በዘንባባ ማስታወቂያ ድርጅት በየወሩ የሚሰናዳው የዲስኩርና የኪነ-ጥበብ ምሽት የዚህ ወር መሰናዶ ‹‹የኛ ትውልድ›› በሚል ርዕስ ሰኞ የካቲት 16 ቀን 2012 ዓ.ም ከቀኑ 11፡30 ጀምሮ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ይካሄዳል፡፡ በዕለቱ ዳኛቸው አሰፋ (ዶ/ር)፣ ወዳጄነህ መሐረነ (ዶ/ር)፣ ወረታው በዛብህ (ዶ/ር)፣ ዓለማየሁ ረዳ (ዶ/ር)፣ መልአከ ብርሃናት አባ ጴጥሮስ ሰለሞን (ዶ/ር) መምህር የሻው ተሰማ (የኮተቤው)፣ ገጣሚ በላይ በቀለ ወያ፣ አርክቴክትና
ደራሲ ሚካኤል ሽፈራው፣ ሙዚቀኛ ታምሩ ንጉሴና ጋዜጠኛ ወግደረስ ጤናው ስራዎቻቸውን የሚያቀርቡ ሲሆን፣ የመግቢያ ዋጋው 100 ብር መሆኑንና ትኬቱ በዮናስ፣ በጃፋርና ዓይናለም መጽሐፍት መደብሮችና ስድስት ኪሎ በሚገኘው ምስካዬ ህ ዙናን መ ድኃኒዓለም ገ ዳም ት ምህርት ቤት እንደሚገኝ አዘጋጆቹ ገልፀዋል፡፡
Saturday, 22 February 2020 10:52
‹‹የኛ ትውልድ›› የዲስኩርና የኪነ-ጥበብ ምሽት ሰኞ ይካሄዳል
Written by ናፍቆት ዮሴፍ
Published in
ኪነ-ጥበባዊ ዜና