Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Print this page
Saturday, 23 June 2012 08:19

ፖል ማካርቲኒ ለጡረታ ገና መሆኑን ተናገረ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

ባለፈው ሰኞ 70ኛ ዓመት የልደት በዓሉን ያከበረው ፖል ማካርቲኒ ጡረታ ለመውጣት ፍላጎት እንደሌለው አስታወቀ፡፡ በንግስት ኤልዛቤት የአልማዝ ኢዮቤልዩ ላይ ባቀረበው ምርጥ ኮንሰርት አድናቆት ያተረፈው ፖል የለንደን ኦሎምፒክ መክፈቻ ላይም የሚያቀርበው ሙዚቃ ይኖራል፡፡ ፖል ማካርቲኒ እና ቤተሰቡ በአጠቃላይ 665 ሚሊዮን ፓውንድ ሃብት እንዳላቸው የሰንደይ ታይምስ የሃብታሞች ደረጃ የሚያመለክት ሲሆን ከ60 በላይ የአልበም ስራዎችን በጎልድ የሽያጭ ደረጃ በመስራትና በዓለም ዙርያ እስከ 100  ሚሊዮን ቅጂ የተሸጡ ነጠላ ዜማዎችን በመስራት በጊነስ ቡክ መስፈሩን ለማወቅ ተችሏል ፡፡ የቀድሞው የቢትልስ ሙዚቃ ቡድን አባል የነበረው ድምፃዊው በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ እውቅና ያላቸው ከ50 በላይ የዘፈን ስራዎች እንዳሉት የገለፀው ዘጋርድያን በሮክ ሙዚቃ ታሪክ የምንግዜም ምርጥ ከሚባሉት አርቲስቶች ግንባር ቀደም ተጠቃሽ ብሎታል፡፡

 

 

Read 1574 times Last modified on Saturday, 23 June 2012 08:23

Latest from