Print this page
Sunday, 08 December 2019 00:00

ግጥምን በመሰንቆ የኪነ ጥበብ ምሽት ማክሰኞ ይካሄዳል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(2 votes)

 በአትሮኖስ ሚዲያና ፕሮሞሽን በየወሩ የሚካሄደውና በአዲስ አበባ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚቀርበው ‹‹ግጥምን በመሰንቆ›› የኪነ ጥበብ ምሽት ማክሰኞ ህዳር 30 ቀን 2011 ዓ.ም ከቀኑ 11፡00 ጀምሮ በጊዮን ሆቴልበግሮፍ ጋርደን ይካሄዳል:: በጎንደር ከተማ ለተከታታይ ሦስት ዓመታት በድምቀትና በስኬት ሲካሄድ የነበረው የኪነ ጥበብ ምሽቱ በአዲስ አበባም በተሳካ ሁኔታ እንዲከወን አስፈላጊው ዝግጅት መጠናቀቁን የአትሮኖስ ሚዲያና ፕሮሞሽን ዋና ሥራ አስኪያጅ ትዕግስት ሲሳይ ገልጻለች፡፡
በዕለቱም ዲስኩር፣ ወግ፣ ግጥም ባህላዊ ሙዚቃና መሰል ኪነ ጥበባዊ መሰናዶዎች ለታዳሚ እንደሚቀርቡ የተገለፀ ሲሆን፣ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች አባንግ ሜቶ፣ ኤርሲዶ ለንደቦ (ዶ/ር)፣ መምህር መስፍን ሰለሞን፣ ገጣሚ ትዕግስት ማሞ ገጣሚ በላይ በቀለ ወያ ስራቸውን እንደሚያቀርቡና የመግቢያ ዋጋው 50 ብር እንደሆነ ታውቋል፡፡

Read 9408 times