Saturday, 18 January 2020 13:57

ጥበብ በሃሳብ መንገድ ላይ

Written by  ተመስገን
Rate this item
(2 votes)


             ሰውየው በሺ ከሚቆጠሩት የእምነት ክፍሎች ያንደኛው ‹ፓስተር› ነበር፡፡ ‹ነቢያችን› እያሉ
…. But I see
I am I is  only mine
And belongs to me
And to nobody else;;
Not to an angel nor to God.
Man  for himself (Eric From)
ብዙ ሰዎች ‹በራስ መቆም› ያዳግታቸዋል:: በራስ መቆም ሁለት ዓይነት ነው፡፡ አንደኛው እግር ወደ ላይ አናት ወደታች ሆኖ  (Upside down) መቆም ማለት ነው። እንደ አርጋው በዳሶ፡፡ ዮጊዎች ‹Reverse pose› ይሉታል፡፡ … እዚች ጋ አንድ አሮጌ ቀልድ ላውራላችሁ።- ሰውየው ከሕይወት ሲያተርፍ የኖረ ነው፡፡  ‹‹ To get more out of life ›› እንደ ሚሉት፡፡ ጊዜው ሲደርስ ሞተ፡፡… ገነት ገባ፡፡ በገነት ምንም የለም::… ካለመሆን በስተቀር፡፡ ‹መሆን› ምድር ላይ ነው፡፡ አልተመችውም፡፡ አልፎ አልፎ ግን ከሩቅ የሚመጣ ቆንጆ ሙዚቃ እየሰማ ይገረማል:: ወደ ጠባቂው መልአክ ሂዶ፡-
‹‹ይኸ የምሰማው ሙዚቃ ከየት ነው?›› በማለት ጠየቀ
‹‹ከገሃነም››… ሰውየው ትንሽ አሰበና…
‹‹ወደዛ መሄድ እችላለሁ?››
‹‹ከወጡ መመለስ አይቻልም››
‹‹እሽ››
‹‹በኋላ እንዳይቆጭህ››
‹‹ችግር የለም›› ብሎት ሄደ፡፡ እዛ ሲደርስ አህዛብ በእሳት ደለል ላይ ይደንሳሉ፣ ይዝናናሉ:: አንዱ ተቀላቀላቸው ደውሉ ተደወለ፡፡ የዕረፍት ሰዓታችሁ ስላለቀ…
‹‹ጭንቅላት ወደ ታች እግር ወደ ላይ›› ተባባሉ። ለካስ ነፃነታቸው በየሃያ አራት ሰዓቱ አስር ደቂቃ ብቻ ነበረች፡፡
ሁለተኛው ‹በራስ መቆም› ማለት የግል ነፃነትን ማስከበር ወይም Independent መሆንን የሚያመላክት ነው፡፡ ለድርጊታችን ወይም ‹ልክ› ነው ብለን የምናምንበትን ነገር ለመፈፀም የሌሎችን ቡራኬ አለመሻት፣ መመሪያ ተቀባይ አለመሆን ወይም ከመንገኝነትና ከቡድን ስሜት መራቅ እንደ ማለት ነው፡፡
ወዳጄ፡- በዚህ ዘመን ሌሎች ሰዎች ሲያደርጉ ስለ ተመለከትን ብቻ ‹‹ለምን?›› ብለን ሳንጠይቅ ተቀብለን የምናስቀጥላቸው ነገሮች እየበዙ መጥተዋል፡፡ ታክሲ ለመያዝ እየተገፈታተሩ መሮጥ፣ ገብተን ከተቀመጥን በኋላ ደግሞ ትርፍ ሰውና ትርፍ ክፍያ ሲጫንብን ምንም እንዳልሆነ መቀበል፣ ከመጠን በላይ ለሚጮኸው ‹ሙዚቃ› ቁብ አለመስጠትና ሌሎች አዲስ ‹ባህል› ያደረግናቸው ጉዳዮች ሞልተው ተትረፍርፈዋል:: ወዳጄ፡- ‹ለምን?› ብሎ መጠየቅ ሃጢዓት አይደለም፡፡ ትርፍ እንጂ ጉዳት የለውም:: ሁሉን ነገር ሌሎች እስኪ ነግሩህ ወይም እስኪጠይቁልህ ከጠበቅህ ያንተ ቦታ  (Your place on the world) የት ነው?
ጓደኛዬ ሲያጫውተኝ፡- እንደ አሁኑ በዓል በመጣ ቁጥር አንድ ዶሮ (አንድ ዓይነት ወጥ) በሁለት ድስት ስትሰራ የተመለከተ አባወራ ሚስቱን፡-
‹‹ለምንድነው ሁለት ድስት ጥደሽ የምትደክሚው?›› ሲላት…
‹‹እማዬም እንደዚሁ ነው› ምታደርገው›› አለችው፡፡
እናቷን ሲጠይቋቸው፡-
‹‹እናቴ ስታደርግ ዓይቼ ነው›› አሉ፡፡ አያት ሲጠየቁ በጅጉ ገረማቸው፡፡ ‹ይሆናል› ብለው ፈጽሞ ያልጠበቁት ነገር ነበር፡፡ … ለምን?
* * *
ወዳጄ፡- ተነገ ወዲያ በዓለ ጥምቀት ይከበራል፡፡ የዘንድሮው አከባበር ከባለፉት ዓመታት ደመቅ ሊል ይችላል፡፡ በዓሉ በዩኔስኮ  (UNESCO) ቋሚ የባህል ቅርሶች መዝገብ የሰፈረበትና ዕውቅና ያገኘበት ወቅት ስለሆነ:: የእምነቱ ቀኖና እንደ ተጠበቀ ሆኖ ጥምቀት ‹‹ብሔር ብሔረሰቦች›› እንደምንለው የሰዎች ባህል እንጂ ‹ሰዎች› ራሳቸው አይደለም፡፡… አይዳሰስማ!!
