Print this page
Tuesday, 07 January 2020 00:00

የህክምና ባለሙያዎችን በተመሳሳይ ብቃት ማስመረቅ

Written by  ፀሐይ ተፈረደኝ ከኢሶግ
Rate this item
(1 Vote)

   ESOG የኢትዮጵያ የማህጸንና ጽንስ ሐኪሞች ማህበር እና በምህጻረ ቃሉ CIRHT እየተባለ የሚጠራው መስሪያ ቤት በትብብር ከሚሰሩ ዋቸው ፕሮጀክቶች አንዱ ወደ ማህጸንና ጽንስ ሕክምና ልዩ ትምህርት የሚገቡ ጠቅላላ ሐኪሞች ጥራትና ብቃት ባለው መንገድ ደረ ጃውን ያሟላ ትምህርት በሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች በተመሳሳይ መንገድ እንዲሰጥ ለማድረግ ድጋፍ መስጠት ነው:: በዚህም መሰረት ሐኪሞቹ የማህጸንና ጽንስ ሕክምና ከሚሰጥባቸው ከአስራ ሁለት ዩኒቨርሲቲዎች ደረጃውን የጠበቀ ትምህርትን በእኩል ቀስመው የተመጣጠነ እና ወጥ የሆነ ደረጃ እንዲኖራቸውና ህብረተሰቡንም በተመሳሳይ እና በተሙዋላ መልኩ እንዲያገለግሉ ለማድረግ ሁለተኛው ዙር ፈተና ተሰጥቶአል፡፡
ይህ ትምህርትና ምዘና ምን እንደሆነ ከአሁን ቀደም ለንባብ ያልን ሲሆን ለማስታወስ ያህል ቀደም ካለው እትም የሚከተለውን ታነቡ ዘንድ መርጠናል፡፡
የማህጸንና ጽንስ ሕክምና ልዩ ትምህርት ባለሙያዎች ትም ህርቱን የሚወስዱት ለአራት አመት ሲሆን በትምህርት ላይ እያሉ የመመዘኛ ፈተና እንዲፈ ተኑ ይደረጋል፡፡ ከአ ሁን ቀደም በነበረው አሰራር  በማህጸንና ጽንስ ሕክምና ልዩ የሙያ ትምህርት በመማር ላይ ያሉት የህክምና ባለሙያዎች አራቱን አመት የትምህርት ጊዜ ካጠናቀቁ በሁዋላ በአራተኛው አመት ላይ የሚሰጣቸውን መመዘኛ ሲያልፉ ለሙያው ብቁ ናቸው ተብሎ ይመረቁ የነበረ ሲሆን አሁን ግን ከዚያ በተ ጨማሪ certification examination ማለትም ከሁሉም ትም ህርት ቤቶች የሚመረቁትን ምሩቃን ወጥ የሆነ ፈተና ፈትኖ እውቅና ወይንም የሙያ ፈቃድ መስጠት እንዲያስችል የተዘረጋ አሰራር ነው፡፡ በሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች ማለትም በጥቁር አን በሳ፤ በአዋሳ፤ በጅማ፤ በመቀሌ… ወዘተ በ12 ቱም ዩኒቨርሲቲዎች ያሉት ባለሙያዎች ልዩ ትምህ ርቱን በሚገባ ተከታትለዋል? ተመሳሳይ እውቀት አላቸው? እናቶችን ወጥ በሆነ እና በተመ ሳሳይ ደረጃ ሕክምና በመስጠት ማገልገል ይችላሉ? የሚለውን ለመመዘን እኩል እውቀት ፤እኩል ክህሎት አላቸው ወይ የሚለውን ለመመዘን የሚያስችል ነው፡፡
በእርግጥ የሙያ ተማሪዎቹ በየትምህርት ቤታቸው የሚመዘኑበትን ፈተና በማለፋቸው ወደስራ ሊገቡ ይችላሉ፡፡ ነገር ግን ሀገሪቱ ለምትፈልገው ደረጃ መብቃት አለመብቃቱን ለማረጋገጥ የሚ ረዳው ይህ በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የታመነበት እና የማህጸንና ጽንስ ሐኪሞች ማህበር የሚሰጠው የcertification examination መመዘኛ ነው፡፡
ዶ/ር ተስፋነህ ፍቅሬ የፕሮጀክቱ አስተባባሪ
