Saturday, 09 November 2019 11:30

የታገል ሰይፉ “ብስጦሽቁዋጭ ቁዋጣሽቆር” ለንባብ በቃ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(3 votes)

በገጣሚ ታገል ሰይፉ የተጻፈውና በጎጠኝነትና በሚያስከትላቸው መዘዞች ዙሪያ የሚያጠነጥነው “ብስጦሽቁዋጭ ቁዋጣሽቆር” የተሰኘ አዲስ የልቦለድ መጽሐፍ ትናንት በገበያ ላይ መዋሉ ተነግሯል፡፡
ለደራሲው ሰባተኛ ስራው የሆነውና መቼቱን በአንዲት ምናባዊት አገር ላይ ያደረገው “ብስጦሽቁዋጭ ቁዋጣሽቆር” የስላቅ ዘውግ ያለውና በ176 ገጾች የተቀነበበ ሲሆን፣ በቡክሳይት አከፋፋይነት በ100 ብር የመሸጫ ዋጋ ለገበያ ቀርቦ በአዲስ አበባና በክልል ከተሞች በመጽሐፍት መደብሮችና በአዟሪዎች እየተሸጠ መሆኑንም ለማወቅ ተችሏል፡፡
በ16 አመት ዕድሜው “ፍቅር” የተሰኘ የመጀመሪያ መጽሐፉን ለንባብ ያበቃው ገጣሚ ታገል ሰይፉ ከዚህ ቀደም “ቀፎውን አትንኩት”፣ “ሌዋታን”፣ “ሃምሳ አለቃ ገብሩ”፣ “የሰዶም ፍጻሜ”፣ “የዕድሜ ጅረት” እና “በሚመጣው ሰንበት” የተሰኙ የግጥምና የልቦለድ መጽሐፍትን ለንባብ ያበቃ ሲሆን፣ በተንቀሳቃሽ ምስል የታገዙ ሁለት ሲዲዎችንም ለህዝብ ማቅረቡ ይታወሳል፡፡
ለረጅም አመታት በተለያዩ ሬድዮ ጣቢያዎች ለአድማጭ ሲያቀርበው የነበረውን “ሃምሳ አለቃ ገብሩ” የተሰኘዉን ተራኪ ግጥሙን በቅርቡ በምስል በማገዝ በኢቢኤስ ቴሌቪዥን በየሳምንቱ ለተመልካቾች ማቅረብ መጀመሩም ይታወቃል፡፡


Read 7963 times