Print this page
Monday, 03 February 2020 11:39

“የሻሼ እንግሊዝኛ” - ከምክር ቤት እስከ ቀበሌ ጽ/ቤት

Written by  ሲሳይ አሰፌ ተሰማ
Rate this item
(0 votes)

  እርስዎ በዕለት ተዕለት ግንኙነትዎ ከተለያዩ ሰዎች ጋር በተለያየ ሁኔታ ሊገናኙ ይችላሉ፡፡ ግንኙነቶቹ ከአንዳንዶች ጋር በጽሁፍ፣ ከአንዳንዶች ጋር በስልክ፣ ከአንዳንዶች ጋር ደግሞ ገጽ ለገጽ ሊሆን ይችላል፡፡ የሚያገኟቸው ሰዎች፣ የቤተሰብ አባላት፣ ዘመዶች፣ ጓደኞች ወይም የሥራ ባልደረቦች ሊሆኑም ይችላሉ:: እንደገና ከእነዚህ ሰዎች መካከልም ፊደል ያልቆጠረ፣ በመጠኑ የተማረ፣ በጣም የተማረና እርስዎንም ሊያስተምር የሚችል ጭምር ሊኖር ይችላል፡፡ አሁን ጥያቄው  ከእነዚህ ሰዎች ጋር የሚገናኙበት የቋንቋና የሀሳብ ምጥቀት ደረጃ፣ በምን ዓይነት አቀራረብ  ሊሆን ይገባል? የሚል ነው፡፡
አንድን ሀሳብ ለአንድ ሰውም ሆነ ለቡድን ወይም ለአጠቃላይ ህብረተሰብ የምንገልጽበት የቋንቋ አጠቃቀም ሆነ የሀሳብ አቀራረብ ደረጃ፣ ለተነሳንበት ዓላማ መሳካት ወይም አለመሳካት ወሳኝ ነው፡፡ ይህም ግባችንን ለመምታት በአግባቡ ስንጠቀምበት የተሳካ ይሆናል፤ በአግባቡ ሳንጠቀምበት እንዲሁ አፍ እንዳመጣ ስንወረውረው ግን ልፋታችን ሁሉ ከንቱ ሆኖ ይቀራል፡፡ በዚህ ጽሁፍ ማተኮር ያስፈለገውም በዚህ ጉዳይ ላይ ነው፡፡
አልፎ አልፎ አንዳንድ ሰዎች፣ እንግሊዝኛ ቋንቋን ከሀገርኛ ቋንቋ ጋር ዝም ብሎ እየደባለቁ መናገር፣ በመልዕክቱ ላይ ያለውን ተጽዕኖ አስመልክተው በተለያዩ መጽሔቶችና ጋዜጦች ላይ አስተያየት ሲሰጡ ተመልክተናል፡፡ ይሁን እንጂ እየባሰበት እንጂ እየተሻሻለ ሲሄድ አይታይም፡፡ በእርግጥ ቋንቋ ይወለዳል፤ ያድጋል፤ ይወራረሳል፤ ይሞታል፡፡ ነገር ግን አጠቃቀሙን ካላወቅንበት ገና ከመወለዱ ዕድገቱን  በቅጡ ሳይጀምር በአጠቃቀም ጉድለት ሊቀጭ ይችላል፡፡ ይህ የአጠቃቀም ጉድለት በተለያዩ ምክንያቶች ሊከሰት ይችላል:: እነዚህም፡-
በዕውቀት ማነስ ወይም በጥራዝ ነጠቅነት፤
በመድረክ ሞቅታ ምክንያት የተናጋሪዎቹ ስሜት ያተኮረው በሚያስተላልፉት መልዕክት ላይ እንጂ በቋንቋው አጠቃቀም ላይ ባለመሆኑ፤
በግድየለሽነት “ከእኛ ወዲያ ዐዋቂ ለአሳር” በሚል ጀብደኝነት የሚሉ ምክንያቶች ናቸው ብዬ አስባለሁ፡፡