የመጀመሪያው ፈተና ባለፈው አመት የተሰጠ ሲሆን ይህ የሁለተኛው ዙር ፈተና ደግሞ ዘንድሮ እ.ኤ.አ ሴፕቴምበር 4 እና 5/2019 ተሰጥቶአል፡፡ ይህ ሁለተኛው ዙር ፈተና በተማ ሪዎች ውጤትና በፈተናው አሰራር በኩል ምን መልክ ነበረው የሚለውን ከአስራ ሁለቱም ዩኒቨርሲቲዎች የተወከሉት ባለሙያዎችና ከኢትዮጵያ የማህጸንና ጽንስ ሐኪሞች ማህበር እንዲሁም ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት በተገኙበት እ.ኤ.አ ዲሴም በር 27/ ለግማሽ ቀን በአዲስ አበባ ቀርቦ ነበር፡፡ ዶ/ር ማህሌት ይገረሙ የኢትዮያ የማህጸንና ጽንስ ሐኪሞች ማህበር ቦርድ ም/ፕሬዝዳንት እና የcertification examination  ፕሮጀክት ኮሚቴ መሪ ባቀረቡት መረጃ እንደታየው፡-
ፕሮግራሞቹን በአገር አቀፍ ደረጃ ደረጃውን የጠበቀ ለማድረግ፤
ፕሮግራሞቹን ጠንካራ ለማድረግ፤
የልዩ ሙያ ተማሪዎችን ተነሳሽነት እንዲጨምር ለማድረግ ከፍተኛ ጥረት ተደርጎአል፡፡
ከዚህም በተጨማሪ የዩኒቨርሲቲዎቹን አስተዳደሮች ትኩረት እንዲስብና በሙያው ዘርፍ አንድ አይነት ተመሳሳይ ባለሙያዎች እንዲኖሩ ለማድረግ እንዲረዳ፤
ወጥ የሆነ የትምህርት ስርአትን ለመዘርጋት፤
የፕሮግራሙን ተግባራዊነት ለመቆጣጠር
ልምድ ያላቸው እና የቆዩ ዩኒቨርሲቲዎች እና ሌሎችም ሙያው የሚተገበርባቸው ባለሙያዎችን በብቃት አስተምሮ ለማውጣት የተሻለ አቅም እንዲኖራቸው ማድረግ
እና ለልዩ ሙያ ትምህርት የሚገቡ ሐኪሞችን የስራ ጫና ለመቀነስ እንዲችሉ ጥንቃቄ የተሞላው ስራ በፕሮጀክቱ በኩል ተግባራዊ እንዲሆን ጥረት ተደርጎአል፡፡
የዩኒቨርሲቲዎችን አቅም በመገንባትም ደረጃ  የኢትዮጵያ የማህጸን እና የጽንስ  ሐኪሞች ማህበር እና የአሜሪካ የማህጸንና ጽንስ ሐኪሞች ኮሌጅ የማህጸንና ጽንስ ሕክምና ሙያ ተማሪዎችን የትምህርት ስርአት ከሙያው ጋር በተጣጣመ መልኩ መንደፍ እንዲቻል እንዲሁም ለልዩ ሙያው ስልጠና የሚገ ቡትን ትምህርትአሰጣጥ በሚመለከት የተሟላ ስራ መስራት የሚያስችል የአቅም ግንባታ ስራ ተሰርቶ አል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ዩኒቨርሲቲዎቹ የቁጥጥርና ምዘናውን ስራ ጥራት ከስራው አጋሮች ጋር በመሆን መስራትና  ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር ልምድን በመለዋወጥ ረገድ ትብብር መፍጠር እንዲሁም ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ፤ትምህርት ሚኒስቴር እና ዩኒቨርሲቲዎቹን የሚያገናኝ መድረክን በመፍጠር ረገድ ESOG እና ACOG ተገቢውን ድርሻ ተወጥተዋል፡፡
ዶ/ር ማህሌት ይረሙ እንደገለጹት የመጀመሪያው ፈተና እ.ኤ.አ June 2018; የተሰጠ ሲሆን በጊዜው የፈተናውን አወጣጥ ለመምራት የሚያገለግለው የፈተና ፕላን (Blue print) የተሰኘው ዶክመንት ያልነበረ እና ጥያቄዎቹ ግን በዩኒቨርሲቲዎቹ እንዲሁም የሚመለከታቸው አካላት ተጨምረው የተዘጋጁ ሲሆን በአስራ ሁለቱም ዩኒቨርሲቲዎች (180) ተመሳሳይ ጥያቄዎች ተዘጋጅተው እንደነበር ገልጸዋል፡፡ ሁለተኛው ፈተናም እ.ኤ.አ Sep 2019; የተሰጠ ሲሆን በዚህ ጊዜ ግን የፈተና ፕላን (Blue print) ስልጠና ለሁ ሉም የሙያ ትምህርቱ ለሚሰጥባቸው ትምህርት ቤቶች አስተማሪዎች ተሰጥ ቶአል፡፡ በሁለተኛው ዙር የቀረቡት ጥያቄዎች በፈተና ፕላን (Blue print)  መሰረት የተዘጋጀ ስለነበር ግልጽ እና ለአሰራር ምቹ በሆነ መንገድ ጥያቄ ዎች ተዘጋጅተው ከአርሲ እና ወላይታ በስተቀር በተቀሩት ዩኒቨርሲቲዎች ለሚገኙ ለሙያው ሰልጣኞች በተመሳሳይ ቀንና ሰአት ተሰጥቶአል፡፡  አርሲና ወላይታ ለሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች