Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 30 June 2012 12:33

ሼፍ ማርክስ አዲስ መፅሃፍ አሳተመ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

ትውልደ ኢትዮጵያዊ የሆነው ታዋቂው የአሜሪካ ሼፍ ማርከስ ሳሙኤልሰን “የስ ሼፍ” የተሰኘ በምግብ ዝግጅት ሙያውና በህይወቱ ዙሪያ የሚያጠነጥን አዲስ መፅሃፍ ለገበያ አበቃ፡፡ ገና በልጅነቱ በስዊዲናዊ አሳዳጊዎቹ በጉዲፈቻ ከኢትዮጵያ የሄደው ማርከስ፤ ለከፍተኛ ዝናና ዕውቅና ያበቃውን የምግብ ማበስል ሙያ የተማረው ከስዊድናዊ አያቱ እንደሆነ በመፅሃፉ ላይ ገልጿል፡፡ ማርከስ እጅግ ጠቃሚ መፅሃፍ ማዘጋጀቱን የጠቆመው ኒውዮርክ ታይምስ፤ ታዋቂ የአሜሪካ ቴሌቪዥን ፕሮግራሞች መፅሃፉ ከወጣ በኋላ በክብር እንግድነት እየጋበዙት እንደሆነ አመልክቷል፡፡ “የስ ሼፍ” በምስል የተደገፈና 319 ገፆች ያሉት መፅሃፍ ሲሆን በአማዞን ድረገፅ ዋጋው 27 ዶላር ነው፡፡

ለአሜሪካው ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ የመጀመርያ የእራት ግብዣ በዋይት ሃውስ ማዘጋጀቱን እንደ ታሪካዊ ስኬት የሚቆጥረው ሼፍ ማርከስ፤  በኒውዮርክ ማሃንታን ውስጥ በከፈተው ሬድ ሩስተር የተባለ ሬስቶራንቱ ውስጥ የሃርለም ነዋሪዎችን ማገልገሉ እንደሚያስደስተው ተናግሯል፡፡ “ቶፕ ሼፍ ማስተርስ” በተባለ የሼፎች ውድድር ያሸነፈው ማርከስ በአሜሪካ የታወቀ የሬስቶራንት ባለሙያ፣ የሼፎች አሰልጣኝና ደራሲ ነው፡፡

 

 

Read 2167 times Last modified on Saturday, 30 June 2012 12:34