Saturday, 30 June 2012 12:35

በዕውቀቱ ኢትዮጵያ የሯጮች ብቻ ሳይሆን የገጣሚዎችም አገር ናት አለ

Written by  ግሩም ሠይፉ
Rate this item
(0 votes)

ከ30ኛው ኦሎምፒያድ ጋር ተያይዞ በሚከናወነው ዓለም አቀፍ የለንደን ፌስቲቫል ላይ የሚሳተፈው ኢትዮጵያዊ ገጣሚ በዕውቀቱ ስዩም አገራችን የሯጮች ብቻ ሳይሆን የገጣሚዎችም አገር ናት ሲል ተናገረ፡፡ ገጣሚ በዕውቀቱ ስዩም ከ204 የኦሎምፒክ ተሳታፊ አገራት የተውጣጡ ገጣሚዎች በሚሳተፉበትና የለንደን ፌስቲቫል ዝግጅት አካል በሆነው “ዘ ፖዬተሪ ፓረንስስ” ላይ ለመካፈል በለንደን ከተማ ይገኛል፡፡ “ዘ ፖዬተሪ ፓረንሰስ” ፕሮግራሙን ባለፈው ማክሰኞ የጀመረ ሲሆን ከተለያዩ አገራት የተጋበዙ ገጣሚዎች በየራሳቸው ቋንቋ የጻፏቸው 100ሺ ግጥሞች  በለንደን በምትገኘው ሳውዝ ባንክ በሄሊኮፕተር ከሰማይ ላይ ተበትነዋል፡፡

ከኦሎምፒያኑ ጋር ተያይዞ በተዘጋጀው ዓለም አቀፍ የግጥም ጉባዔ ላይ የተገኙ ገጣሚዎች  ብዛት በታሪክ የመጀመሪያው የተባለ ሲሆን ለአንድ ሳምንት የሚቆየው ዝግጅቱ ገጣሚያን በቋንቋቸው ግጥማቸውን የሚያቀርቡበት፤ ዎርክሾፖችና የተለያዩ ውይይቶች የሚያካሂዱበት እንደሆነ ታውቋል፡፡ በ”ፖዬተሪ ፓረንስስ” ድረገፅ ቃለ ምልልስ ያደረገው በዕውቀቱ ስዩም፤ በፌስቲቫሉ መሳተፉ የመበረታታት ምንጭ እንደሚሆነው ገልፆ፣ የተለያዩ ቋንቋዎችና ባህሎች ካሏቸው ገጣሚዎች ጋር መገናኘት በአንድ ሳምንት ዓለምን እንደማሰስ ነው ብሏል፡፡

 

 

 

Read 1080 times Last modified on Saturday, 30 June 2012 12:39