Print this page
Saturday, 23 June 2012 08:19

የክሪስ እና ድሬክ ጥል ተወሳስቧል

Written by  ግሩም ሠይፉ
Rate this item
(0 votes)

ባለፈው ሳምንት ክሪስ ብራውንና ድሬክ በኒውዮርክ በሚገኝ የምሽት ክበብ ውስጥ በፈጠሩት ብጥብጥ ዙርያ የሚወጡ ዘገባዎች ሁኔታዎችን እያወሳሰቡ ነው፡፡ በማንሃታን በሚገኝ ዌይፕ የተባለ ክለብ ስለተፈጠረው ሁከት ፖሊስ ምርመራውን እያካሄደ ሲሆን ጠርሙሶች እንደድንጋይ በተወረወሩበት ብጥብጡ ላይ ከ5 በላይ ሰዎች መጎዳታቸውን አሶስዬትድ ፕሬስ ዘግቧል፡፡ በተወረወሩ ጠርሙሶች ከተጎዱት መካከል አንዷ አውስትራሊያዊት ሴት ስትሆን ክሪስ ብራውንም አገጩ ላይ መፈንከቱን የሚያሳይ ምስልን በቲውተር ገፁ ይፋ አድርጓል፡ በተፈጠረው ሁከት ዙርያ እየተናፈሱ ያሉ ወሬዎችን ያበዱና ሃሰት የበዛባቸው ብሎ ክሪስ ብራውን በትዊተር ገፁ መፃፉን ያመለከተው ዋሽንግተን ፖስት ምናልባትም ለጥሉ መነሻ ሆኗል የተባለው ድሬክ በጉዳዩ ላይ ቃሉን እንዲሰጥ በፖሊስ ሳይፈለግ አይቀርም ብሏል፡፡

አንድ በሁከቱ ላይ የነበረ የካናዳዊው ሂፕሆፕ አርቲስት የቅርብ ጓደኛ ከጥሉ በኋላ ድሬክና ክሪስ በመልካም ግንኙነታቸው መቀጠል ይፈልጋሉ ብሎ ተናግሯል፡ ዘ ሰን ጋዜጣ ጥሉ ሊቀሰቀስ የቻለው ክሪስ ብራውን ለድሬክና ጓደኞቹ 2ሺ ዶላር የሚያወጣ ሻምፓኝ በግብዣ ሲልክ እነድሬክ በብጣሽ ወረቀት ፍቅረኛህን እያማገጥኩልህ ነው የሚል መልዕክት ከላከ በኋላ እንደሆነ ተወርቷል፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ ግጭቱ  በሪሃና ሳቢያ መቆስቆሱን አንዳንድ መረጃዎች በመግለፅ ላይ ቢሆኑም የሁለቱ የሂፕ ሆፕ ኮከቦች ያበጠ ባህርያ መጠጥ ምክንያት እየተደረገም ነው፡፡በጉዳዩ ላይ ሪሃና ምንም አይነት አስተያየት ከመግለፅ መቆጠቧን የሚገልፁ መረጃዎች በአንድ ወቅት ለአንዳን ወንዶች ውድቀት ሴት ምክንያት ትሆናለች ብላ የተናገረችውን በመጥቀስ በጉዳዩ ላይ ስሟን እንዳነሱ ለማወቅ ተችሏል፡፡

 

 

 

Read 1576 times Last modified on Saturday, 23 June 2012 10:59