Print this page
Saturday, 29 February 2020 10:57

በጋምቤላ በተፈጠረ ግጭት የ12 ሰዎች ሕይወት አለፈ

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(0 votes)

  በጋምቤላ ክልል አዌር ዞን በተቀሰቀሰ ግጭት 12 ሰዎች ሕይወታቸው ሲያልፍ 7 ሺህ ያህል መፈናቀላቸውን ከ4 መቶ ቤቶች በላይ መቃጠላቸውን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡
ግጭቱ ቀደም ባለው ሳምንት የተፈጠረ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን ለግጭቱ መነሻ የሆነውም አንድ የአካባቢው አስተዳዳሪ ባልታወቁ ሀይሎች መገደል ነው ተብሏል፡፡
የባለሥልጣኑን ግድያ ተከትሎ በኑዌር ዞን በተቀሰቀሰው ግጭት 12 ሰዎች በተለያየ መንገድ ሲገደሉ 21 መቁሰላቸው እና ከ7 ሺህ በላይ መፈናቀላቸውን እንዲሁም ከ4 መቶ በላይ ቤቶች ተቃጥለው አበወራዎች ቤት አልባ መሆናቸውን የረድኤት ድርጅቶች መረጃ ያመለክታል፡፡
የጋምቤላ ክልላዊ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን በበኩሉ በአካባቢው የተከሰተውን ግጭት መቆጣጠር መቻሉንና በጥቃቱ ተሳትፈዋል ተብለው የተጠረጠሩ 6 ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተጣራ መሆኑን አስታውቋል፡፡
በግጭቱ የተፈናቀሉና የተጎዱትን ለመደገፍም ክልሉ 3 ሚሊዮን ብር መድቦ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን አስታወቋል፡፡  


Read 1159 times