Saturday, 11 January 2020 12:20

“የጊዜ ሰሌዳ” የግጥም መድበል በጐንደር ተመረቀ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

 በገጣሚ ሰይድ ኑርሁሴን የተጻፉ ግጥሞችን ያካተተ “የጊዜ ሰሌዳ” የተሰኘ የግጥም መድበል ባለፈው ሳምንት እሁድ በጐንደር ከተማ ቋራ ሆቴል ገጣሚያን፣ ደራሲያንና የኪነ -ጥበብ አፍቃሪዎች በተገኙበት ተመረቀ፡፡
በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ ልዩ ልዩ ኪነ-ጥበባዊ መሰናዶዎች ግጥሞችና የመጽሐፍ ዳሰሳ መቅረቡም ታውቋል፡፡ የግጥም መድበሉ በፖለቲካዊ፣ ማህበራዊ፣ ስነልቦናዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ላይ የሚያጠነጥኑ ከ70 በላይ ግጥሞችን ያካተተ ሲሆን በ102 ገጾች የተቀነበበው መጽሐፉ፤ በ50 ብር ለገበያ ቀርቧል፡፡
ገጣሚው ከዚህ ቀደም “የህይወት ፍሬ” እና “መንገድ” የተሰኙ ግለ ታሪክ መጻህፍትን እንዲሁም “ምን ይውጠን” የተሰኘ የግጥም መደብል ለንባብ አብቅቷል፡፡


Read 10798 times