Print this page
Saturday, 22 February 2020 09:56

“ዋጋ ሜዲካል ሰርቪስ” ቪአይፒ የአይን ሕክምና ክፍል ከፈተ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

   የዛሬ 8 ዓመት ገደማ የተመሰረተውና ደረጃውን የጠበቀ የአይን ሕክምና በመስጠት የሚታወቀው ዋጋ ሜዲካል ሰርቪስ፤ የአገራችንን ገጽታ የሚገነባና ልዩ አገልግሎት የሚሰጥ ቪአይፒ የአይን ሕክምና ክፍል አስመረቀ፡፡  
ድርጅቱ ባለፈው ቅዳሜ ምሽት ላይ በይፋ ባስመረቀው የቪአይፒ አይን ሕክምና ማዕከሉ “የተለያዩ አገራት አምባሳደሮች፣ ከፍተኛ የጤና ባለሙያዎች፣ የድርጅቱ ከፍተኛ የጤና አመራሮችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡
ተቋሙ በተጨማሪም ‹‹ዋጋ የአይን ማዕከል››፣ ‹‹ዋጋ ኦፕቲካል የመነጽር ክፍል›› እና ‹‹ዋጋ የሕክምና ዕቃዎች ጥገና ክፍል››ን በሥሩ ያስተዳድራል፡፡ ማዕከሉ ከአገር ውስጥ ታካሚዎች በተጨማሪ ከኤርትራ፣ ጅቡቲ፣ ኬንያ፣ ሱዳን ሶማሊያና ሌሎች አገራት ለሚመጡ ታካሚዎች ደረጃውን የጠበቀ የሕክምና አገልግሎት በመስጠት ላይ እንደሚገኝ ሀላፊዎቹ ተናግረዋል፡፡
የዛሬ ሳምንት የተመረቀው ቪአይፒ የማቆያና የምርመራ ክፍልም ወረፋ መጠበቅ ለማይፈልጉ፣ ብቻቸውን መታከም ለሚሹ፣ ለአምባሳደሮች፣ ለዲፕሎማቶችና በአጠቃላይ አገልግሎቱን ለሚፈልጉ ሁሉ ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት የተቋቋመ ልዩ ክፍል ሲሆን ይህ ልዩ ክፍል በአገር ኢኮኖሚ፣ በአገር ገጽታ ግንባታና ተጨማሪ የስራ ዕድል በመፍጠር አስተዋጽኦ ይኖረዋል ተብሏል:: ዋጋ ሜዲካል ሰርቪስ በአይን ሕክምና ላይ ምርምር በመስራትና የሕክምና ደረጃውን በማላቅ ሀላፊነቱን እየተወጣ ሲሆን በቅርቡም በግል የሕክምና ተቋማት አሰሪዎች ማህበር በሚሊኒየም አዳራሽ ለሶስት ቀናት በተካሄደው ነፃ የሕክምና አገልግሎትና የጤና ኤግዚቢሽን ላይ በሰጠው ነፃ የህክምና አገልግሎት፣ በአይን ሕክምና ዘርፍ ልዩ ተሸላሚ እንደነበር ይታወሳል::   

Read 2805 times