Saturday, 23 June 2012 08:08

የኒጀሩ ጊታሪስት ሙዚቃ ነፃነት ነው አለ

Written by  መልካሙ ተክሌ (melkamutekele@gmail.com)
Rate this item
(0 votes)

ታዋቂው ኒጀራዊ ሙዚቀኛ ኦማር ቦምቢኖ ሙክታር ሙዚቃ ነፃነት ነው ሲል ለሲኤን ኤን ተናገረ፡፡ ጊታሩን በበርሃ መጫወት ስለሚያበዛ የበረሃው የጊታር ጀግና ተብሎ ለመወደስ የበቃው ቦምቢኖ በሮክና ብሉስ ሙዚቃዎቹ በሰሜን አፍሪካና በመካከለኛው ምስራቅ ተወዳጅነት አትርፏል፡፡ በ12 ዓመቱ ጊታር መጫወት የጀመረው ቦምቢኖ የማሊውን አሊ ፋሩካ ቱሬና ጂሚ ሄንድሪክስን እንደተምሳሌት ይመለከታል ያለው የሲኤን ኤን ዘገባ በሙዚቃ ህይወቱ ስለወገኖቹ ችግርና ሰቆቃ የፈለገውን በመናገር የታገለ አርቲስት ብሎ አድነቆታል፡፡

በዘርግንዱ ከዘላኑ የበርበር ጎሳ ቱሬግ የሚዛመደው ኦማር ቦምቢኖ ሙክታር  ከ3 ዓመት በፊት ለወገኖቹ ነፃነት በሚወጋ ቡድን ውስጥ ተቀላቅሎ እነደነበረ የገለፀው ሲኤን ኤን በትግል ወቅት ሁለት ሙዚቀኛ ጓደኞችን በሞት ተነጥቋል ብሏል፡፡ ቦምቢኖ ባለፈው ዓመት ‹ኦጋዴስ ዘሚውዚክ ኤንድ ዘ ሬበሊዮን› በተባለ ጥናታዊ ፊልም ተውኖ አለም አቀፍ እውቅና አግኝቷል፡፡

 

 

 

Read 982 times Last modified on Saturday, 23 June 2012 08:11