Print this page
Saturday, 23 June 2012 08:06

የፓኪስታኗ ድምፃዊት አሟሟት አሳዘነ

Written by  ግሩም ሠይፉ
Rate this item
(0 votes)

ሰሞኑን በሰሜን ምእራብ ፓኪስታን በምትገኝ  ፔሽዋር ከተማ በግፍ የተገደለችው የ24 ዓመቷ ድምፃዊት ጋዛላ ጃቬድ አሟሟት አድናቂዎቿን ማሳዘኑን ዘ ሂንዱስታን ታይምስ ዘገበ፡፡ የታሊባን ሃይሎች የሙዚቃና ዳንስ ክልከላ በማድረግ የጣሉትን ገደብ በመጣስ ከፍተኛ መስዕዋትነት የከፈለች አርቲስት በሚል የአርቲስቷን ሞት በርካታ ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ዘግበዋል፡፡ በፓኪስታንና በአፍጋኒስታን የፓሻት ቋንቋ በሚናገሩ ህዝቦች ከፍተኛ እውቅና ያላት ጋዛላ ባለፈው ማክሰኞ ከቁንጅና ሳሎን ስትወጣ ባልታወቁ ታጣቂዎች በስድስት ጥይት ተመትታ ህይወቷ ያለፈ ሲሆን አብረዋት የነበሩ አባቷም መገደላቸው ታውቋል፡፡ የፓኪስታን ፖሊስ ለግድያው የመጀመርያ ተጠርጣሪ ያደረገው የድምፃዊቷን የቀድሞ ባል ቢሆንም አንዳንድ መረጃዎች ጋዛላ ጃቬድ በታሊባን አማፂዎች ሳትገደል አይቀርም በሚል ዘገባዎች ተነብበዋል፡፡

ጋዛላ ጃቬድ በርካታ የታሊባን አማፂዎች በሚገኙባት ፔሽዋር የተባለች ከተማ ትኖር እንደነበር ያወሳው ዘ ሂንዱስታን ታይምስ ከ3 ዓመት ከዚሁ ከተማ ስትወጣ በታሊባን አክራሪ ሃይሎች ጥቃትን በመሸሽ  እንደነበር ገልፀል፡፡ ፓኪስታናዊቷ ጋዛላ ጃቬድ በ8 አመት ውስጥ ስድስት አልበሞችን የሰራች ስትሆን በመካከለኛው ምስራቅና ኤስያ ዱባይ ፤ ካቡል እና ኩዋላላሙፕርን ጨምሮንበ10 ከተሞች ኮንሰርት ያቀረበች ነበረች፡፡

 

Read 684 times