Saturday, 11 January 2020 12:17

‹‹የሚሰማ ጆሮ ቢኖርማ ኖሮ›› መጽሐፍ ለንባብ በቃ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(1 Vote)

   የብላቴን ጌታ ወልደማሪያም አየለን ታሪክ የሚዘክረውና በልጃቸው ፓስካል ወልደማሪያም አየለ የተሰናዳው ‹‹የሚሰማ ጆሮ ቢኖር ኖሮ›› የተሰኘ መጽሐፍ ለንባብ በቃ፡፡
መጽሐፉ ብላቴን ጌታ ወልደ ማሪያም ከልጅነት እስከ እውቀት ያሳለፉትን የትምህርት የስራ፣ የሃላፊነት፣ በአገር ውስጥና በውጭ አገር ያከናወኗቸውን በርካታ አይነት የሕይወት ዘርፎች የሚተነትን ነው:: የመጽሐፉ አዘጋጅ ታሪካቸውን በጽሑፍ ከመግለጽ ባለፈም በአገር ውስጥና በውጭ አገር ከዲፕሎማቶች፣ ከቀዳማዊ ሀይለ ሥላሴና በተለያዩ አገራት የነበራቸውን የሥራ እንቅስቃሴ በፎቶ ለመግለጽ ሞክሯል፡፡
በ197 ገጽ የተቀነበበው መጽሐፉ በ150 ብር ለገበያ የቀረበ ሲሆን ክብሩ መጽሐፍት መደብር በዋናነት ያከፋፍለዋል፡፡ 

Read 2885 times