Saturday, 30 June 2012 12:39

“ዳጉ” በድረገፅ ቢዝነስ ዳይሬክተሪ አዘጋጀ

Written by  መልካሙ ተክሌ (melkamutekele@gmail.com)
Rate this item
(0 votes)

ዳጉ ማስታወቂያና ፕሮሞሽን ድርጅቶች አገልግሎታቸውን እያስተዋወቁ የሚገበያዩበት የድረገፅ ቢዝነስ ዳይሬክተሪ ያዘጋጀ ሲሆን ይኸው ዳይሬክተሪ በሚቀጥለው ሳምንት በራዲሰን ብሉ ሆቴል በሚደረግ የራት ግብዣ ይመረቃል፡፡ከ50 ሺህ በላይ የኩባንያዎች ዳታ የያዘው ዳይሬክተሪ፤ ክፍት የሥራ ቦታ ማስታወቂያ የዜናና የጨረታ ገፆችም አሉት፡፡ Daguethiopia.com በሚል ድረገፅ የሚገኘው ዳይሬክተሪ በሁለት ሚሊዮን ብር ወጪ እንደተዘጋጀና ከሰላሳ በላይ የመጀመሪያ ዲግሪ እና ከዚያ በላይ ያላቸው ባለሙያዎች እንደሚሰሩበት የድረገፁ ባለቤቶች ተናግረዋል፡፡በስድስት ወር 800 ብር፣ በዘጠኝ ወር 1100 ብር፣ በዓመት 1400 ብር የማስታወቂያ ዋጋ የሚጠይቀው ድረገፅ፤ ክፍት የሥራ ቦታ ማስታወቂያዎችን የሚያስተናግደው በነፃ ነው፡፡ ድረገፁን በሁለት ወር ብቻ 29 ሺህ ያህል ሰዎች እንደጐበኙት ባለቤቶቹ ይናገራሉ፡፡

 

 

Read 2018 times Last modified on Saturday, 30 June 2012 12:42