Print this page
Saturday, 09 November 2019 11:44

የዋሺንግተን ዲሲ ከንቲባ ዛሬ አዲስ አበባ ይገባሉ

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(2 votes)

   የአሜሪካ ዋና ከተማ ዋሺንግተን ዲሲ ከንቲባ ሞዩሪየል ባውዘር ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ም/ከንቲባ ኢ/ር ታከለ ኡማ በቀረበላቸው ግብዣ መሠረት ዛሬና ነገ በአዲስ አበባ ጉብኝት ያደርጋሉ ተብሏል፡፡
የአሜሪካ ኤምባሲ በድረ ገፁ ባሠራጨው መግለጫ፤ ከንቲባዋ ለመጀመሪያ ጊዜ በሚያደርጉት በዚህ ጉብኝት ላይ ከ50 በላይ የአሜሪካ የንግድ ማህበረሰብ አባላት አብረዋቸው እንደሚመጡ አስታውቋል፡፡
የንግድ ማህበረሰብ አባላቱ በሁለት ቀን ቆይታቸው በኢንቨስትመንት አማራጮች ላይ ውይይት እንደሚያደርጉ ታውቋል፡፡
አዲስ አበባና ዋሺንግተን ዲሲም እህትማማች ከተማነታቸውን የሚያድስና በበርካታ የኢኮኖሚ ትስስሮች ላይ ያተኮረ አዲስ ስምምነት ይፈራረማሉ ተብሏል፡፡
ከንቲባዋ ወደ አዲስ አበባ ዛሬ የሚመጡት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ም/ከንቲባ ታከለ ኡማ ባለፈው ነሐሴ ዋሺንግተን ዲሲን በጐበኙበት ወቅት ባቀረቡላቸው ግብዣ መሠረት እንደሆነ ታውቋል፡፡

Read 8988 times