Saturday, 22 February 2020 10:47

‹‹የሚዲያና የሕዝብ ግንኙነት አሰራር›› መጽሐፍ ለንባብ በቃ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(4 votes)

 በሚዲያ ምንነት፣ በሚዲያ ህጐች፣ በሬዲዮና በቴሌቪዥን ፕሮግራሞች አዘገጃጀት፣ በሀተታ ጽሑፍ፣ በጉዞ ማስታወሻ አጻጻፍ፣ በጋዜጠኝነት ዘርፎች፣ በህዝብ ግንኙነት አሰራርና በተያያዥ ጉዳዮች ላይ ጥልቅ ትንታኔና ግንዛቤን የሚያስጨብጠው ‹‹የሚዲያና የሕዝብ ግንኙነት አሰራር›› መጽሐፍ ለንባብ በቃ፡፡
በጋዜጠኝነትና ተግባቦት መምህሩ መኮንን ተካ አያሌው የተጻፈው ይሄው መጽሐፍ በተለይም በተለያየ የጋዜጠኝነት ዘርፍ ማለትም በስፖርት፣ በጥብቅና፣ በሰላም፣ በሕዝባዊ፣ በልማታዊ እና በምርመራ ጋዜጠኝነትና የሕዝብ ግንኙነት ስራ ላይ ለተሰማሩ እንዲሁም በዘርፉ እውቀትና ግንዛቤ ለሚፈልጉም ሆነ ለጥናትና ምርምር በግብአትነት የሚያገለግል ነው፡፡ በስምንት ምዕራፎች ተከፋፍሎ በ300 ገጽ የተቀነበበው መጽሐፉ፣ በ153 ብር ለገበያ ቀርቧል፡፡

Read 1656 times