Saturday, 18 January 2020 13:18

‹‹ፊት ማንበብ›› መጽሐፍ ለንባብ በቃ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(2 votes)

  በፓትሪሺያን ማካርቲ ተጽፎ በሃብታሙ አየለ ወደ አማርኛ የተተረጎመው ‹‹ፊት ማንበብ›› መጽሐፍ ለንባብ በቃ፡፡ መጽሐፉ በዋናነት ሰዎችን በማየት ባህሪያቸውን የማወቅ ስነ ልቦና ላይ የሚያጠነጥን ሲሆን ‹‹ሚየን ሺያንግ›› (የፊት ንባብ) ከሦስት ሺህ ዓመታት በፊት የነበረ የቻይናዊያን ጥበብ እንደሆነ በመጽሐፉ ተገልጿል፡፡
የሰውን ውጫዊ አካል በማየት ባህሪን ማወቅ እንዴት ይቻላል የሚለው የብዙዎች ከባድ ጥያቄ በዚህ መጽሐፍ መልስ እንዳለው ተርጓሚው በማስታወሻው ገልፀው፤ ይህ መጽሐፍ ‹‹አምስቱ የሰው አይነቶች›› በሚል ታትሞ ለንባብ የበቃው መጽሐፍ ቁጥር ሁለት ነውም ተብሏል፡፡ በ248 ገጽ ተቀንብቦ በ150 ብር ለገበያ መቅረቡም ታውቋል፡፡  

Read 10777 times