Saturday, 15 February 2020 10:59

Menstrual Hygiene--በወር አበባ ወቅት ጤናን መጠበቅ

Written by  ፀሐይ ተፈረደኝ ከኢሶግ
Rate this item
(0 votes)

    በእንግሊዝኛው Menstrual hygiene በአማርኛው የወር አበባን ጤናማ በሆነ መንገድ ማስተ ናገድ በአለም አቀፍ ደረጃ ቀን ተወስኖለት እ.ኤ.አ May 28- አመታዊ ቀን ሆኖ  በመገናኛ ብዙሀንም ሆነ በተለያዩ እለቱ ሊታሰብ በሚገባቸው ቦታዎች ሁሉ እንዲታሰብ የተወሰነ ሲሆን በ2018/አመታዊ ቀንም #No More Limits የሚል መሪ ቃል እንደነበረው የWorld Bank Group መረጃዎች ያስረዳሉ:: (#No-more limits) ማለትም ምንም ክልከላ ወይንም ገደብ ሳይጣልባት አንዲት ልጃገረድ ወይንም ሴት በወር አበባዋ ወቅት የራስዋን ጤና ክብርዋን በጠበቀ፤ መገለልን ባስወገደ፤የምትገለገልበት ቁሳቁስ በተሟላ መልኩ አግኝታ ጤንነ ትዋን እንድትጠብቅ እና በአስፈላጊው ወቅትና ጊዜ ሁሉ እንደልብዋ መንቀሳቀስ መቻል ያለባት መሆኑን መረጃ የሚሰጥ ነው፡፡ በ2019/አመታዊ ቀንም የተሻለ ውጤት እየተመዘገበ መሆኑን መረጃው አክሎ ገልጾአል፡፡
አንዳንድ ቦታዎች የተለያዩ ነገሮችን እንደነውር በመቁ ጠር ለውይይት ወይንም ለሚነሳ ጥያቄ መልስ ለመስጠትም ሆነ መጠየቅ የሚገባው ነገር እንዳይጠየቅ በሩ ዝግ ስለሚሆን በተለ ይም በት ምህርት ላይ ላሉ ልጃገረዶች አስቸጋሪ ሁኔታን የሚፈጥ ርበት አጋጣሚ መኖሩን ሀገራ ችንን ጨምሮ በተለያዩ ሀገራት የወጡ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ ሴት ልጆች በትምህርት ላይ እያሉ የወር አበባቸው በሚከሰት ጊዜ በትክክል ሊጠቀሙባቸው የሚያስችሉዋቸው ነገሮች ማለትም ውሀና መጸዳጃ ቤትን ጨምሮ የሚጠቀሙባቸው ንጹህ የወር አበባ መቀበያ ፓዶች የማግኘት እድላቸው በጤናማ መንገድ መስተናገዳቸውንና አለመስተናገዳቸውን ይገልጻል፡፡ እነዚህ ነገሮች ካልተሙዋሉላቸው የስነልቡናና ሌሎች የጤና መጉዋደል ችግሮች ሊገጥሙዋ ቸው እንደሚችል እሙን ነው፡፡
አንዲት ሴት የወር አበባዋን በምታይበት ወቅት በምን መንገድ የእራስዋን ጤንነት በጠበቀ መልኩ ማስተናገድ ትችላለች?