በእርግጥ በዓለም አቀፍ መግባቢያነት የምንጠቀምበት የእንግሊዝኛ ቋንቋ፤ በሀገራችን በሥርዓተ ትምህርቱ ውስጥ ተካትቶ የሚሰጥ ከመሆኑ በተጨማሪ ለተለያዩ ተግባራት ከምንጠቀምባቸው የዕውቀት ምንጮቻችን ውስጥ እጅግ በርካታ መጻሕፍት በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተጻፉ በመሆናቸው፣ ቴክኖሎጂው ይህንን ቋንቋ በብዛት ስለሚጠቀም ተጽዕኖ እንደሚያሳድር ይታመናል፡፡ ቋንቋ የሚወራረስ በመሆኑ አንዳንድ ቃላትን አንድም ከፈጠራ ጋር በተያያዘ፡- ለምሳሌ፡- ራዲዮ፣ ቴሌቪዥን፣ ቪዲዮ የመሳሰሉት ፤ወይም አንዳንድ የእንግሊዝኛ ቃላት ሃሳቦችን በስፋት በተለያየ አገባብና አማራጮች ለመጠቀም በሚያስችል መልኩ ለመግለጽ አመቺ በመሆናቸው፤ ለምሳሌ፡- ኮሙዩኒኬሽን፣ ቢዝነስ፣ ፌዴሬሽን፣ ፌዴራሊዝም፣ ኢንቨስትመንት፣ ፕራይቬታይዜሽን -- ወዘተ.የመሳሰሉ ቃላትን አዘውትረን ልንጠቀምባቸው እንችላለን፡፡ ከእንዲህ ዓይነት ተመሳሳይ ነገሮች በዘለለ መልኩ ግን ስሙንም፤ ተውላጠ ስሙንም፣ ግሱንም፣ ቅጽሉንም፣ ተውሳከ ግሱንም፤ መስተዋድድና መስተጻምሩንም ሁሉ ዝም ብለን ባገኘንበት ቦታ የምንደነቅር ከሆነ፣ መልዕክታችንን ለማን ማድረስ እንደፈለግን እንኳንስ ሌላው አድማጭና ተመልካች፡ እኛው ራሳችንም መልሶ  ግራ ያጋባናል፡፡
እንዲህ ዓይነት ነገሮች በተለይ በስብሰባና በብዙኃን መገናኛ ሲተላለፉ እጅግ በጣም አሳፋሪና ውሉ የጠፋ ልቃቂት ይሆናሉ:: በዚህ ዓይነት መንገድ ከተላለፉ በርካታ መልዕክቶች ውስጥ የሚከተሉትን ብቻ እንደ ምሳሌ  ብንወስድ፣ ምን ያህል ግራ የሚያጋባና መልዕክታችን ለኢትዮጵያዊ ነው? ወይስ ለአሜሪካዊና ለእንግሊዛዊ? ወይስ ዝም ብለን ለግድግዳውና ለድምጽ ማጉሊያው ነው? ብለን ራሳችንን እንድንጠይቅ  ያስገድደናል፡፡ እዚህ ላይ አቀራረባችን ልክ ለአንድ የምናውቀው የቅርብ ሰው የምንነግረውን ያህል ቀለል ያለ መሆን እንዳለበት ባምንም፣ ትኩረቴ ግን መልዕክታችንን በምናስተላልፍበት የቋንቋ አጠቃቀማችን ላይ መሆኑን በአጽንኦት መግለጽ እወዳለሁ፡፡ ከዚህ በታች የተጠቀሱት ምሳሌዎች የተሰባሰቡት ከሀገሪቱ መሪዎች ጀምሮ በተለያየ እርከን የሚገኙ ከፍተኛ የመንግስት ባለሥልጣናት፡ የዩኒቨርስቲ ምሁራን፡ በተለያየ መስክ ከከፍተኛ እስከ ዝቅተኛ ደረጃ የሚገኙ ባለሙያዎች ወዘተ. ከተናገሯቸው መካከል የተወሰኑት ብቻ ናቸው፡፡ የእንግሊዝኛዉን ቃል ልክ ሰዎቹ እንደተጠቀሙበት እንዳለ የወሰድኩት የበለጠ እንዲለይና፣ ግድየለሽነቱ እየበዛ ከሄደ፣ ወደፊትም በጽሕፈትም ቢሆን፣ እንደዚህ መጻፉ የማይቀር አደጋ ስለሆነ ነው፡፡
እነዚህ እጅግ በጣም ጥቂቶቹ ብቻ ናቸው:: ይህንን በስብሰባ ስናዳምጥ ወይም በብዙኃን መገናኛ ስንከታተል፣ መልዕክቱ ለማን እንደሚተላለፍ ግራ ያጋባል፡፡ ከ85% ያላነሰ አርሶ አደር ባለባት ሀገር፣ ብዙ በትምህርት የገፋ ዜጋ በሌለባት ሀገር፣ በዚህ መልክ የሚተላለፍ ሀሳብ (ሀሳቡ እጅግ አስፈላጊ ቢሆንም እንኳን) እጅግ ውስን ለሆኑ ቡድኖች ካልሆነ በስተቀር መልዕክቱ የሚደርሰው