በአሁኑ ግዜ በየዓመቱ ከ100 በላይ የቲቪ ተከታታይ ድራማዊ ፊልሞች በቱርክ እንደሚሰሩ የገለፀው ቫራይቲ ፊልሞቹ በቱርኪሽ ቋንቋ ቢሰሩም በመካከለኛው ምስራቅ ፤ በኤስያና በአፍሪካ ከፍተኛ ተመልካችና ተወዳጅነት እያገኙ ናቸው ብሏል፡ ከተጀመረ ሁለት ዓመት ያለፈው ተከታታይ የቴሌቭዥን ድራማ ፋቱማ በ80ኛው ክፍል ያበቃል፡፡ እያንዳንዱ ክፍል ከ10 ሚሊዮን በላይ ተመልካች በተለያዩ የዓለም ክፍሎች ሲያገኝ ቆይቷል ተብሏል፡፡ በዚሁ ፊልም ላይ ከሚሰሩት ተዋናዮች መካከል ቤረን ሳትና ኢንግን አካዬሬክ በሰሜን አፍሪካ እና በመካከለኛው ምስራቅ የወቅቱ ምርጥ እየተባሉ ተዋናዮች ናቸው፡፡ በፋቱማ ፊልም በቱርክ የፊልም ኢንዱስትሪ ታላቅ ክብር የሚሰጠውን የጎልደን በተር ፍላይ አዋርድ አከታትላ ለመውሰድ የበቃችው የ28 ዓመቷ ተዋናይት ቤረን ሳት ፋቱማጉል ኬተንሲ የምትባለውን መሪ ገፀባህርይ ትተውናለች፡ የ30 ዓመቱ ኢንገን አካዬሬክ ሰሞኑን የቱርክ ምርጥ የድራማ ተዋናይ ተብሎ የተሰየመ ሲሆን በፋቱማ ፊልም ላይ ካሪም ኤልጋዝን ሆኖ ይጫወታል፡፡