በወር ውስጥ ለተወሰኑ ቀናት የሚደርሱ ቀናትን  ሰላማዊና ጤናማ በሆነ መንገድ ምንም ሳይሸማቀቁ ወይንም ክብርን እና በራስ መተማመንን በጠበቀ ሁኔታ ለማለፍ የሚከተሉትን መንገዶች መከተል ይጠቅማል፡፡
ለወር አበባ መቀበያ እንዲሆን የሚጠቀሙበትን ፓድ ወይንም ሞዴስ ከ4-6 ሰአት በሚሆን ጊዜ መቀየር ያስፈልጋል፡፡
ሰውነትን በደንብ መታጠብ ይገባል፡፡
በመታጠብ ጊዜ ሳሙናን ወይንም ሌሎች ተመሳሳይ ነገሮችን መጠቀም አያስፈልግም፡፡
የተጠቀሙበትን ሞዴስ በትክክለኛ መንገድ ማስወገድ ይገባል፡፡
ይህንን ከላይ የተጠቀሱትን መንገዶች በተመሳሳይ መልኩ በየወሩ መፈጸም ይገባል፡፡
የወር አበባን ጤናማ በሆነ መንገድ መቆጣጠር በአለም አቀፍ ደረጃ ለአንዲት ልጃገረድ ወይንም ሴት የስነተዋልዶ ጤና ችግር እንዳይደርስ ለማድረግ ዋነኛ ከሚባሉት መካከል ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የወር አበባቸውን በተገቢ መንገድ መቆጣጠር መቻላቸው በትምህርታቸው እንዳ ይዘናጉ፤ በስራ ቦታቸው ግዳጃቸውን እንዲወጡ ፤ሌሎች ሊገኙ የሚችሉባቸው ቦታዎች ቢኖሩም  ምንም ሳይሸማቀቁ በኩራት እና በክብር ተገቢ ተፎካካሪ እንዲሆኑ ብቃት ያላቸው መሆኑን እንዲያምኑ ያስችላቸዋል፡፡
በአለም አቀፍ ደረጃ ቢያንስ 500/ሚሊዮን የሚሆኑ ሴቶችና ልጃገረዶች የወር አበባቸውን ጤናማ በሆነ መንገድ ለማስተናገድ ሊያገኙ የሚገባቸውን የተለያዩ ቁሳቁሶች የማግኘት እድል የላቸውም፡፡ ለዚህም በአንዳንድ ሀገራት WASH (water, sanitation and hygiene) የተባለው ግብረሰናይ ድርጅት በትምህርት ቤቶች እንዲሁም በስራ ቦታ ወይንም ሰዎች በተለያዩ ምክንያ ቶች በሚገኙባቸው ስፍራዎች እና የጤና ተቋማት ከወር አበባ ጋር በተያያዘ በሴቶች ላይ ሊደርስ የሚችለውን ችግር ለመፍታት ጥረት እንደሚያደርጉ የገለጸው የተባበሩት መንግስታት ሕጻናት አድን ድርጅት UNICEF ነው፡፡  
በችግር መልክ ከተጠቀሱት በተለይም ሴት ተማሪዎችን በሚመለከት በተለይ የሚገቡበትና
በሩ በሚገባ ሊዘጋ የሚችል መጸዳጃ ቤት አለመኖር፤ የተጠቀሙበትን ፓድ የሚያስወግዱበት
ቦታ ወይንም ቆሻሻ ማስወገጃ አለመኖር፤ እጃቸውን በሳሙናና በውሀ የሚታጠቡበት ቦታ አለመኖር፤ ጤንነታቸውን በጠበቀ፤ ክብራቸውን በማይነካ መልኩ በወር አበባቸው ወቅት ሊጠቀሙባቸው የሚገቡ ነገር ግን ብዙ ቦታ (ትምህርት ቤት) የማያገኙበት ሁኔታ ይስተዋላል:: የዚህ ውጤትም ተማሪዎቹ በየወሩ ለተወሰኑ ቀናት ትምህርታቸውን እንዲያቋርጡና በተጨ ማሪም ከፍተኛ የሆነ የኢኮኖሚ ወጪ የሚያስከትል ሕክምናን የሚጋብዝ የስተዋልዶ ጤና ችግር ስለሚያስከትል በራሳቸው ቤተሰብም ይሁን በአገራቸው ላይ ጉዳት ያስከትላል፡፡
ከላይ ከተጠቀሰው በተጨማሪም የወር አበባ ጉዳይ በብዙ ሀገራት ልማድና ባህል እንዲሁም እምነት ሴት ልጅ የወር አበባ በምታይበት ወቅት ያልተሟላች ወይንም የቆሸሸች ተደርጋ ስለምትወሰድ እራሳቸውን ዝቅ እንዲያደርጉና ከብዙ ነገሮች እራሳቸውን እንዲያገልሉ ስለሚ ገደዱ ተፈጥሮን እንዲያማርሩ ይሆናሉ፡፡ ይህ እንደነውር የመቆጠርና የመገለል ልማድ ወይንም ባህል ደግሞ በጉዳዩ ላይ ዝርዝር መረጃ እንዳይጠየቅ ወይንም ሴትዋ ማወቅ ያለባትን ነገር ጠይቃ እንዳትረዳ እና በምን መንገድ ጤንነትዋን በጠበቀ መልኩ እራስዋን እንድትጠብቅ የሚያስችላትን መረጃ ወይንም ትምህርት እንዳታገኝ ምክንያት ይሆናል ይላል በቅርቡ በ---World Bank Group (WBG) የወጣው ጥናት፡፡
