Saturday, 28 December 2019 13:17

‹‹በኢትዮጵያ የሞት ፍርድ ሊቀር ይገባል››

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(1 Vote)

  የሞት ፍርድ በኢትዮጵያ ሊተገበር እንደማይገባውና ከሕግ ድንጋጌዎችም መውጣት እንዳለበት የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ ገለፁ፡፡
ኮሚሽነሩ ከሰሞኑ ለሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ቀርቦ ውይይት የተደረገበትን በሰው የመነገድና በሕገወጥ መንገድ ድንበር የማሻገር ወንጀል ረቂቅ ሕግን አስመልክቶ በማህበራዊ ገጻቸው ባሰፈሩት አስተያየት፤ ረቂቅ ሕጉ የሞት ፍርድን ማካተቱ ተገቢ አይደለም ብለዋል፡፡
ሕጉ በእጅጉ አስፈላጊ ቢሆንም በውስጡ የሞት ቅጣትን ማካተቱ ግን ስህተት ነው ያሉት ኮሚሽነሩ የሞት ፍርድ ጨካኝና ኢ.ሰብዓዊ ቅጣት ነው ብለዋል፡፡
አገሪቱ በጀመረችው አዲስ የለውጥ ምዕራፍ ውስጥ የሞት ፍርድ በማንኛውም መልኩ ተፈፃሚነቱ ሊታቀብና ለወደፊቱም ሊቀር እንደሚገባ ኮሚሽነሩ አብራርተዋል፡፡
የሞት ፍርድ ጨካኝና ኢ.ሰብዓዊ ተግባር ከመሆኑም ባሻገር ሊመለስ ወይም ተመልሶ ሊታይ የማይችል ቅጣት በመሆኑ በማንኛውም መልኩ ሊቀር ይገባዋል ብለዋል፡፡

Read 11808 times