ህብረተሰብ በምን መልክ ሊረዳው ይችላል? የዚህ ዓይነት አቀራረብ በማን ህሊና ውስጥ ገብቶ፣ የሰውን ስሜት ሊኮረኩርና ከጐኑ ሊያሰልፍ ይችላል? ማደናበርና ማደናገር ካልሆነ በስተቀር በእውነት እንነጋገር ከተባለ፣ በመንግስትና በግል ተቋማት የሚዘጋጁት መድረኮች ሁሉ መልዕክታቸውን በታሰበው ልክ ሳያስተላልፉና የልብ ሳያደርሱ፣ በአብዛኛው ባክነው ይቀራሉ ቢባል ማጋነን አይሆንም፡፡
በነገራችን ላይ አማርኛን ለምሳሌ አነሳሁ እንጂ በሌሎችም የሀገራችን ቋንቋዎች ተመሳሳይ ችግር እንደሚኖር አልጠራጠርም፡፡ በዚህ ረገድ ጋዜጠኞቻችን ትልቅ ኃላፊነት አለባቸው፡፡ ከሙያ መገለጫና በፅንሰ ሀሳብ ከገለፅናቸው የተወሰኑ መሰል  አጠቃቀሞች በስተቀር ዝም ብሎ የቋንቋ ከተፋ ሲሰራ፣ በመጀመሪያ ደረጃ የብዙኃን መገናኛ፣ ተጋባዥ የሆኑትን እንግዶች ጋዜጠኞቻችን ሊመክሯቸው (በቅድሚያ ሊያሳስቧቸዉ) ካስፈለገም በዘዴ ቃላቱን እንዲያስተካክሉ ማድረግ ይችላሉ፡፡ በግልጽና በድፍረት ከተነጋገርን፣ አንዳንድ ጋዜጠኞች፣ በተለይም በኤፍ.ኤም ራዲዮ ጣቢያዎች የምናዳምጣቸው (በይበልጥም በሙዚቃና በስፖርት ፕሮግራሞች) አቀራረቦች፤ በእውነት ባለሙያ የሚያስተላልፋቸው፡ የብዙኃን መገናኛ ሕግና ሥርዓትን የሚከተሉ፣ ትምህርታዊና የመዝናኛ ፕሮግራሞች አይመስሉም፡፡
ከቋንቋ አጠቃቀም ጋር በተያያዘ በአርአያነት የሚጠቀሱ እንዳሉም  በዚህ አጋጣሚ መጥቀስ ተገቢ ነው፡፡ በስብሰባም ሆነ በብዙኃን መገናኛ በሚተላለፉ መልዕክቶች፣ የቋንቋ አጠቃቀማቸውን በሥርዓትና በአግባቡ በማቅናት በአርአያነት ከሚጠቀሱ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች መካከል፣ (በእኔ በኩል ብዙ ጊዜ እንደተከታተልኩት)፤ አምባሳደር መሐመድ ድሪርና አምባሳደር ግርማ ብሩ፣ ከጋዜጠኞችም የሸገሩ ጋዜጠኛ (ዋና አዘጋጅ) እሸቴ አሰፋ ሊመሰገኑና ዳናቸውን ልንከተል ይገባል፡፡
ስለሆነም የስብሰባ መድረክ ሲዘጋጅ፤ በብዙኃን መገናኛ የሚተላለፉ የተለያዩ ቃለ መጠይቆችም ሆኑ ሌሎች መሰል ፕሮግራሞች ሲካሄዱ የምናደርገው  ንግግር፣ የምናስተላልፈው መልዕክት ለኢትዮጵያዊ ዜጋ መሆኑን ቆም ብለን ልናስተውል ይገባል፡፡ ይህ ካልሆነ ግን በ”ቤቶች ድራማ” ከሚጫወቱት ዝነኛ ተዋናዮች አንዷ የሆነችው ሻሼ፤ ስድስተኛ ክፍልን ያጠናቀቀችና ከሌሎቹ የቤቱ ሠራተኞች በትምህርት የተሻለች መሆኗን ለማሳየት፣ ባልደረቦቿ ሲጠሯት፣ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ክህሎቷን ለመግለጽ፤ “አቤት ማነው የጠራኝ?” በማለት ፈንታ፣ ¨yes, who is የጠራኝ?¨ ያለችው፣ በየመድረኩ ከሚሰማው የቋንቋ አጠቃቀም በምን ይለያል?




