Sunday, 05 January 2020 00:00

ከ11 ሺህ ሰው በላይ የተሳተፈበት ‹‹ግባ በለው ሸዋ›› የሙዚቃ ቪዲዮ ተለቀቀ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

 አገር ወዳድ በሆነውና 365ቱንም ቀናት የባህል አልባሳትን በመልበስ በሚታወቀው እንዲሁም የባላገሩ አስጎብኚ ድርጅት ባለቤት በሆነው አቶ ተሾመ አየለ (ባላገሩ) ፕሮዲዩስ የተደረገውና 11 ሺህ ሰው በላይ የተሳተፈበት ‹‹ግባ በለው ሸዋ›› የሙዚቃ ቪዲዮ ትላንትና አርብ ታህሳስ 24 ቀን 2012 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ጀምሮ በ‹‹የኛ ቲዩብ› ተለቅቆ ለእይታ በቅቷል፡፡
በዚህ ቪዲዮ ላይ የሸዋን ባህል አለባበስ የአገር ፍቅር በአጠቃላይ ኢትዮጵያዊነትን ሺህ ዓመት ወደኋላ መልሶ ለመዳሰስ ተሞክሯል፡፡
የሙዚቃ ቪዲዮው ከ5 ሚ.ብር በላይ ወጪ የወጣበት ሲሆን አስራት ቦሰና (ኧረ ና ጎበዙ) በድምፅ ስትጫዎት ተሾመ አየለ (ባላገሩ) ተውኖበታል፡፡ በርካታ ፈረሰኞች እንደተሳተፉበትና በቅርቡም እንደሚመረቅ የታወቀ ሲሆን በዚህ ቪዲዮ ላይ ይሳተፋል በተባለው የሰው ብዛት በእጥፉ ጨምሮ ከ11 ሺህ በላይ ሰው ሊሳተፍ ችሏል፡፡

Read 10645 times