Saturday, 15 February 2020 12:25

‹‹ዋጋችን ስንት ነው?›› የኪነ ጥበብ ምሽት ሰኞ ይካሄዳል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

 በሰምና ወርቅ ኢንተርቴይንመንት በየወሩ የሚካሄው 26ኛው የኪነ ጥበብ ምሽት ‹‹ዋጋችን ስንት ነው?›› በሚል ርዕስ ሰኞ የካቲት 9 ቀን
2012 ዓ.ም ከቀኑ 11፡00 ጀምሮ በብሄራዊ ቴአትር ይካሄዳል፡፡ በዕለቱ ወዳጄነህ ማሀረነ (ዶ/ር)፣ ዶ/ር ብርሃኔ ረዳኢ፣ ኡስታዝ አቡበከር አህመድ፣ የፍልስፍና
መምህር ዮናስ ዘውዴ፣ አርቲስት ሽመልስ አበራ፣ ደራሲና ገጣሚ ኤፍሬም ስዩም፣ በልጅነቱ ግዕዝን፣ ፊዚክስን፣ እና የህዋ ሳይንስን የተረዳው ታዳጊ የእውቀት ብላቴና ቅዱስ ዕንቁ ስራቸውን የሚያቀርቡ ሲሆን አዝመራው ሙሉ ሰው ኮሜዲ፣ ድምፃዊ ታረቀኝ ሙሉ ሽለላ እና አበባው አስራት ሙዚቃ እንደሚያቀርቡም ታውቋል፡፡ የመግቢያ ዋጋው 100 ብር ሲሆን ትኬቱን በጃፋር፣ በዮናስና በዓይናለም መጻሕፍት መደብሮችና ስታዲየም በሚገኘው አቡጊዳ ካፊቴሪያ ማግኘት እንደሚቻል ታውቋል፡፡

Read 10763 times