Print this page
Saturday, 07 December 2019 12:09

አለም አቀፍ የበጎ ፈቃደኞች ቀን ተከበረ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

    ዓለም አቀፍ የበጎ ፈቃደኝነት ቀን ትላንት በአምባ (ENPA) አስተናጋጅነት ተከበረ፡፡ በዕለቱ በርካታ የክብር እንግዶችና በጎ ፈቃደኞች የታደሙ ሲሆን የተባበሩት መንግስታት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ መልዕክት በተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም (UNDP) የኢትዮጵያ ወኪል በሆኑት አቶ እንድሪያስ ጌታቸው በኩል ተነቧል፡።
ከዚህም በተጨማሪ የተለያዩ በበጎ ፈቃደኝነት ላይ የሚሰሩ ተቋማት በበጎ ፈቃደኝነትና በቱሩፋቱ ዙሪያ ያላቸውን መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን በዝግጅቱም ላይ የዚህ አመት የበጎ ፈቃደኝነት ቀን አከባበርን ያዘጋጁት የኮሚቴ አባላት የዩኤን ሸለንቲርስ፣ Cuso፣ Vos፣ እና CCM የተሰኙት ተቋማት ለተቋሙ ከመቶ ሺህ ብር በላይ የሚያወጣ ድጋፍ ማድረጋቸውን አምባ (ENPA) ገልጿል፡፡ በመርሃ ግብሩ ላይ የተለያዩ የመዝናኛ ዝግጅቶች የቀረቡ ሲሆን በተቋሙ ቅጥር ግቢ ውስጥም የችግኝ መትከል ሥነ ሥርዓት መካሄዱን የፕሮግራሙ አስተናጋጅ አምባ ገልጿል፡፡    

Read 10519 times