                            እንደወረደ የተነገረዉ አገላለጽ                                የተሻለ አገላለ

    በሽተኞቹ health seeking behaviour እንዲኖራቸው ማድረግ
ያስፈልጋል፡፡                                                                                  በሽተኞቹ ለጤና ትኩረት የመስጠት ባህርይ እንዲኖራቸዉ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡
ተማሪዎቹ teacherochun respect ማድረግ አለባቸዉ፡፡                             ተማሪዎቹ መምህራኑን ማክበር አለባቸዉ፡፡

…በቃ…ልጆቹን ወስደው ሲያሳድጉ ምን ያህል satisfied እንደሚያደርግና          …በቃ… ልጆቹን ወስደዉ ሲያሳድጉ ምን ያህል እንደሚያረካ ማየት ይቻላል፡
እንደሚያረካ ማየት ይቻላል፡፡                                                                
Confusion clear ማድረግ አለብን፡፡                                                                 ግራ መጋባትን ማስወገድ አለብን፡፡
የclarity ችግር አለ፡፡                                                                                የግልጽነት ችግር አለ፡፡ ግልጽ አይደለም (ግልጽነት ይጎድለዋል)፡፡
Direct beneficiaries የምንላቸዉ አሉ፡፡                                                          ቀጥተኛ ተጠቃሚዎች የምንላቸዉ አሉ፡፡
እዚህ profitable ካልሆኑ፣ እዚያም profitable አይሆኑም፡፡                                  እዚህ ትርፋማ ካልሆኑ፣ እዚያም ትርፋማ አይሆኑም፡:
እነርሱ የሚፈልጉት Free trade ነው፡፡                                                             እነርሱ የሚፈልጉት ነጻ ንግድ ነው፡፡
የእኛ ባንኮች ገና capitalachewun አልገነቡም፤ developed አልሆኑም፡፡                  የ እ ኛ ባ ን ኮ ች ገ ና አ ቅ ም አ ል ገ ነ ቡ ም ፤ አ ላ ደ ጉም፡፡
እቅዱ ወደ እዚህ align መሆን አለበት፤ gear መደረግ አለበት ማለት ነዉ፡:            እ ቅ ዱ ወ ደ እ ዚ ህ መ ጣ መ ር አ ለ በ ት ፤ ከ እ ዚ ህ ጋ ር መ ቀናጀትና                                                                                                              መስማማት አለበት ማለት ነው፡፡
በሀገራችን lasting peace ለማምጣት ሰላሙ ላይ contribute ለማድረግ ነው፡፡         በሀገራችን ዘላቂ ሰላም ለማምጣት፣ ሰላሙ ላይ አስተዋጽኦ ለማድረግ                                                                                                                    ነው፡፡
እንደዚህ ስንቀመጥ more elegant እና confident ያደርገናል፡፡                                እንደዚህ ስንቀመጥ የበለጠ ውብና በራስ እንድንተማመን ያደርገናል፡፡
እዚህ ያለው burden of diseaዙ high ነው፡፡                                                          እዚህ ያለው የበሽታው/የህመሙ ጫና ከፍተኛ ነው፡፡
በየቦታው dust binoች አሉ፡፡                                                                            በየቦታው የቆሻሻ ማጠራቀሚያ ገንዳዎች አሉ፡፡
ከብቶቹ taste አድርገዉ አይቀምሱትም፡፡ ከብቶቹ (አጣጥመው) አይቀምሱትም፡፡
አገልግሎቱ mainly ለsocietዉ ነዉ፡፡                                                                      አገልግሎቱ በዋናነት ለህብረተሰቡ ነዉ፡፡
ዉድድሩ ከunder 17 ጀምሮ ነዉ፡፡                                                                         ዉድድሩ ከ17 ዓመት በታች ጀምሮ ነዉ፡፡
…የተባለዉ ተጫዋች defender ነዉ፤…ደግሞ top attacker ነዉ፡፡                           …የተባለው ተጫዋች ተከላካይ ነው፤….. ደግሞ ከፍተኛ አጥቂ                                                                                                                           ነው፡፡
