(ስለ ስደት)
• እኛ የዚህ አህጉር ሰዎች፣ የውጭ ዜጎችን አንፈራም፤ አብዛኞቻችን በአንድ ወቅት የውጭ ዜጎች ነበርን፡፡
ፖፕ ፍራንሲስ
• አሜሪካውያን ወገኖቼ፤ እኛ ሁሌም የስደተኞች አገር ነን፡፡ የሆነ ዘመን ላይ እኛም ራሳችን ለአገሩ ባዕድ ነበርን፡፡
ባራክ ኦባማ
• ሁላችንም ስደተኞች ነን፡፡ አንዳንዶች ግን ይሄን ረስተውታል፡፡
ያልታወቀ ሰው
• እዚህ አገር የሚመጣ እያንዳንዱ ስደተኛ፣ በአምስት ዓመት ውስጥ እንግሊዝኛ እንዲማር አ ሊያም ወ ደ አገሩ እንዲመለስ መገደድ አለበት፡፡
ቲዎዶር ሩዝቬልት
• እኔ፤ ሕጋዊ ስደትን ደጋፊ ነኝ፡፡
ሂዘር ዊልሰን
• እያንዳንዱ የአሜሪካ ኢኮኖሚ ዘርፍ፣ እዚህ አገር ከመጡ ስደተኞች አስተዋጽኦ ተጠቅሟል፡፡
ጆን ኤፍ ኬኔዲ
• ስደት ዕድል እንጂ መብት አይደለም፡፡
ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ
• ሕገ ወጥ ስደተኞች ወደ አገራቸው እንዲመለሱ መገደድ አለባቸው፡፡
ሚት ሮምኒ
• ስደትን ከእነ አካቴው ማቆም አለብን እያልኩ አይደለም፤ ሰዎች ከየትም ሥፍራ ሊመጡ ይችላሉ፡፡
ጄብ ብራድሌይ
• እኔ ስደትን እደግፋለሁ፤ ግን ደግሞ ሕጎችም ያስፈልጉናል፡፡
ጌሪ አክማን
• እንደ ሌሎች ሕግ አክባሪ አሜሪካውያን ሁሉ፤ ሕጋዊ ስደትን ሙሉ በሙሉ እደግፋለሁ፡፡
ቴድ ኑጀንት
Published in
ጥበብ