Saturday, 30 November 2019 13:55

በሀሳብ መንገድ ላይ

Written by  ተመስገን
Rate this item
(1 Vote)

  “--በነገራችን ላይ ግን ዳን ብራውን በ‹‹ዳቪንቺ ኮድ›› መጽሐፍ እንዳሰፈረው ዓይነት ሰለሞናዊው ንቅናቄም መልዕክቶቹ፣ ዘመን ተሻግረው ለትውልድ የሚተላለፉት፤በረቂቅ ሙዚቃዎች፣ በሥዕሎች፣ በአርኪቴክቸርና ሥነ ሕንጻ ውጤቶችበመሳሰሉት መንገዶች ነው፡፡--”
           
            ‹‹ሃሎ››
‹‹ይሰማኛል››
‹‹እየመጣሁ ነው››
ቀኑን፣ ቦታውንና ሰዓቱን ነገረው፡፡ ደዋዩ በአውሮፓ የዓለም አቀፍ ሰሎሞናዊ ንቅናቄ (ISM) አክቲቪስት ነው … ኢትዮጵያዊ፡፡ የተደወለለት ደግሞ የዚህ አገር የንቅናቄው ክንፍ አስተባባሪ ነው፡፡ ንቅናቄው በመላው ዓለም የሚገኙ የሁሉም እምነቶች ተከታዮች የሆኑ ብዙ አባላት አሉት፡፡ ዋናው ማዕከሉ ቻይና ይገኛል:: ቻይና የተመረጠችው በሁለት ምክንያት ነው:: አንድም የሁለቱ ጠቢባንን (የኮንፊሽየስና  የሰለሞንን) ወዳጅነት ለማስታወስ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ቻይና አቻ የሌለው የእምነት መንገድ እናት በመሆኗ ነው… የጣዖኢዝም!!
ንቅናቄው  ወዳጆች እንዳሉት ሁሉ… ተቀናቃኞቹም ብዙ ናቸው::  አንዳንድ አለም አቀፍ የስለላ ድርጅት ባለሥልጣናት፤ የንቅናቄውን አባሎች ማወቅና መለየት ይፈልጋሉ፡፡ ‹‹ከምንም ነገር በላይ ሰው መሆን ይበልጣል›› የሚለውን የንቅናቄውን መርህ አልወደዱትም፡፡
ሰውየው ስልኩን ሲዘጋ ንግግራቸው መጠለፉን አላወቀም፡፡ ንግግራቸው ከጠላፊዎቹ ጋር በትብብር ለሚሰራው የኢትዮጵያ የደህንነት ተቋም ኢ.ሜይል ተደረገ፡፡ ሰዎቹ በቀጠሯቸው መሰረት… ሲገናኙ ተከታትለው እንዲቀርጿቸውና እንዲያሳውቋቸው አደራና ስራ ማስኬሃጃ ላኩ፡፡
የቀጠሮው ቀን ደረሰ፡፡ ደህንነቱ የከተማዋን ጠጅ ቤቶች ተቀጣጥሮ እንግዶቹን ይጠባበቃል:: ድግሱን የማያውቁት ሰዎች ግን በተቃጠሩበት ሰዓትና ቦታ ተገናኝተው፣ ጉዳያቸውን ጨርሰው ተሰነባብተዋል፡፡ ከውጭ የመጣው ሰው ለተመሳሳይ ስራ በማግስቱ ዑጋንዳ ነበር፡፡ … እንዴት ተላለፉ?
***
ታላላቅና ባህላዊ የሆኑ እምነቶች ሳይቀሩ ሁለትና ሶስት ቦታዎች ተሰነጣጥቀዋል፡፡ ጄኒዝምና ቡድሂዝም የተወለዱት ከ‹ሂንዱ› እምነት ነው፡፡ ታላቁ ራማ ክርሽና እንዳለው፤ ሁሉም አንድ ዓይነት መዳረሻ ያላቸው የተለያዩ መንገዶች ናቸው፡፡ ጥያቄው፡- መንገድ እንጂ መዳረሻ እስካልሆኑ ድረስ ስለ ምን እርስ በርሳቸው እየተጋጩ… ተከታዮቻቸውን ያደናግራሉ የሚል ነው፡፡ መልሱን ለባለቤቱ እተወዋለሁ፡፡ ዕምነት የግል ነውና!!
ኮንፊሺያኒዝምና ቡዲሂዝም እንዳሉ ሆነው፣ የዓለም አንድ አራተኛ ያህል ሕዝብ የሚከተለው ጣዖኢዝምን (Taoism) እንደሆነ ተጽፏል፡፡ ጣዖ ከሁለት ሺ ዓመታት በላይ ሳይንገጫገጭ የዘለቀና ‹ፍፁም› የሚያስብል እምነት ነው፡፡ ‹ጣዖ› ማለት መንገድ (way, road, path) ማለት ሲሆን ወደ እውነተኛው ቦታ ለመድረስ የፈለገ ሰው የሚራመድበት ወይም ሊኖረው የሚገባ ሥርዓት (method )፣ መርህ (principle) እና ቃለ ብፅዓት (doctrine) ብለው ይተረጉሙታል … ሊቃውንቶቹ፡፡
‹ጣዖ› በሌላው ስሙ ‹የተፈጥሮ መንገድ› በመባልም ይታወቃል። ሰው የተፈጥሮን ምስጢር በገለጠ ቁጥር ከጣዖ ጋር እየተዋሃደ ይመጣል፤ ለማንኛውም ጉዳትና ህመም (physical harm and disease) አይጋለጥም፣ በፍፁም ሰላም የሚኖርበትን ባህርያ ያዳብራል ይላሉ፡፡ ቢሞት እንኳ ስጋው እንጂ የመንፈሱ ህላዌ ብርሃን፣ ዘለዓለማዊነቱ እንደማይደበዝዝ በቅዱሱ መጽሐፍ ‹‹Tao Te ching›› ምዕራፍ 16 ላይ ተከትቧል፡፡
