Saturday, 16 November 2019 11:28

ኦነግ ሀገር አቀፍ ፓርቲ ሆኖ ተመዘገበ

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(0 votes)

በአቶ ዳውድ ኢብሣ የሚመራው የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ)፤ ሀገር አቀፍ ፓርቲ ሆኖ በምርጫ ቦርድ መመዝገቡን ያስታወቀ ሲሆን ድርጅቱ በመላ ሀገሪቱ የፖለቲካ እንቅስቃሴውን እንደሚያደርግ አስታውቋል፡፡ ‹‹የምዝገባ ሠርተፊኬት አግኝቻለሁ፤ ደስ ብሎኛል፤ እንኳን ደስ አላችሁ›› በማለት ድርጅቱ ትናንት ከሰዓት በኋላ ባሠራጨው መግለጫው፤ ከተመሠረተ 46 አመት ቢሆነውም እስከዛሬ በኢትዮጵያ በህጋዊነት ተመዝግቦ እንደማያውቅ ጠቁሟል፡፡
ድርጅቱ በኢትዮጵያ የፌደራሊዝም ስርአት ግንባታ ተጠናክሮ እንዲቀጥል የሚያደርግ የትግል አቅጣጫ ለመያዝ በመላ ሀገሪቱ ጽ/ቤቶችን በመክፈት ለመንቀሳቀስ መወሰኑንም አስታውቋል፡፡ ኦነግ ከዚህ በኋላ በሠላማዊና ዲሞክራሲያዊ መንገድ ብቻ እንደሚንቀሳቀስና አሳካዋለሁ የሚለውን የትግል ግብ ላይ ለመድረስም ፓርቲውን የወጣቶች ፓርቲ በማድረግ ላይ አተኩሮ እንደሚሠራ በመግለጫው ጠቁሟል፡፡
አሁንም በሀገሪቱ በርካታ ውስብስብ የፖለቲካ ችግሮች መኖራቸውን በመግለጽ፤ ሁሉም ሀይሎች እነዚህ ችግሮች በሚፈቱበት ሁኔታ ላይ አተኩረው እንዲንቀሳቀሱ ጥሪ አቅርቧል፡፡  


Read 1466 times