Saturday, 25 January 2020 11:32

ኢትዮጵያ ከቻይና በሚገቡ መንገደኞች ላይ ምርመራ ማድረግ ጀመረች

Written by  መታሰቢያ ካሳዬ
Rate this item
(1 Vote)

     በቻይና ውሃን ግዛት የተቀሰቀሰውና ከ25 በላይ ቻይናውያንን ለሞት የዳረገው ኮሮና ቫይረስ ለኢትዮጵያም ስጋት ሆኗል፡፡ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከቻይና የሚመጡ መንገደኞችን መመርመር ጀምሯል፡፡ እስካሁን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች አለመገኘታቸውንና አየር መንገዱ በተለይም ከቻይና የሚገቡ መንገደኞች ላይ ጥበቃ ፍተሻ እያደረገ መሆኑ ተገልጿል፡፡
የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲቲዩት ይህንኑ ጉዳይ አስመልክቶ ዛሬ ለጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥቷል፡፡
ከእንስሳት ወደ ሰው እንደተዛመተ የሚነገርለት ይኸው ቫይረስ በአሁኑ ወቅት በትንፋሽ አማካኝነት ከሰው ወደሰው በመተላለፍ ላይ መሆኑ ተገልጿል፡፡ የቫይረሱን መከሰት ተከትሎ ቻይና በቤጂንግና ሆንግኮንግ የሚካሄዱ ታላላቅ ዝግጅቶች እንዳያካሂድ ተወስኗል፡፡ ቫይረሱ በተከሰተበት ውሃን ከተማ ባቡርም ሆነ አውሮፕላን እንዳይገባም እንዳይወጣም ተከልክሏል፡፡ በቻይና 25 ሰዎች በበሽታው ሲሞቱ 880 ያህሉ ደግሞ በቫይረሱ ተይዘዋል፡፡ ታይላንድ፣ አሜሪካ፣ ታይዋን ደቡብ ኮሪያ ቬትናምና ሲነጋፖር ውስጥ በበሽታው የተያዙ ሰዎች ተገኝተዋል፡፡ ከአፍሪካ ጋና ናይጄሪያ፣ ኬኒያ፣ ግብጽና ደቡብ አፍሪካ የቫይረሱ ስርጭት ስጋት ያጠላባቸው ከተሞች ሲሆኑ በአሁኑ ወቅት በአየር መንገዶቻቸው ከቻይና በሚገቡ መንገደኞች ላይ ምርመራ ጀምረዋል፡፡

Read 866 times