Saturday, 11 January 2020 12:22

“ጣና ውሃ አይደለም” የፎቶ ኤግዚቢሽን ማክሰኞ ይከፈታል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(1 Vote)

 በኤሌክትሪካል መሃንዲሱና በፎቶግራፍ ባለሙያው ስለሺ ባዬህ ካሜራ የተነሱና በጣና ባህል፣ ታሪክ፣ መልካ ዓምድርና ዕደ ጥበብ ዙሪያ የሚያጠነጥኑ ልዩ ልዩ ፎቶግራፎች ለእይታ የሚቀርቡበት “ጣና ውሃ አይደለም” የተሰኘ የፎቶ አውደ ርዕይ የፊታችን ማክሰኞ ከቀኑ 11፡00 ጀምሮ ካዛንቺስ በሚገኘው ፈንዲቃ የስነ -ጥበባትና የባህል ማዕከል ይከፈታል፡፡ የፎቶግራፍ ባለሙያው ስለሺ ባዬህ፤ በጣና ዳር ተወልዶ እንደማደጉ ጣና ከውሃ እንደሚወፍርና ከዚያም ባሻገር ያለውን ተፈጥሯዊ ትሩፋት በጣና አካባቢ በመዘዋወር በካሜራውና በአዕምሮው ያስቀረ ሲሆን ሌላውም አይቶ የጣናን ውሃ ብቻ አለመሆን እንዲያረጋግጥ አውደ ርዕዩን ማዘጋጀቱን አስታውቋል፡፡
33 ምስሎችን ባካተተው በዚህ አውደ ርዕይ የመክፈቻ ሥነ ሥርዓት ላይ ታዋቂ ሰዎች፣ ሰዓሊያን፣ እውቅ የፎቶግራፍ ባለሙያዎች፣ የፎቶግራፍ አድናቂዎችና ጋዜጠኞች እንደሚታደሙና ፎቶግራፎቹ ለሁለት ቀናት ለእይታ ክፍት እንደሚሆኑ የዝግጅቱ አስተባባሪ ጋዜጠኛ ትዕግስት ታደለ ገለፃ የጣና ዙሪያ ገደማት ነዋሪዎች ያለመብራት መኖራቸውን ለማስታወስ ፎቶዎቹ በጭለማ ውስጥ በጧፍ ብርሃን ለእይታ ይቀርባሉ ብላለች፡፡

Read 10480 times