Saturday, 23 June 2012 08:37

“ሰቆቃ” እንደገና ታተመ

Written by  መልካሙ ተክሌ (melkamutekele@gmail.com)
Rate this item
(0 votes)

“ሮማን የወረረ ጀግና” ለአንባቢያን ቀረበ

በደራሲ፣ ወግ ፀሐፊና ተርጓሚ ኤፍሬም እንዳለ ወደ አማርኛ የተተረጐመው የሲድኒ ሼልደን “Morning, Noon and Midnight” የተሰኘ ልብወለድ “ሰቆቃ” በሚል ርእስ ከ13 አመት በፊት ለንባብ መብቃቱ የሚታወስ ሲሆን ይኸው መፅሐፍ ሰሞኑን እንደገና ታትሞ ገበያ ላይ ውሏል፡፡ ተርጓሚው ኤፍሬም እንዳለ የመፅሃፉን በድጋሚ መታተም አስመልክቶ በሁለተኛው እትም መግቢያ ላይ “ሲድኒ ሼልደን በሀገራችን ከሚወደዱት የውጭ ደራስያን ግንባር ቀደሙ ነው፡፡ ለዚህም ማሳያዎቹ የፃፋቸው መፃሕፍት በሙሉ ወደ አማርኛ መመለሳቸው ነው፡፡ ይህ “ሰቆቃ” የተባለው መፅሐፍ ከወጣ ረዘም ያለ ጊዜ በመሆኑ ያላዩት እንዲያነቡት ይኸው ዳግመኛ ታትሟል” ብሏል፡፡በ228 ገፆችና በሰላሳ አምስት ምዕራፎች የተቀነበበው መፅሐፉ፤ በአልፋ አሳታሚዎች የታተመ ሲሆን ዋጋውም 35 ብር ነው፡፡

የጀግናው አትሌት ሻምበል አበበ ቢቂላን ታሪክ እና ገድል የሚተርከው “ሮማን የወረረ ጀግና” የተሰኘው መፅሐፍ ታትሞ ለአንባቢያን ደረሰ፡፡ ከአበበ ቢቂላ ሌላ የ1950ዎቹ ኢትዮጵያን ፖለቲካ የሚዳስሰው መፅሐፍ 292 ገፆች አሉት፡፡ በአቶ ትኩህ ባህታ የተፃፈው ይኸው መፅሐፍ፤ ለሀገር ውስጥ በ50 ብር ለውጭ ሀገራት በ15 ዶላር እየተሸጠ ነው፡፡ አቶ ትኩህ አምና “መለስ ከልጅነት እስከ እውቀት” የሚል መፅሐፍ ማሳተማቸው ይታወሳል፡፡

 

 

Read 1221 times Last modified on Saturday, 23 June 2012 08:39