“Being at one with the Tao is eternal. And thogh the body dies, the Tao will never pass away”
‹ጣዖ› እንደ እምነት መመለክ ከመጀመሩ በፊት ከፍልስፍና (none passive philosophy) ጋር የሚነጻጸርበት ማዕዘናት እንዳሉ  ጥናቶች ያሳያሉ፡፡ በጎሽ ጀርባ ተቀምጦ ከሚኖርበት የ‹ቹ› ግዛት በመነሳት ወደ ሌሎች ቦታዎች እየተዘዋወረ ሲያስተምር የነበረው የዕምነቱ አባት ላዖ-ፁ (Lao-tzu) በመባል ይታወቃል፡፡ ትርጉሙም ሽማግሌው (Old one, old master)  ማለት ነው፡፡ ሽማግሌ ያሰኘውም በናቱ ሆድ፣ ብዙ ዘመን በመቆየቱ ሲወለድ ሸብቶ ስለነበረ ነው፡። የ‹ጣዖ› ፈላስፋ የሚባለው የዚህ አባት ዕውነተኛው ስሙ ግን ሊ-ኤር (Li-Erh) ነው፡፡
‹ጣዖ›፤ እኛ  ‹እግዜር› የምንለውን፣ ፈጣሪ ወይም ‹Creator God› መኖሩን አይቀበልም። የነበረው፣ ያለውና የሚኖረው ‹ጣዖ› ብቻ ነው ይለናል፡፡
Born before heaven and earth
 Nourished by virture (Te)
Formed from matter
Shaped by environment…
call it Tao
***
ወደ ጨዋታችን ስንመለስ፡- ለአዲስ አበባው የደህንነት ቢሮ የተላከው ኢ-ሜይል፤ የሰዎቹን የቀጠሮ ቦታና ሰዓት በመጥቀስ ‹‹ጅማ ውስጥ ታገኘኛለህ፣ ትልቁ ጠጅ ቤት፣ ለማንኛውም ቀኝና ግራውን እየተገላመጥክ ተራመድ›› ይላል:: ይህን ለመረዳት የአገር ቤቱ ሰው አልተቸገረም:: ‹Jimma› የሚለው መጠሪያ ውስጥ ‹‹Maji›› የሚል የሌላ ከተማ ስም አለ፡፡ ይኸን ቢዘነጋ እንኳን የከተማው ስም በአማርኛ ተጽፎ ከቀኝ ወደ ግራ ሲነበብ ‹ማጂ› የሚል እንደሆነ ፍንጭ አግኝቷል፡፡ ስለዚህ የሰዎቹ ቀጠሮ ማጂ ነበር ማለት ነው፡፡ ለደንባራው ለኛ ደህንነት መስራች ግን ‹‹ፍየል ወዲህ ቅዝምዝም ወዲያ!›› ነበር፡፡
በነገራችን ላይ ግን ዳን ብራውን በ‹‹ዳቪንቺ ኮድ›› መጽሐፍ እንዳሰፈረው ዓይነት ሰለሞናዊው ንቅናቄም መልዕክቶቹ፣ ዘመን ተሻግረው ለትውልድ የሚተላለፉት፤ በረቂቅ ሙዚቃዎች፣ በሥዕሎች፣ በአርኪቴክቸርና ሥነ ሕንጻ ውጤቶች በመሳሰሉት መንገዶች ነው፡፡ ዓላማው ከሚታይ፣ ከሚጨበጥና ከሚደመጥ ነገር ውስጥ ከነሱ የበለጠ አቅም ያለውን፣ ነገር ግን የማይታየውን ኢነርጂ ‹ኮንሲቭ› ማድረግ መቻል ነው - የአንስታይን ፎርሙላ ወይም የ‹Tao› መንገድ እንደሚነግረን፡፡
ወዳጄ፡- ቅድም የሰሎሞናዊው ንቅናቄ ማዕከል ቻይና ነው ብዬ ነበር፡፡ ከሰሞኑ ደግሞ የታላቁ የቻይና ኩባንያ አሊባባ ጃክማ አዲስ አበባ ነበሩ፡፡ አሊባባ የብልህ አረብ ወጣት ስም ሲሆን ‹‹Alibaba and the forty thieves› ምርጥ የአረቦች ተረት ነው፡፡ በዚያን ዘመን በድምፅ ‹ኮድ› የሚከፈትና የሚዘጋ የዋሻ በር እንደነበር ማሰብ አያስደንቅም?
የሆነው ሆኖ ወዳጄ፡- ሰለሞናዊውን ንቅናቄ፣ ቻይናና አረብን ምን አስተሳሰራቸው? ብለህ አትጠይቅም? መልሱን W.B Yeats ይነግረሃል፡፡
… There is not a thing
  But love can make
The world a narrow pound
Solomon to Sheba (1918)
መደመር!!
ሠላም!!

Read 1516 times