Monday, 11 November 2019 00:00

‹‹የኢትዮትያ ቴአትርና ሥነ - ጽሑፍ ታሪክ ከልደቱ እስከ እድገቱ” መጽሐፍ ለንባብ በቃ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)


            የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቴአትር መምህር በሆነው ደራሲ ዳኜ አበበ የተሰናዳውና የኢትዮጵያን ቴአትርና ስነጽሑፍ እድገት ከትላንት እስከዛሬ የሚፈትሸው “የኢትዮጵያ ቴአትርና ሥነ ጽሑፍ እድገት ከልደቱ እስከ እድገቱ” የተሰኘ መጽሐፍ ለንባብ በቃ፡፡
መጽሐፉ በዋናነነት ስለ ኪነ-ጥበብና ዘርፈ ብዙ ክንዋኔዎቹ፣ ስለኪነ-ጥበባዊ ሂሶች፣ ስለ ሥነ ጽሑፋዊ ድንጋጌዎች፣ ስለ ፈር ቀዳጅ የስነ ጽሑፍ ደራሲያን፣ ስለ ቴአትር ጥቅሞች፣ ስለዘመናዊ ቴአትር አጀማመር፣ ስለ አራቱ ቴአትር ቤቶች፣ ስለ ባህል ማዕከላት፣ ስለ ፀሐፊ ተውነቶች፣ ስለ ቴአትር ልሂቃንና በጠቅላላ በቴአትርና በስነጽሑፍ እድገትና ውጣውረድ ዙሪያ ሰፊ ትንታኔ ከመስጠቱም በላይ ለቴአትርና ለስነ ጽሑፍ የወደፊት እድገት የሚጠቅሙ የመወያያ ጥያቄዎችን አንስቷል፡፡ በ443 ገጽ የተቀነበበው መጽሐፉ በ200 ብር ለገበያ ቀርቧል፡፡

Read 480 times