Sunday, 12 January 2020 00:00

የቀድሞ ጠ/ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝና ምክትላቸው ለአቶ በረከት ስምኦን ምስክር ሆነው ፍ/ቤት ይቀርባሉ

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(4 votes)

    የቀድሞ ጠ/ሚኒስትር አቶ ኃይለ ማርያም ደሳለኝ፣ ም/ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንንና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ገዱ አንዳርጋቸው ከነገ በስቲያ ሰኞ በባህር ዳር ፍ/ቤት ለእነ አቶ በረከት ስምኦን የመከላከያ ምስክር ሆነው እንደሚቀርቡ ይጠበቃል፡፡
ከጥረት ኮርፖሬት ጋር በተያያዘ በሙስና የተከሰሱት የቀድሞ ከፍተኛ ባለሥልጣን አቶ በረከት ስምኦን መሪዎቹን በምስክርነት ቆጥረው ለሀሙስ ታህሳስ 30 ቀን 2012 ዓ.ም ፍ/ቤት ይቀርባሉ ተብሎ ቢጠበቅም ምስክሮች ሊቀርቡ አለመቻላቸውን ምንጮች ለአዲስ አድማስ ጠቁመዋል፡፡
እነ አቶ ኃይለ ማርያም የምስክርነት ቃላቸውን ለመስጠት በእለቱ ባህር ዳር ከተማ ተገኝተው እንደነበር የጠቆሙት ምንጮች፤ ሆኖም እኒህ ምስክሮች ባልታወቀ ምክንያት ችሎት ሳይገኙ መቅረታቸውን ተናግረዋል፡፡
ይህን ተከትሎም የአቶ በረከት ስምኦን ጠበቃ፤ ምስክሮቹ በፖሊስ ተገደው እንዲቀርቡ ለፍ/ቤቱ አቤቱታ ቢያቀርቡም ፍ/ቤቱ አቤቱታውን ውድቅ በማድረግ፣ ግለሰቦቹ በድጋሚ መጥሪያ እንዲደርሳቸውና ለሰኞ ጥር 4 ቀን 2012 ቀርበው እንዲመሰክሩ ትዕዛዝ አስተላልፏል፡፡

Read 11919 times