Print this page
Saturday, 23 June 2012 08:15

የቱርክ ድራማዎች ተፈላጊ ሆነዋል

Written by  ግሩም ሠይፉ
Rate this item
(2 votes)

የቱርክ የቲቪ ድራማዎች በዓለም ዓቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ተወዳጅነት እያተረፉ መምጣታቸውን ቫራይቲ መፅሄት ዘገበ፡፡ በቱርክ የተሰሩ ድራማዎች ባለፉት 5 ዓመታት 35675 ሰዓታት የቲቪ ፕሮግራሞችን በተለያዩ ዓለም ክፍሎች ስርጭት ላላቸው 76 የብሮድካስት ኩባንያዎች መሸጣቸውን ያወሳው የሮይተርስ ዘገባ በበኩሉ በተለይ ግሪክና እስራኤል የፊልሞቹ  ዋናዎቹ ደንበኞች መሆናቸውን አመልክቷል፡፡

በአሁኑ ግዜ በየዓመቱ ከ100 በላይ የቲቪ ተከታታይ ድራማዊ ፊልሞች በቱርክ እንደሚሰሩ የገለፀው ቫራይቲ ፊልሞቹ በቱርኪሽ ቋንቋ ቢሰሩም በመካከለኛው ምስራቅ ፤ በኤስያና በአፍሪካ ከፍተኛ ተመልካችና ተወዳጅነት እያገኙ ናቸው ብሏል፡ ከተጀመረ ሁለት ዓመት ያለፈው ተከታታይ የቴሌቭዥን ድራማ ፋቱማ በ80ኛው ክፍል ያበቃል፡፡ እያንዳንዱ ክፍል ከ10 ሚሊዮን በላይ ተመልካች በተለያዩ የዓለም ክፍሎች ሲያገኝ ቆይቷል ተብሏል፡፡ በዚሁ ፊልም ላይ ከሚሰሩት ተዋናዮች መካከል ቤረን ሳትና ኢንግን አካዬሬክ በሰሜን አፍሪካ እና በመካከለኛው ምስራቅ የወቅቱ ምርጥ እየተባሉ ተዋናዮች ናቸው፡፡ በፋቱማ ፊልም በቱርክ የፊልም ኢንዱስትሪ ታላቅ ክብር የሚሰጠውን የጎልደን በተር ፍላይ አዋርድ አከታትላ ለመውሰድ የበቃችው የ28 ዓመቷ ተዋናይት ቤረን ሳት ፋቱማጉል ኬተንሲ የምትባለውን መሪ ገፀባህርይ ትተውናለች፡ የ30 ዓመቱ ኢንገን አካዬሬክ ሰሞኑን የቱርክ ምርጥ የድራማ ተዋናይ ተብሎ የተሰየመ ሲሆን በፋቱማ ፊልም ላይ ካሪም ኤልጋዝን ሆኖ ይጫወታል፡፡

 

 

 

Read 4543 times Last modified on Saturday, 23 June 2012 10:58