ስለዚህ GTP 2 ላይ export led መሆን አለበት፡፡                                                  ስለዚህ የዕድገትና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ሁለት በወጪ ንግድ ላይ                                                                                                                     የተመሠረተ (የሚመራ) መሆን አለበት፡፡
Obstaklu እሱ ስለሆነ solve or avoid ማድረግ አለብን፡፡                                    አደናቃፊው እሱ ስለሆነ ችግሩን መፍታት ወይም ማስወገድ አለብን፡፡
Experience share እናደርጋለን፡፡                                                                       ልምድ እንለዋወጣለን (እንጋራለን)፡፡
ሀገሪቱ እንድታድግ ካስፈለገ፣ ዜጎቿ healthy መሆን አለባቸው፡፡                                 ሀገሪቱ እንድታድግ ካስፈለገ ዜጎቿ ጤናማ መሆን አለባቸው፡፡
በትምህርቱ sector complain አለ፡፡                                                                    በትምህርቱ ዘርፍ ቅሬታ አለ፡፡
Maximum benefit extract እያደረግን ነው፡፡                                                       ከፍተኛ ተጠቃሚነት እያገኘን ነው፡፡
ዋናው ነገር thinkinጉ ነው፡፡                                                                              ዋናው ነገር አስተሳሰቡ ነው፡፡
I think ጥሩ identification ይመስለኛል ጥሩ መለያ ይመስለኛል፡፡
ለ maintenance easy የሆነ machine necessary ነው፡፡                                        ለጥገና ቀላል የሆነ መሳሪያ አስፈላጊ ነው፡፡
ይሄ ሰውዬ ለ Research know how የለውም፡፡                                            ይሄ ሰውዬ ስለ ጥናት(ስለምርምር) ዕውቀት የለውም (ምንም አያውቅም)፡፡
…more successful ይሆናል፡፡                                                                     …ይበልጥ ውጤታማ ይሆናል፡፡
This is a high level delegation. (የስዊድን የጤና ሚኒስትር የተናገሩት-
እርሳቸው የውጭ ዜጋ በመሆናቸው ትክክል ናቸው፡፡)
እዚህ የመጣው high level delegation ነው፡፡(ስዊድን የሚኖር አብሮ
የመጣ ኢትዮጵያዊ የተናገረው)                                                                                እዚህ የመጣው ከፍተኛ የልዑካን ቡድን ነው፡፡
ለሚቀጥለው generation ብሩህ የሆኑ opportunitiዎች አሉ፡፡                                       ለሚቀጥለው ትውልድ ብሩህ የሆኑ ዕድሎች (አጋጣሚዎች)አሉ፡፡
ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የwater ሀብት ተወካይ ነኝ፡፡                                                       ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የውሃ ሀብት ተወካይ ነኝ፡፡
Wise ሆነን legitmate እስከሆንን ድረስ…                                                                       አስተዋይ (ብልህ) ሆነን ሕጋዊ እስከሆንን ድረስ…
ምንም አይነት direction ምንም አይነት benchmark ያደረግነው ነገር የለንም፡፡               ምንም ዓይነት የተከተልነው አቅጣጫ፡ምንም ዓይነት የወሰድነው                                                                                                                  ተሞክሮ የለንም፡፡
ኮሌጃችን በሆቴል management, accounting, secretary…                                    ኮሌጃችን በሆቴል አያያዝና አስተዳደር፣በሂሳብ አያያዝ፣በፀሐፊነት   ተወዳዳሪዎችን መቅጠር ይፈልጋል፡፡                                                                            ሙያ ተወዳዳሪዎችን መቅጠር ይፈልጋል፡፡                         
