Monday, 18 November 2019 00:00

“The Habesha Chronicles” በአማዞን ድረገጽ ለገበያ ዋለ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(1 Vote)

 በደራሲ  መርስኤ ኪዳን በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተዘጋጀው  “The Habesha Chronicles” የተሰኘ ታሪክ ላይ የሚያጠነጥን መፅሐፍ፣ በኣሜሪካ የኢፌዲሪ ቆንስላ፣ አምባሳደር እውነቱ ብላታ በተገኙበት የተመረቀ ሲሆን ከሰሞኑ በአማዞን ድረ ገጽ ላይ ለሽያጭ ቀርቧል፡፡ መጽሐፉ፤ ከአክሱም ዘመነ መንግስት አንስቶ እስከ ሰለሞናዊው መንግስት ፍፃሜ ድረስ ያለውን የሐበሻ ህዝብ ታሪክ ያስቃኛል ተብሏል፡፡
ከንግስተ ሳባ እስከ ንጉስ ኢዛና፣ ከኣፄ ካሌብ እስከ ንግስት ዮዲት (ጉዲት)፣ ከላሊበላ እስከ አሕመድ ኢብን ዓልጋዚ (ግራኝ ኣሕመድ)፣ ከሸዋ ነገስታት እስከ ኦሮሞ መስፋፋት፣ ከዘመነ መሳፍንት እስከ ዘመናዊት ኢትዮጵያ ምስረታ፣ ከኣድዋ ጦርነት እስከ መጨረሻው የኢትዮጵያ ንጉስ አሟሟት ድረስ ያሉት ታሪኮች ቀለል ባለ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ተተርከዋል - The Habesha Chronicles  በተሰኘው መጽሐፍ፡፡  
መፅሐፉን በኢንተርኔት  ከአማዞን ድረገፅ ላይ መግዛት የሚቻል ሲሆን በቅርቡ በአትላንታ፣ በዋሺንግተን ዲሲ፣ በዴንቨርና ሌሎች የአሜሪካ ከተሞች፣ የማስተዋወቂያ ፕሮግራምና የደራሲው የፊርማ ሥነሥርዓት እንደሚካሄድ  ለማወቅ ትችሏል።

Read 8246 times