ብዙ ፀሐፊዎችና ሀሳባውያን ድንቅየዋ ሄለን ኬለር ተፈጥሮን በገለጠችበት… ‹‹ The most beautiful things in this world cant’t be touched or even seen, they must be felt With the heart” በሚለው አቀራረብ ይስማማሉ፡፡
ወዳጄ፡- ጦርነትን ለመሳሰሉ አሰቃቂ ድርጊቶች የሚውሉ እንደ ጠመንጃ፣ መድፍ፣ ሚሳኤል አይነት መሳሪያዎች ይዳሰሳሉ፡፡
ውጤታቸውም በተጨባጭ ይታወቃል:: ሞት፣ የንብረት ውድመት፣ ስደት ወዘተ፡፡ አብዛኛዎቹ ለሰው ልጆች ህይወት አስደሳችና ጠቃሚ የሆኑ ነገሮች ግን በስሜት የሚለው እንጂ በእጅ የምንነካቸውና በዓይናችን የምናያቸው አይደሉም፡፡ ፍቅር፣ መልካምነት፣ ፀሎትና የመሳሰሉት፡፡ ሰዋዊና ተፈጥሯዊ ውበትም እንደተመልካቹ ስለሚመዘን ከዚሁ ይመደባል:: “Beauty is at the eye of the beholder” እንደሚባለው፡፡
ወዳጄ፡- ጥበብን፣ መገለጫዎቿንና ጥቅሟን (aesthetic value) ለመረዳትና በፍቅሯ ለመስከር የሚቻለው ከስሜት በፊት በዕውቀት፣ በትዕግስት በልምድ ሲታነፁ ይመስለኛል… ከፈረሱ ጋሪው እንዳይቀድም፡፡ በበጐም እንኳ ቢሆን፣ አንዳንድ ጊዜ ከልክ ያለፈ ስሜት ጉዳት ሊያስከትል ይችላልና፡፡
ሐምሌት በአውሮፓ ሲከወን ኢያጐ ላይ ሽጉጥ የሚተኩስና ጫማ የሚወረውር ኦዲየንስ እንደነበር ሰምተናል፡፡
ወዳጄ፡- የክፋት ቃና የሌላቸው የቅናት ዓይነትና ንዴትም አሉ፡፡ በፍፁም ሊወገዱ የማይችሉ፡፡ ያለነሱ ህይወት ጐዶሎ ናት፡፡ ያለነሱ የሚኖሩ መላዕክት ወይም “ኒርቫናን የተቀዳጁ ብፁዐን ናቸው፡፡ አሸንፊው እንዳይማርኩን ግን መጠንቀቅ ተገቢ ነው፡፡ ለዚህ ነው ሰዎች መንፈሳዊ ድጋፍ የሚሹት፡፡ ለዚህ ነው የምንጠቀመው፡፡
ውስጣዊ ጥንካሬ የሚፈጥሩልን ሌሎች ሰዋዊ ስሜቶችም ያጋጥማሉ፡፡ እንደ ሼክስፒር፣ ደስቶቭስኪ፣ ሃውትሮን፣ ሄስ፣ ዎልፍና መሰል ፀሐፍት ላይ በብዛት እናገኛቸዋለን:: ለብዙ ቅዱሳን እምነትና መጻሕፍትም የአስተምህሮታቸው ምሰሶ (Pillars) ሆነው ይጠቀሳሉ፡፡ የባልቲሞሩ ዴዚ ደሬታም የሚመክረን እነሱን መሠረት አድርጐ ነው፡፡ ዴፓክ ቾፕራም፡፡
In the midst of movement and chaos, keep stillness inside you” በማለት ያጠናክረዋል፡፡
ወዳጄ ቅድም እንዳልነው ሀይማኖታዊው ቀኖናውን ወደ ጐን ትተን እኔ እንደሚገባኝ ጥምቀት በፀበሉ በኩል የቅዱሳን አባቶች ኢነርጂ ወይም መንፈስ ወደ ምዕመኑ የሚደርስበት ስርዓት ወይም መንገድ ይመስለኛል፡፡ የሰፈረብንን አጓጉል አባዜ ገለል እንዲያደርግልን Washine out the gloom እንደሚሉት!!
ወዳጄ፡፡ አንዳንዶቻችን በወጣትነታችን ዓይናችንን የጋረደብን ወይም በትክክል ለማሰብ፣ ለመገንዘብና ለመሞከር አቅቶን የተውነው ነገር “ስንጠመቅ” ይገለጥ ይሆናል፡፡ ማን ያውቃል?” ጥምቀትን ስናስብ የመደመርንና በራስ ለመቆም ብቃትም ማሰብ ጠቃሚ ነው፡፡ ምናልባት ወደፈለግንበት የሚያደርሰን ጐዳና ሊሆን ይችላልና!!
* * *
ወደ ጨዋታችን ስንመለስ፡፡ ባልና ሚስት አያት ዘንድ ሄደው፡-
“ለምንድነው በሁለት ድስት አንድ ዓይነት ወጥ ሲሰሩ የኖሩት?” ብለው ሲጠይቋቸው እማሆይ ከት ብለው ስቀው” ትልቅ ድስት ስለሌለኝ ነዋ!” አሉዋቸው አሉ፡፡ አ/መ ወዳጄ፡- ለማንኛውም ጃንሜዳ እንገናኝ፡፡ አዳዲስ ትዕይንት (art) አይጠፋምና፡፡ በነገራችን ላይ “Earth without “art” is Eh!” በማለት የተጠበበው ማን ይመስልሃል?
ሠላም!! መልካም በዓል!!        


Read 1753 times