በጣልያን ባህል ማዕከል አዘጋጅነት የሚካሄደው ‹‹ሙዚቃ በየአይነቱ›› የሙዚቃ ድግስ ማክሰኞ ህዳር 30 ቀን 2012 ከምሽቱ 12፡30 ጀምሮ በኢትዮጵያ ብሄራዊ ቴአትር ይካሄዳል፡፡ ኮንሰርቱ ታዋቂው የጣሊያን የሙዚቃ ባንድ ‹‹ኦርኬስትራ ፒያሳ ቪቶሪያ››፣ የባህል አምባሳደሩ ከያኒ መላኩ በላይና “ኢትዮ ከለር ባንድ” የተጣመሩበት ሲሆን በምሽቱ የተለያዩ የሙዚቃ ተጫዋቾች ስራዎቻቸውን በልዩ ዝግጅት የሚያቀርቡበት ነውም ተብሏል፡፡ በዚህ ኮንሰርት ላይ ለመታደም የመግቢያ ዋጋ የማያስከፍልና በነፃ መዝናናት የሚቻልበትም ነው ተብሏል፡፡