Saturday, 21 December 2019 12:27

“ሀድራና ሙሃባ” የኪነ-ጥበብ ምሽት ዛሬ በባቲ ከተማ ይካሄዳል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

በእውቁ ደራሲና ጋዜጠኛ ዘላለም መሉ የተዘጋጀው ‹‹ሀድራና ሙሃባ›› የተሰኘ የኪነ ጥበብ ምሽት ዛሬ ቅዳሜ ታህሳስ 11 ቀን 2012 ዓ.ም ከምሽቱ 12፡00 ጀምሮ በወሎዋ ባቲ ከተማ ውስጥ በማህሙዴ ካፊቴሪያ ይካሄዳል::
በዕለቱም ወግ፣ ግጥም፣ ዲስኩር፣ ወግ፣ መነባንብና ሙዚቃ ለታዳሚ የሚቀርብ ሲሆን በዚህ ምሽት ባቲ የምትታወቅበት የሙዚቃ ቅኝት፣ የልጃገረዶች ውበት፣ የባቲ የገበያና የግብይት ባህል የሕዝቡ እርስ በርስ መዋደድና ፍቅር እንደሚዳሰስ ጋዜጠኛ ዘላለም ሙሉ ገልጿል፡፡
በዚህ መሰናዶ ገጣሚና ጠበቃ መንግሥቱ ዘገዬ (ጃኖ)፣ አብዱ ሰላም ሁመድ፣ ሙሉጌታ ስዩም፣ መሃመድ ሷሊህ፣ ኢስማኤል ኢብራሂም፣ ሀቢባ መሃመድና ሌሎችም የአካባቢው ወጣቶች ስራቸውን እንደሚያቀርቡ የታወቀ ሲሆን፣ መግቢያው ነፃ እንደሆነና የኪነ ጥበብ ምሽቱ በየወሩ እንደሚካሄድ ተገልጿል፡፡


Read 849 times