የኢፊድሪ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ወደ ልዩ ሙያ ትምህርት የሚገቡ ባለሙያዎችን ወይንም ጠቅላላ ሐኪሞችን ባሉበት የስራ ቦታ ሆነው በሚፈትንበት የኢንተርኔት አሰራር በቀጥታ መስ መር ፈተናውን መስጠት ባይቻልም በሌላ ዘዴ በተመሳሳይ ቀንና ሰአት ከሌሎቹ ዩኒቨርሲቲ ዎች እኩል ፈተናው ተሰጥቶአል፡፡ በዚህም ባለሙያዎቹን ብቁ አድርጎ በአገር ደረጃ ለማቅረብ በቂ የሆነ አሰራር መዘርጋቱ ታውቆአል:: በአሰራሩም የኢፊድሪ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የዩኒቨር ሲቲዎቹና የስራው አጋሮች በቅርበት የሚሰሩበት ሁኔታ ተፈጥሮአል፡፡ የፈተና ፕላን (Blue print) ስልጠና ለሁ ሉም የሙያ ትምህርቱ ለሚሰጥባቸው ትምህርት ቤቶች አስተማሪዎች የተሰጠ በመሆኑም ስርአቱን በመጠቀም ረገድ የፈተናዎቹን አይነትና መጠን እንዲሁም የፈተና ጊዜ አጠቃቀምን ያሻሻለ መሆኑን የፕሮጀክቱ ኮሚቴ መሪ ዶ/ር ማህሌት ይገረሙ አብራር ተዋል፡፡  
‹‹በኢትዮጵያ ከጠቅላላ ሐኪምነት ወደ ማህጸንና ጽንስ ሕክምና እስፔሻሊስትነት ለመዞር ለሚፈ ልጉ ባለሙያዎች ከአሁን ቀደም ትምህርቱ በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ይሰጥ የነበረ ሲሆን ነገር ግን የትምህርት አሰጣጡም ሆነ የፈተናው አቀራረብ ወጥነት የሌለው እና ተመሳሳይ ያልሆነ ነበር ማለት ይቻላል፡፡አንድ ሐኪም በየትኛውም ዩኒቨርሲቲ ወደ ማህጸንና ጽንስ ሕክምና ልዩ ትምህርት ሲገባ የተነ ደፈውን የትም ህርት ስርአት Curriculum በተመሳሳይ መልኩ አግኝቶ ምዘናውም ደረጃ ውን በጠበቀና በስርአት በሚመራ መልኩ በተመሳሳይ ከተካሄደ ወደስራው አለም ሲገቡ በተመ ሳሳይ ሁኔታ ውጤታማ የሆነ ስራ ይሰራሉ ተብሎ ይታመናል፡፡ ይህ በሌላው አለም በአሜሪካና በአው ሮፓ የተለመደና ቀደም ብሎ የተጀመረ አሰራር ሲሆን በኢትዮጵያም የተጀመረው የኢት ዮጵያ የማህጸንና ጽንስ ሕክምና ማህበር ከጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር እንዲ ሁም ድጋፍ በሚያደርጉ አካላት ትብብር ነው፡፡››
ዶ/ር ተስፋነህ ፍቅሬ የፕሮጀክቱ አስተባባሪ ቀደም ሲል ከሰጡት ማብራሪያ የተወሰደ
ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ዶ/ር ዳሜ አበራ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሳይኮሎጂ አሶስየት ፕሮፌሰር የፈተናዎቹን አቀራረብና የተፈታኞቹን ብቃት በሚመለከት ያለበትን ደረጃ የሚገልጽ ዝርዝር መረጃ በጥናት ያቀረቡ አቅርበዋል:: እሳቸው እንደገ ለጹትም በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ቀር በው ፈተናውን የወሰዱት የልዩ ሙያ ተማሪዎች ውጤታቸው የተለያየ መሆኑን እና በአብዛ ኛው ግን ጥሩ ውጤት የተመዘገበበት መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በዚህም መሰረት የኢትዮጵያ ማህጸንና ጽንስ ሐኪሞች ማህበር አሁን የያዘውን ማለትም ባለሙያዎችን አንድ ወጥ የሆነ ምዘና በማድረግ ብቃትን ለማረጋገጥ የሚያስችለውን አሰራር ቢቀጥልበት ለህብረተሰቡ በተመሳ ሳይ መንገድ ደረጃውን የጠበቀ የህክምና አሰጣጥን እውን ማድረግ ያስችላል ብለዋል፡፡

Read 8791 times