በUNICEF እገዛ በተለያዩ ሀገራት የተለያዩ የጤና ጉዳዮችን የሚሰራው WASH (Water sanitation and hygiene) የተባለው ፕሮጀክት በናይጄርያ፤ በባንግላዴሽ፤ በፓናማ፤ ጋና …ወዘተ በመሳሰሉት ሀገራት የጽዳት መገልገያዎችን እና ስለጤንነት በየትምህርት ቤቶቹ ለሴት ተማሪዎች ትምህርት ይሰጣል፡፡ በኢትዮጵያም ይህ WASH የተሰኘው ፕሮጀክት ተማሪዎች በወር አበባ ጊዜ ጤንነታቸውን በጠበቀ መልኩ የሚጸዳዱበትን ሁኔታ በትምህርት ቤቶች በተሻሻለ መንገድ እንዲዘጋጅ ለማድረግ የተቻለውን ያህል መስራቱን ዩኒሴፍ ገልጾአል:: ይህ በመንግስትና በፕሮጀክቱ መካከል ያለው በስምምነት የመስራት ውጤት በብሔራዊ ደረጃ ከፍ እንዲልም መንገድ የሚከፍት መሆኑን በተጨማሪ ፕሮጀክቱ ገልጾአል፡፡
ሴት ልጆች ወይንም ሌሎች ሴቶች በወር አበባቸው ወቅት የሚያስፈልጋቸው የተለያየ እርዳታ አለ ይላል መረጃው፡፡
ማህበራዊ እርዳታ፡- ብዙ ሴቶችና ልጃገረዶች በወር አበባቸው ወቅት የሚደርስባቸው የተዛባ ግንዛቤና እምነት እነርሱን ወደእፍረት ወይንም መሸማቀቅ እና ማፈር እንደሚወስዳቸው እሙን ነው፡፡ ስለዚህ ሴት ተማሪዎችም ሆኑ ሌሎች ሴቶች በዚህ ወቅት ምንም አይነት መሸማቀቅ ሳይደርስባቸው በነጻነት የሚንቀሳቀሱበትና ጤናቸውን የሚጠብቁበት መንገድ መመቻቸት አለበት፡፡ ይህ ትብብር በወንዶችንም በኩል እንዲፈጸም ያስፈልጋል፡፡ መገለልን ለማስወገድ አቻ ጉዋደኞች፤ አስተማሪዎች፤ ወላጆች፤ ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች፤ የእምነት መሪዎች፤ የአገር ሽማግሌዎች …ወዘተ ሊሳተፉበት ይገባል፡፡  
እውቀትና ችሎታን ማዳበር፡- ብዙ ሴት ልጆች ፍርሀትና ጭንቀት ስለሚኖራቸው ስለ ወር አበባ ሁኔታ ጥያቄ ማቅረብ አይፈልጉም፡፡ መረሳት የሌለበት ነገር ግን ማንኛዋም ሴት ስለ ወሲብ አካላትና የስነተዋልዶ ጤና አስቀድማ ትምህርት ማግኘት እንደሚገባት ነው፡፡ የወር አበባዋ በሚመጣበት ወቅትም በምን መንገድ በንጽህና ተፈጥሮን ማስተናገድ እንደሚገባት ከትምህርት ቤት እና ከወላጆች በሚገባ ልታውቅ ይገባል፡፡
የመገልገያ ቁሳቁሶች፤- ልጃገረዶችና ሴቶች በሚማሩበት ወይንም በስራ ቦታ፤ በቤታቸው እንዲሁም ህብረተሰቡ በሚገለገልባቸው ተቋማት፤ የጤና ተቋማት …ወዘተ ጭምር የሚገ ለገሉባቸው ውሀ፤ የመጸዳጃ ቤት፤እና የተጠቀሙበትን ፓድ የሚያስወግዱበት ቦታ ሊያገኙ የማይችሉባቸው አጋጣሚዎች ብዙ ናቸው፡፡ ስለዚህ ከላይ የተጠቀሱት ነገሮች እንዲሟሉ አስፈላጊው ትኩረት መሰጠት አለበት፡፡
ባጠቃላይም ሴቶች በተለይም በትምህርት ላይ የሚገኙ ሴት ልጆች ጤናቸውን በጠበቀ መንገድ የወር አበባቸውን መቆጣጠር የሚያስች ሉዋቸውን ማናቸውንም አቅርቦቶች እንዲሟሉላቸው እና መገለል እንዳይደርስባቸው ማድረግ የሁሉም ድርሻ መሆኑን ዩኒሴፍ እና የአለም ባንክ ባወጡት መረጃ አስነብበዋል፡፡    


Read 13665 times