋ የሚሸቱ ግጥሞች፣ ወጎች፣ መነባንቦች፣ ዲስኩርና የኮሜዲ ስራዎች ለታዳሚ የሚቀርቡ ሲሆን በዕለቱም ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና፣ ጥበበ የማነ ብርሃን (ዶ/ር) አረጋዊ በርሄ (ዶ/ር) አህመዲን ጀበል፣ አርቲስት ይገረም ደጀኔ (አስቴር)፣ ፀሐፊ ተውኔት አያልነህ ሙላቱ፣ ገጣሚና ሰዓሊ በቀለ መኮንን፣ አርቲስት ሸዊት ከበደ፣ አርቲስት ሰለሞን ቦጋለ፣ ኮሜዲያን አዝመራው መለሰ፣ እስጢፋኖስ በፍቃዱ፣ ደራሲና ዳይሬክተር ሄኖክ አየለና ሌሎችም ሥራዎቻቸውን ያቀርባሉ፡፡

Read 11499 times