Saturday, 21 December 2019 12:36

ግለሰቡ ባደጉበት ቀበሌ ያስገነቡት ቤተ መጻሕፍት ስራ ጀመረ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)


               በኦሮሚያ ክልል ፊንፊኔ ዙሪያ ልዩ ዞን አቃቂ ወረዳ ኦዳነቤ ቀበሌ ውስጥ ተወልደው ያደጉትና ኑሯቸውን መውጭ አገር ያደረጉት ገዛኸኝ ወርዶፋ (ዶ/ር) ከውጭ አገር በመመላለስና በራሳቸው ወጪ በኦዳነቤ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት ውስጥ ያስገነቡት ትልቅ ቤተ መጻሕፍት ተመርቆ ሥራ ጀመረ። ግለሰቡ በዚሁ ቀበሌ ውስጥ ልጅነታቸውን ያሳለፉና በአሁኑ ወቅት በውጭ የሚኖሩ ሲሆን የአካባቢያቸውን ወጣቶችና ተማሪዎች እውቀት ለማስፋት በማሰብ ቤተ መጻሕፍቱን መገንባታቸውን ባለፈው ቅዳሜ በምርቃቱ ላይ ተናግረዋል።
በምርቃት ሥነ ሥርዓቱ ላይ የኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ ሀላፊዎች፣ አባገዳዎች የት/ቤቱ መምህራንና ሰራተኞች ተገኝተዋል። ቤተ መጽሐፍቱ መገንባቱ ለመማር ማስተማር ሂደቱ ክፍተኛ እገዛ እንደሚያደርግና የትምህርት ጥራትን እንደሚጨምር የት/ቤቱ ርዕሰ መምህር አቶ ጀቤሳ ገመዳ ገልጸው ግለሰቡ ላደረጉት አስተዋጽኦ ምስጋና አቅርበዋል:: ዶ/ር ገዛኸኝ ወርዶፋ በቀጣይ ለአካባቢው ማህበረሰብ ንፁህ የመጠጥ ውሃ ከጉድጓድ ለማውጣት እቅድ እንዳላቸው ተገልጿል፡፡

Read 2964 times