Capacitያቸው build እየተደረገ ነው፡፡                                                                                  አቅማቸው እየተገነባ ነው፡፡
Idea አስባለሁ፤ idea ይመጣልኛል፤ አንዳንድ ጊዜ ideaውን ለማብሰልሰል
walk አደርጋለሁ፡፡                                                                                         አስባለሁ፤ ሀሳብ ይመጣልኛል፤ አንዳንድ ጊዜ ሀሳቡን ለማብሰልሰል                                                                                                                         በእግር እጓዛለሁ::
ቴዎድሮስ ከአባ ሰላማ crown ነጥቆ ሲያደርግ የሚያሳይ ቴያትር ነበር፡፡                      ቴዎድሮስ ከአባ ሰላማ ዘውድ ነጥቆ ሲያደርግ የሚያሳይ ቴያትር ነበር፡፡
Physically, mentally affect ያደርጋል፡፡                                                               በአካልም፣ በአእምሮም ይጎዳል፡፡
Business manual expand ያደርጋል…                                                              የቢዝነስ መመሪያ ያስፋፋል፡፡
At the end of the course ግን I don’t know በቃ ምን እንደማደርግ                          በኮርሱ (በትምህርቱ) መጨረሻ ግን በቃ ምን እንደማደርግ          አላውቅም፡፡                                                                                                                   አላውቅም፡
                                                                                               
ኮንትራክተሮቹን መክሮ ወደ ሥራ መመለስ wise decision ነው፡፡                          ኮንትራክተሮቹን መክሮ ወደ ሥራ መመለስ አስተዋይነት ያለው ውሳኔ                                                                                                                ነዉ፡፡
Export standard meet ለማድረግ ነው፡፡                                                        የወጭ ንግድን ደረጃ ለሟሟላት ነው፡፡
Basically ግን ጥቅማችንን compromise በማያደርግ መንገድ at the                        በመሠረቱ ግን ጥቅማችንን በማይደራደር (አሳልፎ በማይሰጥ) መንገድ፣ በተመሳሳይ ሁኔታ የግብፅን ጥቅም በማይነካ መልክ…
same time የግብፅን ጥቅም በማይነካ መልክ…
በመሠረቱ ግን ጥቅማችንን በማይደራደር (አሳልፎ በማይሰጥ) መንገድ፣ በተመሳሳይ
ሁኔታ የግብፅን ጥቅም በማይነካ መልክ…
Intiatiቩን ወስደን invite ብናደርጋቸው…                                                              ተነሳሽነቱን ወስደን ብንጋብዛቸው…
በQuality ደረጃ gapoች አሉ፤ ይህንን feel እናደርጋለን፡፡                                             በጥራት ደረጃ ክፍተቶች አሉ፤ይህ ሁኔታ እንዳለም ይሰማናል፡፡
Compromise ማድረግ ይኖራል፤ it depends፤ challenጆች አሉ፡፡ yes
accordingly ትፈታለህ፡፡
                                                                                               ድርድር ማድረግ (መደራደር) ይኖራል፤እንደ ሁኔታው ነው፡፡ ፈተናዎች አሉ፤ አዎ
                                                                                                  እንደ ሁኔታው ትፈታለህ፡፡
Time set አድርገን ፕሮግራሞቹ adjustment ያደርጋሉ ማለት ነው፡፡         የ ጊ ዜ ሰሌዳ አዘጋጅተን ፕሮግራሞቹ (መርሃ-ግብሮቹ) ይስተካከላሉ ማለት                                                                                                         ነዉ፡፡
At the same time ለ human problem የለውም፤ effective ነው፡፡                             በተመሳሳይ ሁኔታም ለሰው ችግር የለውም፤ውጤታማ ነዉ፡፡

Read 1232 times